Connect with us

Ethiopia

‹በኦህዴድ የተገባልኝ ቃል አልተፈፀመም› – ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

Published

on

‹በኦህዴድ የተገባልኝ ቃል አልተፈፀመም› - ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

መቼም የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት በመሆን ከ1988 እስከ 1993 ድረስ ያገለገሉት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከቤተ መንግስት ከወጡ በኋላ ስለ ደረሰባቸው ግፍ ታውቃለህ አይደል?፤ ልክ ነህ፤ ‹በህገ ወጥ መንገድ› ፀድቋል በሚሉት የቀድሞ ፕሬዚዳንቶችን ጥቅማ ጥቅም በሚደነግገው አዋጅ አማካይነት ‹መብቴ ተጥሷል› በማለት በየፍርድ ቤቱ ሲንከራተቱ ቆይተዋል፡፡

መቼም የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት በመሆን ከ1988 እስከ 1993 ድረስ ያገለገሉት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከቤተ መንግስት ከወጡ በኋላ ስለ ደረሰባቸው ግፍ ታውቃለህ አይደል?፤ ልክ ነህ፤ ‹በህገ ወጥ መንገድ› ፀድቋል በሚሉት የቀድሞ ፕሬዚዳንቶችን ጥቅማ ጥቅም በሚደነግገው አዋጅ አማካይነት ‹መብቴ ተጥሷል› በማለት በየፍርድ ቤቱ ሲንከራተቱ ቆይተዋል፡፡

እናስ? የዛሬ ዓመት በቁም ነገር መፅሔት ላይ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ታስታውሰዋልህ? ምን አሉ? ብሶታቸውን እንዲህ ነበር የገለፁት፤‹ አሁን ካለሁበት ቤት ውጣ ተብዬ ሁለቴ ተፅፏል፡፡ ለቤት ውስጥ እና ለኑሮ የማወጣውን ገንዘብ ተከልክያለሁ፡፡

የምኖረው በ1ሺህ 700 ብር የፓርላማ ደመወዝ ነው፡፡ መኪናም ተቀምቻለሁ፡፡ ይህን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቢያውቁት ጥሩ ነው፡፡ የቤት ሠራተኛ ባለቤቴ ናት የቀጠረችው፡፡ ጥበቃም በትንሽ ገንዘብ ቀጥሬ ነው። ለህክምና የባለቤቴ ጓደኞች መደሃኒት ገዝተው ባይልኩልኝ ከባድ ነበር የሚሆንብኝ፡፡ ጠዋት እና ማታ አምስት ኪኒን ነው የምወስደው፡፡ የደም ስሮቼ ይዘጋጋሉ፡፡

ለህክምና እና ምርምራ ከሄድኩኝ ሁለት ዓመት ሞልቶኛል፡፡ የስኳር እና የልብ በሽታ አለብኝ፡፡ ለመመርመር እና ውድ መደሃኒቶች ለመግዛት ገንዘብ የለኝም፡፡ ባለፈው ሳምንት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ፕሬዚዳንቱ ጋር በታክሲ ነው የሄድኩት፡፡ የአገሪቱ አቅም በሚፈቅደው መጠን ክብር እና ጥቅም ይገባኝ ነበር። ይህ ለእኔ ተከልክሏል፡፡ ጥሩ ባለቤት እና የሰው ፍቅር ስላለኝ ደስ ይለኛል፡፡ ግን ይህ አገር እና መንግስት የሚገባኝን ጥቅምና ክብር አልሰጠኝም፡፡ ለወደፊትም ይህን ታሪክ ይፈርደዋል፡፡›

ይህ ይፋ ከወጣ በኋላ አቤቱታቸው ምላሽ ያገኘ መስሎ ነበር፤ ነበር ስትል? ላለፉት 13 ዓመታት ለጥያቄያቸው ምላሽ የሚሰጥ በጠፋበት በዚህ ወቅት ባለፈው ዓመት የካቲት ሲካሄድ የሰነበተው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ሀገር ሲመሩ ለቆዩትና አሁን በችግር ላይ ለሚገኙት ፕሬዚዳንት ድርጅቱ የአንድ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉ ተሰምቶ ነበር፡፡ ይህ ድጋፍ ደግሞ ዘመናዊ መኪና፤ ነፃ የውጭ ሀገር የህክምና ወጪን መሸፈን ይጨምራል ተብሎ ነበር፡፡

እናስ? እናማ ሰሞኑን ታትሞ ለንባብ የበቃው የአዲስ አበባ መስተዳድር ልሳን የሆነው አዲስ ልሳን ጋዜጣ ያ በኦህዴድ የተባለው ቃል እንዳልተፈፀመ በምሬት ዶ/ር ነጋሶ አንስተዋል፡፡

አዲስ ልሳን፤- በርዕሰ ብሔርነት ላገለገሉበት አሁን እየተደረገልዎት ያለው ነገር በቂ ነው ብለው ያምናሉ ?

ዶ/ር ነጋሶ፡- አላስብም፤ ኦዲፒ ያደረገው ነገር እንዳለ ሆኖ ስለተግባራዊነቱ ግን ማንሳቱ ዋጋ ስለሌለው ብንተወው ጥሩ ነው፤ መኪናውም ቢሆን የኦሮሚያ ምክር ቤት ፅሕፈት ቤት ትርፍ ስላለ ለጊዜው በዚህ ተጠቀም ሌላ ይገዛልሃል ተብሎ ነበር፡፡ነገር ግን እስካሁን አልተገዛም፤ አሁንም በውሰት መኪና ነው እየተገለገልኩ ያለሁት፡፡ ያው በጤንነቴም ጉዳይ ቢሆን በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገር የማደርገው ህክምናም በራሴ ወጪ እንጂ በተገባልኝ መሠረት አይደለም እየተሸፈነልኝ ያለው፡፡
አዲስ ልሳን፤- በአብዛኛዎቻችን ዘንድ ደመወዝ፤ የመንቀሳቀሻ ገንዘብና መኪና እንዲሁም የህክምና ወጪዎ እየተሸፈነልዎ እንደሆነ ነው የምንረዳው፤ ይህ ካሆነ ለምን ዝምታን መረጡ ታዲያ?

ዶ/ር ነጋሶ፡- አይደለም፤ እኔ ሰው ማሳጣት አልወድም፤

(ምንጭ:- ቁምነገር መጵሔት/ሚድያ)

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close