Connect with us

የዓለም ክብረ ወሰን ተብሎ የተመዘገበዉ ትዳር

ለ80 ዓመታት ያህል በትዳር የቆዩት ጥንዶች የአለም ክብረ ወሰን መዝገብ ተመዘገቡ
Photo: dailymail

አስገራሚ

የዓለም ክብረ ወሰን ተብሎ የተመዘገበዉ ትዳር

ለ80 ዓመታት ያህል በትዳር የቆዩት ጥንዶች የአለም ክብረ ወሰን መዝገብ ተመዘገቡ

መኖሪያቸዉን በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት የሆነዉ ጥንዶች በዓለም ለረዥም ጊዜ የቆዩ ባለትዳሮች በመባል በአለም አቀፉ የጊነስ ሬከርድስ መመዝገባቸዉን ዩ. ፒ. አይ ዘግቧ፡፡

ጆን ሀንደርሰን የ106 አመት እድሜ ያስቆጠሩ ሲሆን ባለቤታቸዉ ወይዘሮ ቻርሎቴ ሀንደርሰን ደግሞ የ105 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ጊነስ የሁለቱን ጥንዶች ዕድሜ በመደመር ለዚህን ያህል አመት የኖሩ ጥንዶች አለመኖራቸዉን መስክሯል፡፡

ጥንዶቹ የተገናኙትና የተጋቡት በቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ከ10 ዓመት በፊት ሎንግ ሆርን ወደተባለ ቦታ መዛወራቸዉን ዘገባዉ አመልክቷል፡፡

ጥንዶቹ በመዋደድና እርስ በርሳቸዉ በመከባበር ያሰለፏቸዉን 80 ዓመታት በመጭዉ ታህሳስ ወር እንደሚኪብሩት ታዉቋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top