Connect with us

“የቀጣይ የህወሓት ዕድል በፍቃዱ አይወሰንም በአብይም አይወሰንም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

የቀጣይ የህወሓት ዕድል በፍቃዱ አይወሰንም በአብይም አይወሰንም
Photo: Reuters

ፓለቲካ

“የቀጣይ የህወሓት ዕድል በፍቃዱ አይወሰንም በአብይም አይወሰንም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

“ቀፃሊ ዕድል ህወሓት፣ ብኣባላት ህወሓት፣ ብደገፍቲ ህወሓትን ብህዝቢ ትግራይን እዩ ዝዉሰን።”

“የቀጣይ የህወሓት ዕድል በፍቃዱ አይወሰንም በአብይም አይወሰንም። ቀጣይ ዕድላችን በህወሓት አባላት፣ በህወሓት ደጋፊዎችና በትግራይ ህዝብ ነው የሚወሰነው።” – አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ (ቪኦኤ )

“የኢህአዴግ ስብሰባ አጀንዳ መናገር አልፈለገም ነበር ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ስብሰባ ጠሩ ነሀሴ 20 የአራቱ ድርጅቶች ሪፓርት ተፅፎ እንዲቀርብ እና እሱን መሰረት አድርግን የት ነው ያለነው የሃሳብ እና የተግባር አንድነታችን ምን እንደሚመስል ለመገምገም ቀጠሮ ይዘን ነበር።

እኛ ህወሓቶች ሪፓርት ልከናል ነሀሴ 20 እየጠበቅን ነበር ግን ስብሰባ ሰይጠራ ቀረ ስብሰባ የማድረግ ፍላጎትም አልነበረም። ምክንያቱም ሊቀ መንበሩ ቡድን የሚመራው ውህደትን በተመለከተ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነበር በሌሎች አካባቢዎች።

እኛ ሀገራዊ ሁኔታው እንገምግም ነበር ያልነው። ሊቀ መንበሩ የተዘጋጃ ሪፓርት የለም ብለው ተናገሩ ሌላ ግዜ ሰፊ ግዜ ወስደን እንወያያለን አሉ። በኛ በኩል ምርጫም እየቀረበ ስለሆነ ዝግጅት እየተደረገ ስላልሆነ እንወያይ ብለን አቀረብን ሁለተኛው አጀንዳ አቀረብን ሶስተኛው አጀንዳ ደግሞ የተጠና ጥናት አለ ማየት እንችላለን ሀሳብ መስጠት እንችላለን ብለን አቀረብን።

ሊቀ መንበሩ ግን የሰላምና የደህንነት ሁኔታው ለመገምገም ሰፊ ዝግጅት ስለሚያስፈልገን እንዲሁም ሪፓርትም ሌሎች አላቀረቡም ህውሓት ብቻ ነው ያቀረበው ሶስቱ ብሔራዊ ድርጅቶች ሪፓርት ስላላቀረቡ ማታረም እንዳለበት ገልፀው በቀጣይ ስብሰባ እናየዋለን የሚል ሀሳብ ቀረበ። እኛ ሀገራዊ ሁኔታው ይገምገም አልን ድምፅ ይሰጥ ተባለ ሁለቱ ይቅረብ የምትሉና አንዱ ብቻ ተባለ ወቅታዊ ሁኔታ አንገብጋቢ አይደለም የሚል ሀሳብ አሸነፈ በድምፅ ማለት ነው፡፡

ውህደት የሚባል እንደ ሓሳብ እንደ ፕሪንስፕልም ልትቀበለው ከሆነ ፕሮግራም ሊኖር ይገባል። በየትኛው የሀሳብ ዙሪያ ነው የምትሰባሰበው? የፖለቲካ ፓርቲ ይቅርና አልሙኒ አሶሴሽንም ቢያንስ በአንድ ትምህርት ቤት በዚህ ዓመት የተማርን ሰዎች ልንሰበስብ ነው ብለህ ነው ስብሰባ የሚጠራው።

