Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ እዝ አዣዥ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ እዝ አዣዥ ጋር ተወያዩ
Photo: Facebook

ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ እዝ አዣዥ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ እዝ አዣዥ ከሆኑት ከጀነራል ስቴፈን ታውንሴንድ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

ጀነራሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርቡ ባገኙት የኖቤል ሰላም ሽልማት ደስታቸውን ገልጸው፣ ይህ ለኢትዮጵያም ሆነ ለቀጣናው አበረታች ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ቀጥሎም በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በተለይም ከወታደራዊ የጦር ኃይል አንጻር የነበረውን የረዥም ጊዜ የትብብር ግንኙነት በማስታወስ፣ የሀገሪቱን ጦር ሠራዊት አቅም ለመገንባት የአጭር እና የረዥም ጊዜ ትብብርን በማጠናከር ላይ ተወያይተዋል፡፡

በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ እየተከናወነ የሚገኘውን የተሓድሶ ሥራ ከማስቀጠል አንጻር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሠራዊቱን ብቃት ያለው ባለሙያ ማድረግ እና ለየትኛውም አካል እና የፖለቲካ ተቋም ምንም ዓይነት አድልዎ ሳያሳይ ወገናዊነቱን ለዲሞክራሲ ብቻ ያደረገ እንዲሆን ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top