Connect with us

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማረጋጋት የሚደረገው ጥረት ቀጥሏል

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማረጋጋት የሚደረገው ጥረት ቀጥሏል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማረጋጋት የሚደረገው ጥረት ቀጥሏል

~ተማሪዎች አንማርም በማለታቸው የትላንቱ ውይይት ተቋርጧል፣

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በትላትናው ዕለትም ቀጥሎ መዋሉ ታውቋል።
ዩኒቨርሲቲው እንዳስታወቀው በትላንትናው ዕለት ተማሪዎቹ ከወልድያ ከተማ አስተዳደር፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፡ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ተወያይተዋል ፡፡ በውይይቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎቹ እንደተናገሩት በተማሪዎቻችን ላይ የደረሰው ጉዳት የሁላችንም ነው ፡፡ ክስተቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ ያሳዘነ ያስቆጣና ሊደገም የማይገባው ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡ በቀጣይ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈፀም ከዩኒቨርስቲውና ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅርበት እንሰራለንም ብለዋል ፡፡

በተማሪዎቹ በኩልም:
* የወልዲያ ከተማ ህዝብ ሰው አክባሪና እንግዳ ተቀባይ መሆኑን ነገርግን ተማሪውን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ ጥቂት ወገኖች መኖራቸው አንስተዋል።

አንዳንድ ተማሪዎች በተመሳሳይ መልኩ ከአሁን በፊት በተፈጠረ ችግር ምን እርምጃ ተወሰደ፣ ችግሩ ነገም ላለመከሰቱ ምን ዋስትና አለን የሚል ጥያቄ ያነሱ ሲሆን አጥፊዎች ተለይተው በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

ትላንት በተካሄደው በዚሁ ውይይት ላይ አንዳንድ ተማሪዎች አንማርም የሚል አቋም በመያዛቸው መግባባት ላይ ሳይደረስ ውይይቱ መጠናቀቁን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተረጋግተው የመማር ማስተማር ሒደቱ እንዲቀጥል አሁንም ጥረቱ የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን ለማወያየት ፕሮግራም መያዙን ገልጷል ፡፡

ትላንት ማምሻውንም የዩኒቨርሲቲው ተ/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስረስ ንጉስ ከዲኖች፣ ዳይሬክተሮች፣ ከትምህርት ክፍል ተጠሪዎችና ከተለያዩ የስራ ክፍል ሀላፊዎች ጋር ተማሪዎቻችን በሚረጋጉበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የዞንና የከተማ አሰተዳደሩ አመራሮችም በበኩላቸው ችግሩን ለማረጋጋትና ለመፍታት ውይይት እያካሄዱ ነው ፡፡

የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ የፀጥታ አካላት ከትላንትና በስቲያ ጀምሮ የግቢውን ፀጥታ ሁኔታ እየመሩት ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው አያይዞም የሐሰት ምስል እና ወሬ በመጠቀም በዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ችግር እንዲፈጠር በማህበራዊ ሚድያ እየሰሩ ያሉ ወገኖች ከእኩይ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top