ስለዚህ ትርጉም የሌለው ፕሮግራም የሚባል ሕገ-ደንብ የሚባል የሌለው ውህደት የሚባል ንግግር vote ሊደረግ የለበትም አይገባም። እንደዚህ ዓይነት ሀሳብም የለም። ልመና ሊባል በሚችል መልኩ ነው ያቀረበው ሊቀመንበሩ። በቃ እመኑኝ እኔ ብዙ ሀሳብ አለኝ የኢህአዴግ ሀሳብ ለማስቀጠል ነው የምፈልገው ምናምን ብሎ ብዙ ተናግረዋል። ከዛ ቦኋላ No እንደዛ የሚባል ነገር የለም ብለናል።

ሊቀመንበሩ ምንድነው የፈለገው በቃ ቢያንስ በመርህ ደረጃ ውህደት እንደ ሀሳብ እንደተቀበልነው ማረጋገጥ አለብን አለ። ይሄ ስለማንቀበለው ሙሉ በሙሉ በስብሰባው የተሳተፈ ድምፅ በሚሰጥበት ሰዓት የነበረ የህወሓት አመራር ሙሉ በሙሉ ተቃውሞታል። እንጠብቃቹኋለን የናንተ መኖር በጣም ሊያስፈልገን ነው ምናምን ወደ ሚል ግማሽ ልመና ግማሽ ማግባባት ነው የገባው።

ስለዚህ መጀመሪያ ውህደት የሚመለከት ለመወሰን አልገባንም። ውህደት አስመልክቶ የተካሄደ ጥናት ለመወያየት ነው የገባነው። ከሁሉም በላይ ግን የገባንበት ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ለመወያየት ፍላጎት የሌለው ቡድን ዋና ትኩረቱ የሚድያ ጥቃት ላይ የውህደት ሀሳብ ተቀባይነት አግኝቷል የሚል ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚውል ድምፅ የማሰባሰብ ነው።

ውህደቱ በፕሮግራም ላይ መመስረት አለበት። ፕሮግራም ሳይቀርብ ስለ ውህደት መወሰን አይቻልም። በሊቀ መንበሩ በኩልና የሚመራው ቡድን የነበረው ፍላጎት ውህደትን የሚመለከት በprinciple ተቀብለነዋል ካላቹህ ፕሮግራም ቦኋላ አሳያቹኋለሁ እመኑኝ የሚል ንግግር ነው የነበረው። እኛ ደግሞ እናምንሃለን አናምንህም የሚባል ነገር የለም እንደ ህወሓት በፕሮግራም ነው ልንወሃድም ልንቃወምም ልንቀበለውም ከሆነን በፕሮግራም ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት የሚል ሐሳብ ነው ያቀረብነው።

ስለዚህ የመወሃድ ችግር የለንም በፕሮግራም አንድ ከሆንን በአስተሳሰብ አንድ ከሆንን በተግባር አንድ ከሆንን እና መወሃድ ለአገር የሚጠቅም ከሆነ ለትግራይ የሚጠቅም ከሆነ ለኦሮሚያ የሚጠቅም ከሆነ ከመወሃድ ወደ ኋላ የምንልበት ምክንያት የለንም። ድሮውም የነበረ አቋማችን ነው። አሁንም ያለን አቋም ነው።

በአሁኑ ሰዓት የቀረበው እሱ በዚህች ቀን ሊያስወስነው የፈለገው ነገር ስለነበረው በእምነት ደረጃ በመርህ ደረጃ ተቀብለነዋል በሉ በመርህ ደረጃ ተቀብለነዋል የሚባል ውህደት የለም።

ለመወሃድ ፕሮግራም መኖር አለበት። ፕሮግራም ሳይዙ ምንም ሳያደርጉ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል ለሚድያ ፍጆታ ሲባል ብቻ ወደ ድምፅ መስጠት እንግባ ብለዋል። ስለዚህ በወቅቱ ህወሓት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም የሚል አቋም ነው ያቀረብነው።
አገር በአደጋ ላይ ወድቃ እያለች መልስ ለመስጠት ፍላጎት ያለው አመራር በጠፋበት ሰዓት ስለ ውህደት ስለ አካላዊ ውህደት ተቀራርበናል ተቃቅፈናል የሚል ብቻ መናገር ትርጉም የለውም የሚል ግልፅ አቋም ነው የያዝነው።

