Connect with us

በስልጤ ዞን የእሳት ቃጠሎ ንብረት አወደመ

በስልጤ ዞን የእሳት ቃጠሎ ንብረት አወደመ
Photo: Facebook

ዜና

በስልጤ ዞን የእሳት ቃጠሎ ንብረት አወደመ

በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ ትናንት ረፋድ ላይ የተከሰተዉ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

የወረዳው ዋና አስተዳደሪ አቶ ከድር መሀመድ ለኢዜአ እንደገለፁት ትናንት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ በወረዳዉ ዋና ከተማ 01 ቀበሌ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ለጊዜው መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀው በዚህ የእሳት ቃጠሎ 11 ሱቆችና የተለያዩ ድርጅቶች ያሉበት ሕንጻ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በስፍራው የሚገኘው የወረዳ የነዳጅ ማከፋፈያ የንግድ ተቋምና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ጉዳቱ ከፍ እንዲል እንዳደረጉት ገልጸው ቃጠሎው በቁጥጥር ስር እንዲውል ህብረተሰቡና የጸጥታ አካላት ያደረጉት ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

በቃጠሎው ንብረታቸውን ያጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማቋቋም ከዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጋር በመነጋገር የተለያየ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን አቶ ከድር ገልጸው በቃጠሎው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም አስረድተዋል።

ምንጭ:- ኢዜአ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top