Connect with us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይል 20ኛ ዓመት እና የደንበኞች ቀንን አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይል 20ኛ ዓመት እና የደንበኞች ቀንን አከበረ

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይል 20ኛ ዓመት እና የደንበኞች ቀንን አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይል የተመሠረተበት 20ኛ ዓመት እና የደንበኞች ቀንን ትላንት ህዳር 2 ቀን 2012 ዓ.ም በስካላይት ሆቴል በድምቀት አከበረ፡፡

 

የኢትዮጽያ አየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በሥነሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንንግግር አየር መንገዱ ከተመሰረተ 73ኛ ዓመቱ ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ከሌላው ዓለም ጋር ለማገኛኘት ሲያከናውን የነበረው ከባድና ውጣውረድ የበዛበት ሥራ በብቃት ሊያልፍ የቻለው በደንበኞች የቅርብ ድጋፍ መሆኑን በማስታወስ አመሰግነዋል፡፡

አየር መንገዱ በቀጣይ 13 ዓመታት አሁን ካስመዘገበው ዕድገት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተወልደ በሰው ሀይል፣ በመሠረተ ልማትና በመሳሳሉት የተደረገውን ዝግጅት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በሥነሥርዓቱ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የአየር መንገዱ ደንበኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በሼባ ማይል የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ደንበኞች ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ሰጥቷል፡፡

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top