Connect with us

ኢትዮጵያዊው የሚስቱን፣ የልጁን እና የራሱን ህይወት ቀጠፈ

ኢትዮጵያዊው የሚስቱን፣ የልጁን እና የራሱን ህይወት ቀጠፈ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ኢትዮጵያዊው የሚስቱን፣ የልጁን እና የራሱን ህይወት ቀጠፈ

ኢትዮጵያዊው የሚስቱን፣ የልጁን እና የራሱን ህይወት ቀጠፈ

(ታምሩ ገዳ)

ነዋሪነቱን በምድረ አሜሪካ፣ ኒዮርክ ግዛት ውስጥ፣ ያደረገው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ የተነገረለት ዮናታን ተድላ በጎረቤቶቹ ዘንድ ሰው አክባሪ እና ከሁሉም ጋር ተግባቢ፣ ሳቂታ ሰው ነበር ይሉታል። ይሁንና በትዳሩ ውስጥ በገባው ተቃርኖ ሳቢያ የትዳር አጋሩን፣ የአብራክ ክፋያቸውን እና የራሱን ህይወት ለማጥፋት ተገዷል ሲል ደይሊ ኒውስ የተሰኘው ድህረ ገጽ እስደንጋጩን ዜናን አስነብቧል።

እንደ ብዙዎች እምነት እስከ በትላንትናው እሮብ ድረስ ከባለቤቱ ጄኒፈር ሼቸልቲን እና ከአምስት አመት ጨቅላ ሴት ልጃቸው ፣አባይነሽ ፣ ጋር የዚህን አለም ኑሮን በደስታ እና በሰላም የሚያጣጥሙ ጥንዶች ለመሆናቸው ምስላቸውን እና እለታዊ እንቅስቃሴያቸውን አይቶ ለመፍረድ አይከብድም።

ይሁንና መንስኤው ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት ጄኒፈር ከዮናታን ጋር የነበራትን ግንኙነት በፍርድ ቤት ፍቺ ለመቋጨት መወሰኗን የተረዳው ዮናታን ” ብታርፊ ይሻላል፣ ያንቺንም ሆነ የሁላችንንም ህይወት አመሰቃቅለዋለሁ” የሚል ዛቻ እንዳስፈራራት ባለፈው እሁድ ለመጨረሻ ጊዜ እያለቀሰች በስልክ መናገሯን የሰባ ስድስት አመቱ የጄኒፈር አባት ያውሳሉ። ሌሎች መረጃዎች እንዲሁ እኤአ 2016 በሁለቱ ጥንዶች መካከል ተከስቶ በነበረ አለመግባባት የተነሳ ዮናታን ከጄኒፈር እና ከልጁ እርቅ እንዲል በፍ/ቤት ታግዶ ነበር። ይሁንና ጄኒፈር ነገሩን ከረር ባለማድረጓ የህግ አስገዳጅነት አልጸናም ነበር። ቢጸናም ሴት ልጅ እራሷን ለመከላከል የጦር መሳሪያ በማትታጠቅበት በኒዬርክ ግዛት እና ለመሞት የቆረጠ ሰውን የህግ ጋጋታ እስከምን ድረስ ይከለክላል ሲሉ የዘገቡም አልጠፉም።

እሮብ ምሽት ላይ የሰላ ቢለዋ በባለቤቱ እና በህጻን ልጁ አንገታቸው ላይ በማሳረፍ ፣በመግደል በመጨረሻም እራሱን ሰቅሎ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የተገኘው ዮናታን እና ጄኒፈር የመጀመሪያ ትውውቃቸው በታዋቂው የኮሎምቢያ ዪኒቨርስቲ ውስጥ እርሱ የመረጃ ቴክኖሎጂ (IT)ሰራተኛ ሆኖ ሳለ እርሷ ደግሞ በማህበራዊ የጤና አያያዝ ማስትሬት ዲግሪዋን በማጥናት ላይ በነበረችበት የዛሬ አስር አመት አካባቢ ነበር።

አሳዛኙ እና አስደንጋጩ ክስተትን ማመን ያቃታቸው የዮናታን ጎረቤቶቸ መካከል የአርባ አመቷ ፖትሪሺያ ለዜና ሰዎች እንደገለጸችው “ዮናታንን እስከማወቀው ድረስ ልጁን ተሸክሞ ወደ ት/ቤት የሚያደርስ ፣ የቤተሰብ ፍቅር ያለው፣ከሁሉም ጎረቤት ጋር ተግባቢ ሰው ነበር ። ለምን ይህንን መሰል እርምጃ እንደወሰደ ለእኔ ግልጽ አይደለም።” ብላለች

ሌላኛ ጎረቤት እንዲሁ “በጭራሽ የማይታመን ነገር ነው የምሰማው ዮናታን እና ጄኒፈር ማለት እጅግ የሚዋደዱ እና የፍቅር ተምሳሌቶች ፣አንድም ቀን ተጣልተው የማያውቁ ጥንዶች ነበሩ። ዮናታን ያቺ እንደ አይኑ ብሌን የሚሳሳላት ጨቅላ ልጁ ህይወትን እንዴት ሊቀጥፍ ቻለ?” ሲሉ ጠይቀዋል፣ ዘክረዋቸዋል ።

በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ አገልግሎት መስጪያ ውስጥ በመስራት ላይ ስለ ነበረችው ጄኒፈር በተመለከተ የስራ ባልደረቦቿ ባወጡት የሀዘን መግለጫ” የ ቤተሰብ እቅድ እና አስቸኳይ እርዳታ አሰጣጥ በተለይ ለህጻናት እና ለሴቶች እንክብካቤ ዋንኛ ተዋኒት፣ስለ ጨቅላ ልጇ እለታዊ ክንዋኔ ተናግራ የማታቆም ፣ በብዙዎች ዘንድ የምትወደድ ባልደረባችን እና ጓደኛችን ነበረች። ሲሉ በተፈጠረው ሁናቴ በጣም መደናገጣቸውን ገልጸዋል።

እንደ ጄኒፈር ቤተሰቦች እምነት የአርባ ስድስት አመቱ ዮናታን እና የትዳር ጓደኛው የአርባ ሁለት አመቷ ጄኒፈር መቃቃር የጀመሩት የዛሬ አምስት አመት ልጃቸውን አባይነሽን ከወለዱ በኋላ ብዙም ፍቅር አይታይባቸውም ነበር ይላሉ።

በኒውዮርክ ግዛት ውስጥ እኤአ ከ2010 እስከ 2016 ባሉት ጊዜያት ውስጥ 560 ሰዎች ህይወታቸውን በወንጀለኞች ያጡ ሲሆን ግማሽ ያህል በትዳር ጓደኞቻቸው መካከል በተፈጠረ ጸብ የተነሳ መገደላቸውን እና ሀምሳ ያህሉም ሴቶች መሆናቸውን የፖሊስ መረጃዎች ይገልጻሉ።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top