Connect with us

የዱባዩ መጠጥ ቤት ለሴቶች  ያቀረበዉ አስገራሚ ስጦታ

የዱባዩ መጠጥ ቤት ለሴቶች  ያቀረበዉ አስገራሚ ስጦታ
Photo: Facebook

አስገራሚ

የዱባዩ መጠጥ ቤት ለሴቶች  ያቀረበዉ አስገራሚ ስጦታ

የዱባዩ መጠጥ ቤት ለሴቶች እንደየክብደታቸዉ የነፃ መጠጥ ስጦታ ማበርከት ጀመረ

በዱባይ ሀገር የሚገኝ አንድ መጠጥ ቤት ለሴት ደንበኞቹ ክብደታቸዉን መሰረት በማድረግ ነፃ የመጠጥ ስጦታ ማበርከት መጀመሩ እያነጋገረ ነዉ ሲል ዩ.ፒ.አይ ዘግቧል፡፡

ይህ መጠጥ ቤት ክብደትዎ በጨመረ ቁጥር በርከት ያለ መጠጥ በነጻ ያገኛሉ በማለት ለሴት ደንበኞቹ “It is good to gain weight” በማለት የማስተዋወቂያ ጥሪ እያሰማ ይገኛል፡፡

ካሴልስ አልባርሽ በተባለዉ ሆቴል ዉስጥ የሚገኘዉና ፊዩዥን በመባል የሚጠራዉ ይህ የምሽት ክለብ አስከ መጭዉ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ድረስ እንደሚቀጥል የገለጸዉ ይህ የነፃ መጠጥ ግብዣ ለሴቶች ብቻ የቀረበ ሲሆን ደንበኞቹ ለእያንዳንዱ አንድ ፓዉንድ ክብደታቸዉ 0.12 ዶላር ዋጋ ያለዉ የነፃ መጠጥ ይበረከትላቸዋል፡፡ ይህ ማለት 150 ፓዉንድ የምትመዝን እንስት የ18.50 ዶላር ነፃ መጠጥ ትረከባለች፡፡

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እንደገለፀዉ ከሆነ በምሽት ቤቱ የክብደት መለኪያ ሚዛን የተቀመጠ ሲሆን ማንኛዋም ደንበኛ ክብደቷን እንድትለካ እየተደረገ የምትስተናገድ ይሆናል፡፡ ይህንን ማድረግ አልፈልግም ያሉ ደንበኞች ደግሞ ክብደታቸዉን ለአስተናጋጆች በመንገር ብቻ የነጻ አገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

“መጠጥ ቤቱ መግቢያ ላይ የክብደት መለኪያ ማሽን ያስቀመጥን ቢሆንምደንበኞች እንዲመዘኑ አናስገድድም” ሲል አኒል ኩማር የተባለዉ የሆቴሉ ምግብና መጠጥ ማናገር ይናገራል፡፡

“በሴት ደንበኞቻችን ትልቅ እምነት አለን” የሚለዉ አኒል “የክብደት መጠናቸዉን ብቻ በቁራጭ ወረቀት ላይ በመፃፍ ለአስተናጋጆች በታማኝነት በመስጠት ብቻ በክብደታቸዉ ልክ የሚገባቸዉን ነፃ መጠጥ በመዉሰድ መዝናናት ይችላሉ፡፡ ሌላ ምንም ቅድመ ሁኔታአላስቀመጥንም፡፡

መሸታ ቤቱ ይህንን የነፃ መጠጥ ስጦታ ለማስተዋወቅ የተጠቀመበት መሪ ቃል ግብ አሁንም ብዙዎችን እያስገረመ ነዉ፡፡ “It is good to gain weight” “መወፈርሽ ለመልካም ነዉ” እንደማለት ነዉ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top