Connect with us

Ethiopia

ከጎንደር ህብርት- ኩሽ ህብረት | ሬሞንድ ኃይሉ

Published

on

ከጎንደር ህብርት- ኩሽ ህብረት | ሬሞንድ ኃይሉ

ከጎንደር ህብርት- ኩሽ ህብረት | በሬሞንድ ኃይሉ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጎበዝ አለቆች መናጥ ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡ ትናንት እራሳቸውን ቅበተው የህዝብ ተወካይ ያደረጉ ወገኖች ዛሬ ማኅበር እየመሰረቱ የራሳቸውን የፖለቲካ አንጃ ወደ ማደራጀት ተሸጋግረዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች ነገ ትናንሽ የራሳቸውን መንግስታት ላለመመስረታቸውም ዋስትና ያለ አይመስልም፡፡ የሁላችን ጥላ የምንላት ሀገር ኢትዮጵያ በብሄር ቅርጫ ከመበጣጠስ አልፋ ዛሬ ከዛም ባነሱ ቡድኖች እየተጎሳቆለች ነው፡፡

በያከባቢው ያሉ ወጣቶች የፖለቲካ አድራጊ ፈጣሪ ሆነዋል፡፡ በቢሊዮን የሚቆጠር ግብርን ትሰበስብ የነበረቸው ሀዋሳ ዛሬ ሚሊዮን ብር ማግኘት ዳገት ሆኖባታል፡፡ ጅግጅጋ ዓላማቸው ግልፅ ያልሆኑ ቡድኖች እኛ ያልነው ከልተፈፀመ በሚል ያሻቸውን ማድረግ ልማድ አድርገዋል፡፡ አማራ ክልል በየጎጡ የተመሰረቱ ቡድኖች ከመንግስት ሹማምንቱ በላይ የሚፈሩ ሆነዋል፡፡ መደራጀት አስፈላጊ ነው በሚል የተጀመረው እንቅስቃሰሴ በጊዜ ሂደት ከብሄር ወርዶ መንደር ደርሷል፡፡ ፀቡም ብሄር ከብሄር መሆኑ ቀርቶ በጎጥ ሆኗል፡፡

ስለአንድ ጠንካራ ብሄር ምስረታ ጉዞ ጀመርናል ያሉን ወገኖች አፍታም ሳይወስዱ እርስ በእርሳቸው አተካራ ገጥመዋል፡፡ ወሎ ህበረት፣ ጎንደር ህበረት፣ ጎጃም ህበረት፣ ሽዋ ህበርት ለየቅል ጉዞ ጀምረዋል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መገባዳጃ ደግሞ ሌላ አዲስ ህበረት የራሱን ግዛት መስርቷል፡፡ 26 ከኩሽ ነገድ የሚመዘዙ ብሄር ተወካዮችን ያያዘው የኩሽ ህብረት ቅዳሜና ዕሁድን ጅግጅጋ ላይ ሲመክር ሰንብቷል፡፡ ይህ ህብረት ከውይይቱ በኋላ ባሳለፈው ውሳኔም ኩሽ የሚለው ስም ገናና እንዲሆን በየአከባቢው ያሉ አገልግሎት መሰጫ ተቋማት፣ ፋብሪካዎችና የንግድ ተቋማት ስያሜያቸውን ወደዚህ ቢያዞሩ መልካም ነው ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ መደራጀት ህገ-መንገስታዊ መብት ነው፡፡ ስለዚህ ከላይ የጠቀስናቸው በየአከባቢው የነገሱ ወገኖች ለምን ተደራጁ የሚል ቅሬታ የለኝም፡፡ ጥያቄው ማኅበር የሆኑበት አግባብ ላይ ነው፡፡ እነዚህ በየቦታው የሚፈለፈሉ ህበረቶች ህጋዊ ዕውቅና አላቸው ወይ? የመንግስት አካላትስ ይሁንታ ሰጠዋቸዋል ወይ? ከሰጡስ በምን አግባብ ነው?

በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የማኅበራት ምሰረታን ዕውቅና የሚሰጠው የፌደራል በጎ አድራጎት ማኅበራት ኤጀንሲ ነው፡፡ ይህ ማኅበር በመላው ሀገሪቱ ያሉ ማኅበራትን እንቅስቃሴ ይከታተላል፡፡ ማኅበራቱም ሪፖርት ያቀርቡለታል፡፡ እንዲህ ከሆነ ወሎ ህብረት ፣ ሽዋ ህብረት፣ የኩሽ ህብርት የሚባሉ ማኅበራት በዚህ ተቋም ይታወቃሉ ወይ?

በአሁኑ ወቅት በየአከባቢው የተመሰረቱ ማኅበራት ዓላማቸው ፖለቲካዊ መሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ ከሀገሪቱ የማኅበራት ማደራጃ ህግ ጋር የሚጣረስ ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት እነዚህን ማኅበራት ተጣያቂነት ወዳለው ስርዓት ሊያሸጋግር ይገባል፡፡

ማኅበራቱም እራሳቸውንና ዓላማቸውን ግልፅ አድረገው ቆምንለት ለሚሉት ማኅበረሰቡ አግልግሎታቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ፍላጎታቸው ለሚታገሉለት ህዝብ ፖለቲካው ችግር መታገል ከሆነም በምርጫ ቦርድ መመዝገብ አለባቸው፡፡ ያ ካልሆነ ግን በጊዜ ሂደት ሀገራዊ ቀውስን መፍጠራቸው የሚቀር አይመስልም፡፡ ለበጎ አድርጎት ዓለማ የተመሰረቱት ተቋማትም ለእኩይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ህብረትን ስያሜያቸው ላይ አንግበው ሀገርን ያፈርሳሉ፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ

** ኢትዮ ጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close