Connect with us

የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አቶ አባዱላ ገመዳ የተሽከርካሪ እና የገንዘብ ድጋፍ አበረከቱ

የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አቶ አባዱላ ገመዳ የተሽከርካሪ እና የገንዘብ ድጋፍ አበረከቱ
Photo: Facebook

ዜና

የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አቶ አባዱላ ገመዳ የተሽከርካሪ እና የገንዘብ ድጋፍ አበረከቱ

የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አቶ አባዱላ ገመዳ ለኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ማህበር የሁለት ተሽከርካሪ እና የገንዘብ ድጋፍ አበረከቱ።

ኢ/ር ታከለ ኡማ የኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ብሄራዊ ማህበርን ጎብኝተዋል፡፡

ማዕከሉ በወላጆችየተቋቋመ ሲሆን ላለፉት 25 ዓመታት የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ እና እኩል ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል፡፡

በትናንትናው ዕለትም የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አቶ አባዱላ ገመዳ በቅርብ ገበያ ላይ ከዋለው መፅሐፋቸው ሽያጭ ከተገኘ ገቢ ለኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ማህበር የሁለት ተሽከርካሪ እና የገንዘብ ድጋፍ አበርክተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ በጊዜያዊነት ያለበት ቦታ የእእምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው አካላት የመማሪያ እና የስልጠና ማዕከል እንዲሆን ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ይዞታው ለማህበሩ መሠጠቱንም ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

እንደዚህ ያሉ ፈታኝ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ሰፊ ልብ እና ትከሻ ያስፈልጋል ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ የኢትዮጵያ የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው ብሄራዊ ማህበርም ሆነ ሌሎች መሠል ማህበራትን በሚችለው አቅም ሁሉ እንደሚደግፍ መናገራቸውን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top