Connect with us

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላትን አነጋገሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላትን አነጋገሩ

ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላትን አነጋገሩ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ ቡድን አባላትን ትናንት ጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የፓርላማ አባላቱ ከህብረቱ 5 የተለያዩ የፖለቲካ ከሚቴዎች ውስጥ የተውጣጡና ከ17 በለይ አባላትን ያካተተ ሲሆን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ሀሉን አቀፍ ለውጥ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን ስትራቴጅያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

አቶ ገዱ በዚህ ወቅት እንደገለጹት የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ያልተቋረጠ የልማት እና የሰብአዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት በአገራችን የሚያደርጉት ተከታታይ ጉብኝት ህብረቱ ከኢትዮጰያ ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኘነት ያሳያል ብለዋል  አቶ ገዱ በንግግራቸው።

የአውሮፓ ህብረት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የአባል አገራቱ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በስፋት ኢንቨስት እንዲያደርጉም  ሚኒስትር ጥሪ አቅርበዋል። ሚኒስትር አቶ ገዱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ በተመለከተም ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

በአገራችን አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሸያ ላይ የተሰሩ ስራዎችን፣ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፈት በአገሪቱ የዲሞክራሰ ስርዓትን ለመገንበት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በስፋት አብራርተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በመላው አፍሪካ ሰላም እንዲሰፍን እያደረገች ያለውን አጠቃለይ እንቅስቃሴ በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል። አገራችን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ለማሳካት በሰላም ፣ በልማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ለምታደርገው እንቅስቃሴ የአውሮፓ ህብረት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አቶ ገዱ ጠይቀዋል።

የአውሮፓ ሀብረት የፓርላማ አባልና የልኡካን በድን መሪ የተከበሩ ሚ/ር ቶማስ ቶቤ በበኩላቸው የፓርላማ አባለቱ ስራ ከጀመሩ ወዲህ የመጀመሪያ የአፍሪካ ጉብኝታቸው መሆኑን በማስታወስ፣ ኢትዮጵያ በቀጠናው በተለይም ከኤርትራ ጋር ሰላም እንዲሰፈን የወሰደችውን ተነሳሽነትና የተገኘውን ውጤት አድንቀዋል። በዚህም የኢፈዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል ሰላም አሸናፊ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው የኢኮኖሚ እድገትና አገሪቱ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ዲሞክራሲን ለመገንባት እያደረገች ያለውን ጥረት፣ በኢትየጵያ የሚገኙ ስደተኞች የተሻለ ኑሮ እንዲመሩ እንዲሁም በቀጠናው ዘላቀ ሰላም እንዲሰፍን እያደረገች ያለውን አንቅስቃሴ ሚ/ር ቶማስ አድንቀዋል። በኢትዮጵያ የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ለውጥ ግቡን እንዲመታ የአውሮፓ ህብረት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚ/ር ቶማስ ገልጸዋል።

በመጨረሻም አቶ ገዱ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን ስትራቴጅያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከፓርላማ አባላቱ ለተነሱ ተጨማሪ ጥያቄዎች ማብራሪያና ገለጻ አድርገዋል ሲል መረጃውን ያደረሰን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ነው።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top