Connect with us

የተባበሩት መንግስታት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሊመልስ ነው

የተባበሩት መንግስታት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሊመልስ ነው
Photo : Facebook

ዜና

የተባበሩት መንግስታት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሊመልስ ነው

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) በካኩማ የስድተኞች መጠለያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በፈቃደኝነት እንደሚመልስ አስታወቀ።

የድርጅቱ የኬንያ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ቡርጊ እንጊል ብርክት የካኩማ የስደተኞች መጠለያ ከ 10ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን ስደተኞች እንዳሉ ገልጸው ብዙዎቹ ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥያቄ እያቀረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በምክትል ኃላፊዋ የተመራ የተባበሩት መንግስታት ቡድን በኬንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር መለስ ዓለም ጋር በመሆን የካኩማ ካምፕን ጎብኝተዋል። በቅርቡም የዳዳብ የስደተኞች ካምፕን በጎበኙበት ወቅት ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ከኢትዮጵያውያኑ ተወካዮች ጋር በተደረገ ውይይት በኬንያ የነበራቸው ቆይታ አብቅቶ ለአገራቸውና ለህዝባቸው መብቃት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

በካኩማ ስደተኞች ካምፕ 150ሺህ የሚሆኑ የተለያዩ አገሮች ዜጎች ተጠልለዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top