Connect with us

71 ፓርቲዎች በአራት ኪሎ አደባባይ የረሃብ አድማ ያደርጋሉ

71 ፓርቲዎች በአራት ኪሎ አደባባይ የረሃብ አድማ ያደርጋሉ
Ethiopian Reporter

ፓለቲካ

71 ፓርቲዎች በአራት ኪሎ አደባባይ የረሃብ አድማ ያደርጋሉ

ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሃኪሞች እንዲመድብ ተጠይቋል

አዲስ የወጣውን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅን የሚቃወሙ 71 የፖለቲካ ድርጅቶች በጥቅምት መጨረሻ በአራት ኪሎ የድል ሃውልት አደባባይ ላይ ተሰባስበው ለሁለት ቀናት የረሃብ አድማ ለማድረግ መዘጋጀታቸው አስታወቁ፡፡

አዋጅን በመቃወም በተደጋጋሚ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለምርጫ ቦርድ፣ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ደብዳቤ ቢጽፉም እስካሁን ምላሽ አለማግኘታቸውን የገለፁት 71ዱ የፖለቲካ ድርጅቶች በቀጣይ በአዋጁ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ ተከታታይ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ መሰወናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ካወጧቸው እቅዶች መካከል የረሃብ አድማ ዋነኛው ሲሆን ይህን አድማ ጥቅምት 5 እና 6 ለማድረግ አቅደው የነበረውን ወደ ጥቅምት 25 እና 26 ማሸጋገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

የረሃብ አድማውን ወደ ጥቅምት መጨረሻ ለማሸጋገር የወሰኑትም በጥቅምት መጀመሪያ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተፈጠሩ አለመረጋጋትና ሁከት ምክንያት በየክልሉ ያሉ የክልል ፓርቲዎች በተያዘለት ቀን ወደ አዲስ አበባ ለመግባት መንገዶች ዝግ በመሆናቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አድማውን ከቤት ውስጥ ይልቅ በአደባባይ በማድረግ በፓርቲዎቹ መወሰኑ ይሄን ውሣኔ አዲስ አበባ አስተዳደር ማሳወቅ ማስፈለጉም የረሃብ አድማውን ለማራዘም ምክንያት ከሆኑት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በተጨማሪም በረሃብ አድማው ወቅት ተሳታፊዎች ላይ ሊፈጠር የሚችል የጤና ችግርና ድንገተኛ አደጋዎችን ታሳቢ ያደረጉ ሰፊ ዝግጅቶች ማድረግ በማስፈለጉ ፓርቲዎቹ አድማውን ወደ ጥቅምት 25 ለማዘዋወር መወሰናቸውን አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚ/ር ጥቅምት 25 እና 26 ቀን 2012 ዓ.ም በአራት ኪሎ በሚካሄደው የረሃብ አድማ ላይ የጤና ባለሙያዎች በመመደብ ተገቢውን ሀገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርና በጐ ፍቃደኛ የጤና ድጋፍ አድራጊዎች ባለሙያዎች በመመደብ ህዝባዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በእለቱ ፓርቲዎቹ በመፈክርም ሆነ በድምጽ የሚያቀርቡት ተቃውሞ አለመኖሩን፣ መንገድ መዝጋት፣ ጩኸት ማሰማት የመሳሰሉትን እንደማይፈጽሙ ያስታወቁ ሲሆን የመንግስት አካላት ችግሩን ለመርዳት ከመጡ በጽሑፍ ጥያቄዎችን በዝርዝር እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

የረሃብ አድማውም ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓትና በማግስቱም በተመሳሳይ ሰዓት አድማው የሚካሄድ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ የረሃብ አድማ ፓርቲዎቹ ቀና ምላሽ ካላገኙ ምላሽ እስኪያገኙ በቀጣይ የተቃውሞ የድጋፍ ፊርማ ማሠባሰብን ጨምሮ የተለያዩ ሠላማዊ ሰልፎችን በማዘጋጀት ተቃውሞአቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡ በቀጣዩ ምርጫ የመሳተፍ አለመሳተፍ ጉዳይም የየፓርቲዎቹ የተናጠል ውሣኔን የሚጠይቅ መሆኑንም ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል::

ምንጭ:- አዲስ አድማስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤ ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  ነፃ ሃሳብ

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  By

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን...

 • የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል ምላሽ

  ዜና

  የአፋር ክልል ምላሽ

  By

  የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል መንግስት ንጹሀንን እየገደለና እያፈናቀለ ነው ሲል የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ጥፋተኝነትን...

 • የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  ነፃ ሃሳብ

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  By

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ ሰባት ቁጥርና ሕይወት፤ (አፈወርቅ ልሣኑ ~ ድሬቲዩብ) ሰባት ቁጥር...

 • ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release) ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release)

  ነፃ ሃሳብ

  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release)

  By

  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release) “መንግስት የህግ...

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top