ድምፅ ከመስጠት ቦኋላም ልመና ነበር። በነጋታው የተካሄደው ስብሰባም ቢሆን ለመቀራረብ እንዲህ ቢደረግ ይሻላል ምናምን የሚል ነው። ፕሮግራም በሌለበት ፕሮግራም ሳትይዝ ምክንያቱም የማጭበርበር ሥራ ነው ተፈልጎ የነበረው።

ስብሰባው ልንመጣ አንችልም ማለት አትችልም አሁን ባለው ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለው ነገር ማየት መቻል አለብን ብለን ነው እንደ ድርጅት ወስነን ነው የገባነው። ከዚህ ውጪ ፍቃዱ ያለው እገሌ ያለው የሚባል ነገር የለም።

የህወሓት አቋም ነው እየነገርኩህ ያለሁት፡ የህወሓት አቋም ነው። የሥራ አስፈፃሚ 36 አባላት በአሰራር ድምፅ ሊሰጡ ከሆነ ተደራጅተው ድምፅ አይሰጡም ሊሰጡ ከሆኑ። በዚህ አጋጣሚ ይሄ ግን ጉዳዩ ፖለቲካዊ ውሳኔ ስለነበረ የድርጅት ህልውና የማረጋገጥ ጉዳይ ስለነበረ በስብሰባው የተሳተፉ የህውሓት አመራሮች ድምፅ በሚሰጥበት ሰዓት የነበርን ሁላችንም ተቃውመነዋል።

እኔ ከኋላ ሁኜ ሳይ ስለነበረ አብይ ሲቆጥር የደገፉ ሰዎች ቁጥር አልቆጠረም። እኔ እነግርሃለሁ ድጋፍ ያልሰጡ ሰዎች አሉ። ድምፅ ያልሰጡ ማለት ነው ከኋላ ስለነበርኩኝ ያየኋቸው ሰዎች አሉ። በኋላ ድፍረት ኖሯቸው ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል አልገለፁም ሌላ ጉዳይ ነው። ስለዚህ እነሱ እንደ ድርጅት ሓሳብ የሚያቀርቡበት ህወሓት በግለሰብ ሓሳብ እንዲያቀርቡ የሚባል ነገርስ ከየት የመጣ ነው።

ኢህአዴግ በወጉ አልፈረሰም። ምክንያቱም ሥራ አስፈፃሚ ግንባር ሊያፈርስ አይችልም ሥራ አስፈፃሚ ሀሳብ ማቅረብ ይችላል። ግንባር ሊፈርስ ከሆነ የግንባሩ አባላት የሆኑ ድርጅቶች ለመፍረስ ከተስማመሙ ብቻ ነው። ውህደት የሚለው ማላገጥ ተወውና ውህደት መጀመሪያ ግንባሩን የመሰረቱ ድርጅቶች ወደ አንድ ሊመጡ ከሆነ ያ አለን የሚሉት ድርጅት በይፋ መፍረስ መቻል አለበት።

ሌላ ነገር ግን ብሀሳብ ደረጃ በአስተሳሰብ ቴክኒካሊ እንደዛ ዓይነት እርስ በራሱ የሚጋጭ እንደዛ ዓይነት የውሸትና በየቀኑ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ብቻ እየፈበረከ የሚውል ኢህአዴግ አለ ብለህ መናገር አትችልም። በኛ እንደ ህወሓት ግን እንደዚህ ዓይነት መንቦጫረቅ ልንገባ እንደማንችል ተናግረናል። በተግባርም አረጋግጠናል። እነሱ በግላቸው እኛ በድርጅት የሚለው የሚባል ንግግር ግን ማላገጫ ነው።

የቀጣይ የህወሓት ዕድል በፍቃዱ አይወሰንም

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top