Connect with us

‹‹ ምርጫውን ማራዘም መፍትሔ አያመጣም›› ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

‹‹ ምርጫውን ማራዘም መፍትሔ አያመጣም›› ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
Photo: Facebook

ፓለቲካ

‹‹ ምርጫውን ማራዘም መፍትሔ አያመጣም›› ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

የኢህአዴግ ውህደት በስምምነት ላይ መመስረቱ ለአገሪቱና ለህዝቧ ጠቃሚ መሆኑን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ፡፡ ምርጫውን ማራዘምም አገሪቱ ላለችበት ሁኔታ መፍትሔ እንዳልሆነና ለበለጠ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችልም ገለጹ፡፡

ፕሮፌሰር መረራ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የኢህአዴግ እህት ፓርቲዎች አንድ ውሁድ ፓርቲ የመሆን ሃሳባቸው የራሳቸው ቢሆንም እንደ ፖለቲከኛ ግን በስምምነት ቢዋሀዱ ይጠቅማቸዋል፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ሊጥላቸው ይችላል ፡፡

የፓርቲዎቹ ለመዋሃድ አለመስማማት የለውጡን መንገድ እንዳያስትና እንዳያደናቅፍ፣ አገሪቷንም ወዳልተጠበቀ ቀውስ ውስጥ እንዳያስገባ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ፓርቲዎቹ ከራስ በላይ ለአገር ማሰብና ለውጡም እንዳይጨናገፍ የራሳቸውን ሚና መጫወት እንደሚገባቸው አብራርተዋል፡፡

‹‹አሁን ያለው ፌዴራሊዝም ትልቁ ችግር የአንድን ቡድን ወይም ፓርቲ የበላይነትን ለማስፈን ተብሎ ዴሞክራሲ አልባ ሆኖ የቆመ መሆኑ ነው›› ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ ይህ ውህደት የሁሉም ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ሊሆን ስለሚችል በስምምነት ላይ ተመስርቶ መከናወን አለበት፤ ይህ መሆን ካልቻለ ግን አገሪቷን ላልተፈለገ አደጋ ሊዳርጋት ይችላል ብለዋል፡፡

በአገሪቱ የሚነሳው የማንነት ጥያቄ ላለፉት በርካታ ዓመታት የዘለቀ በመሆኑ በስምምነት ላይ የተመሰረተ መልስ ካላገኘንለት በዚህ ወይም በዚያኛው ቡድን ፍላጎት አልፎ ለመሄድ መሞከር ዋጋ ስለሚያስከፍል በጣም መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ‹‹ህዝቦች ለአስተዳዳሪዎቻቸው አንታዘዝም ፤የሚነገረንንም አንሰማም›› እያሉ በመሆኑ ገዢው ፓርቲ በለመደው ሁኔታ መምራት እያቃተው ነው ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ ለዚህ የሚመጥን ፖለቲካዊ መግባባት መፍጠር፣ ከሌሎች ኃይሎች ጋር ተዋህዶ ይህችን አገር የት ድረስ እንወስዳታለን የሚለውን አስፍቶ ማየት እና በዚያው ልክ መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

‹‹እኛ እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ መንግሥትን ልንመክር የምንችለው በስምምነት ላይ የተመሰረተ ውህደት አድርጉ ነው የምንለው ›› ያሉት ፕሮፌሰር መረራ ፣ ውህደቱ በተለይም በቀጣይ የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ነጻና ፍትሀዊ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና እንዳለው ፤ ለዚህ ስኬት ደግሞ ሁሉም በአንድነት መቆምና መተባበር ወቅቱ የሚጠይቀው መፍትሔ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ያለው የፌዴራል ስርዓት መለወጡ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ በሚቀጥሉት አሥርና ሃያ ዓመታት ይህንን ለመለወጥ ከመነሳት ይልቅ ዴሞክራሲ ላይ እንዲመሰረት ማድረጉ የተሻለ አማራጭ መሆኑን ፕሮፌሰር መረራ ተናግረዋል፡፡

ኢህአዴግ ስርዓቱን ዴሞክራሲያዊ ማድረግ ይጠበቅበታል ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲኖር ማስቻል ይጠይቃል፤ ከዚያ ውጭ የሚፈጠሩ ነገሮች በሙሉ አገሪቷን ይበትኑ ይሆናል እንጂ የሚያመጡት ትርፍ ስለማይኖር የኢህአዴግ አመራሮች ይህንን ደጋግመው ማሰብ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በየቦታው ያሉ ቀውሶች መንስኤያቸው አንድ ገዢ ፓርቲ ስልጣንን በበላይነት ይዞ በከፋፍለህ ግዛ ሴራ አገሪቱን ሲመራ በመቆየቱ߹ የአስተዳደርና ፖለቲካዊ ችግሮች ባለመፈታታቸው ፤ በነጻና ፍትሀዊ ምርጫ የመጣ መንግሥት ባለመኖሩ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መረራ ፤ብሔራዊ መግባባት ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ፤ ከዚያ ውጪ ግን ምርጫውን ማራዘም መፍትሔ አያመጣም፤ እንደውም ለበለጠ አደጋ ሊያጋልጥ ይችላል ብለዋል፡፡

በህዝብና በመንግሥት መካከል ለተፈጠረው ሰፊ ክፍተት ምርጫው ራሱ መልስ ሊሆን ይችላል የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ በሀቅ ወደ ምርጫ የምንገባ ከሆነ ህዝቡ በመረጣቸው ተወካዮቹ ወደ መመራት ይሄዳል፡፡ ስለዚህ በእኔ ግምት የሚቻለውን ያህል ጥረት ተደርጎ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ምርጫው መካሄድ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

” በቀጣዩ ዓመት አዲስ መንግሥት ካላገኘን አሁን ያለው ቀውስ የት እንደሚያደርሰን እርግጠኛ አይደለሁም” ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ የሚሻለው አገሪቷ ላይ ብሔራዊ መግባባት እንዲመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

(ምንጭ፡-አዲስ ዘመን ህዳር 3/2012)

Click to comment

More in ፓለቲካ

 • ሥልጠና እየተካሄደ ነው ሥልጠና እየተካሄደ ነው

  ዜና

  ሥልጠና እየተካሄደ ነው

  By

  ሥልጠና እየተካሄደ ነው የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ አስተባባሪ ግብረሀይል የምርጫ ክልል 28 የአስተባባሪዎች...

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤ ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  ነፃ ሃሳብ

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  By

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን...

 • የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል ምላሽ

  ዜና

  የአፋር ክልል ምላሽ

  By

  የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል መንግስት ንጹሀንን እየገደለና እያፈናቀለ ነው ሲል የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ጥፋተኝነትን...

 • የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  ነፃ ሃሳብ

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  By

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ ሰባት ቁጥርና ሕይወት፤ (አፈወርቅ ልሣኑ ~ ድሬቲዩብ) ሰባት ቁጥር...

To Top