Connect with us

አቶ ዮሐንስ ቧ ያለው ከዕይታ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ፍሬ ሀሳቦች

አቶ ዮሐንስ ቧ ያለው ከዕይታ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ፍሬ ሀሳቦች
Walta TV

ፓለቲካ

አቶ ዮሐንስ ቧ ያለው ከዕይታ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ፍሬ ሀሳቦች

አቶ ዮሐንስ ቧ ያለው የአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበርና የማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ ከድርጅቱ ልሳን ከዕይታ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ፍሬ ሀሳቦች

ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በተመለከተ

በ12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የተላለፈው ውሳኔ «የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ፍትሐዊነት ይረጋገጥ» የሚል ነው፡፡ በተለይም የመሠረተ ልማትና የፌዴራል መንግሥት በሚበጅተው በጀት ላይ ክልላችን ተጠቃሚ አይደለም የሚል ጥይቄ ነበር። ይህን ጥያቄ በጥናት እንዲረጋገጥ አስደርገናል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያወጣውን ሪፖርት አይታችሁ ከሆነ እስከ አሁን ድረስ ሲደረግ የነበረው የመሠረተ ልማት ስር ጭትና አንዳንድ የኢኮኖሚ ግንባታዎች የአማራን ክልል ጨምሮ አንዳንድ ክልሎችን ያገለለ ወይም በበቂ ሁኔታ እንደሌላው አካባቢ እንዳይለማ ለማድረግ ሻጥር ሲፈፀም እንደነበር ያረጋግጣል፡፡ ይህ በመረጃ ተደግፎ የወጣ ጥናት ነው፡፡ ይህ ትልቅ ሥራ ነው፡፡

ሕገመንግሥትን ስለማሻሻል

ህገ መንግስትን ለማሻሻል መጀመሪያ ሠላምና ዴሞክራሲ መስፈን አለበት፡፡ ህዝብ በሰከነ መንገድ መወያየት አለበት፡፡ እኛ ደግሞ የትኞቹ ናቸው የሚሻሻሉት? የትኞቹስ ናቸው የማይሻሻሉት? ብለን መለየት አለብን፡፡ የእኛን ፍላጎትና በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት መለየትና ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ዙሪያ እየሠራን ያለነው ሥራ አለ፡፡

የማንነትና የወስን ጥያቄዎች በተመለከተ

እስካሁን በግልፅ ይህ ጥያቄ አይነሳ የሚል ተቃውሞ ያለው አንድ ክልል ብቻ ነው፡፡ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች፣ ፓርቲዎችና የመንግሥት አመራሮች ሁሉ ጥያቄው መነሳቱ ተገቢ ነው፣ አፈታቱም እኛ አንደምንለው ህጋዊና ሰላማዊ መሆን አለበት የሚል አመለካከት ነው ያላቸው፡፡ ለምሳሌ የትግራይ ክልል መንግሥትና ድርጅቱ ሕውሓት (ትህነግ) የወሰንና የማንነት ጥያቄው መነሳት የለበትም የሚል ፉከራ አዘል መግለጫ እንደሰጡ እናውቃለን፡፡ ከዚያ ውጭ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም የትግራይ ህዝብም ቢሆን ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መልኩ እንዲፈታ እንጂ የወሰንና የማንነት ጉዳይ የማይደፈር ነው ብሎ ያስባል ብለን አናምንም፡፡ ስለዚህ ከተጠቀሰው ክልል መንግሥትና ድርጅት ውጭ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለን እናስባለን፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top