Connect with us

Ethiopia

ኢህአዴግ ኑሮህን ልንገርኽ አለኝ!

Published

on

ኢህአዴግ ኑሮህን ልንገርኽ አለኝ ! | በሬሞንድ ኃይሉ

ኢህአዴግ ኑሮህን ልንገርኽ አለኝ ! | በሬሞንድ ኃይሉ

ገዥው ፓርቲ ሁሌም መግለጫ ሲያወጣ ፈገግ ያሰኘኛል፡፡ እኔ የምኖረውን ሕይወት እሱ ሊነግረኝ የሞከረ ይመስለኛል፡፡ ኢህአዴግ በዓመት ሁለት ጊዜ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን ይሰበሰብባል፡፡ ከዛም የአቋም መግለጫ ያወጣል፡፡ በዚህ አሃዝ መሰረት ባለፉት 29 ዓመታት ድርጅቱ 58 መግለጫዎችን ለህዝብ ይፋ አድርጓል፡፡ እነዚህን መግለጫዎች አንድ ብርቱ ሰው ከድርጅቱ መዝገብ ላይ አሰባስቦ ቢመለከታቸው ትልቁ ልዩነታቸው የዘመን መለያየት ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከዛ ውጭ ጭብጣቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ተስፋ!

ግንባሩ በ1983 ሀገር መምራት ሲጀምር ያወጣው መግለጫ የዴሞክራሲ ምህዳርን ማስፋት ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ መሆኑን ነበር ፡፡ 2011 ዓ.ም ላይ ስለ ምህዳር መስፋት ያስተምረናል ፡፡ ከሦስት አስርታት በፊት የሠላምና የልማት ጉዳይ ቅድሚያ እንደሚሰጠው ይተርክ ነበር ፡፡ አሁንም ይኼው ሠላምና ልማት እንደ መና ሊወርድ ነው የሚል ስብከት እየሰማን ነው ፡፡ የትናንቱ ኢህአዴግ ድብቅ ስለነበር ብዙ ነገሮችን ምስጢር አድርጎ ባሻው መንገድ ሲነዳን ኑሯል ፡፡ ዛሬ ግን ምንም የሚደበቅ ምስጢር የለንም የሚሉን ሰዎች እየመሩን ስለሆነ የቀጥታ ስርጭቱ ባይሳካ እንኳን ድርጅቱ በግልፅ የተወያየባቸውን ነገሮች ቢነግርን ደስ ይለናል፡፡

የገዥው ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መቼም መግለጫው ላይ እንዳለው የሚያማልል እንዳልሆነ ለመገመት አያዳግትም ፡፡ ይህ ሀሳብ ማስረጃ የሚሻ ትልቅ ነገር አይደለም ፡፡ ብሄራዊ ድርጅቶቹ ወደ ኢህአዴግ ስብሰባ ከመግባታቸው በፊት ያወጧቸው መግለጫዎች በማዕከላዊ ኮሚቴው ውይይት ላይ የሚያራምዱትን አቋም የሚያንፀባርቁ ናቸው ፡፡ እንዲህ ከሆነ ህወሓት ለውጡ ከሽፏል የሚል ሀሳብ ማራመዷን ለማወቅ በማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባ ላይ መገኘት አይጠየቅም ፡፡

ኦዲፒ የኮየ ፈጬ ኮንደሚኒየም ግንባታ ኦሮሚያ መሬት ላይ የተካሄደ በመሆኑ በዕጣ መተላለፍ የለበትም የሚል አቋም እንዳለው እራሱ ካረጋገጠልን መንፈቅ አልሞላውም ፡፡ደኢህዴን በፌደራሊዝሙና በህገ-መንግስቱ ላይ የሚቃጣን ሙከራ እንደማይቀበለው ከነገረን ወራት አላለፉም ፡፡ ትናንት የወጣው የድርጅቱ መግለጫ ግን በፓርቲዎች መካከል ያለው ልዩነት ይፈታ፣ አይፈታ የሚለን ነገር የለም ፡፡ በእህት ድርጅቶቹ መካካል ያለው የአቋም ልዩነት መታረቅ አለመታረቁንም አልነገረንም ፡፡

ኢህአዴግ እንደ ገዥ ፓርቲነቱ በየትኛወም ዘመን ቢሆን ያሉበትን ችግሮች ለህዝብ ይፋ አድርጎ መፍትሄውን አብሮ ከመፈለግ ይልቅ ሚስጢር ማድረግ ይወዳል ፡፡በዚህ የተነሳም መግለጫዎቹ ሁሉ ያው አሰልች ናቸው ፡፡ ስልጣነ መንበሩን ከተቆናጠጠ ጀምሮ የውጡ መግለጫዎችን በውሉ ብናጤናቸው ሠላም ልማት ዴሞክራሲ ከዛም ችገሮቹን ወደ ውጭ መግፋት የተጠናወታቸው ናቸው ፡፡ ለምሳሌ ኢህአዴግ ከተሰነጣጠቀ በኋላ ባወጣው መግለጫ ደጋግሞ “ጥገኛው መድብ” የሚል ቃልን በመጠቀም ተቀናቃኞቹን ልብሳቸው እንዳይከተላቸው አድርጎ ይሰድብ ነበር ፡፡

በምርጫ ዘጠና ሰባት ሰሞን በፓርቲው ላይ የሚቀርቡ ትችቶችንም “የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች አስተያየት” በሚል ሲያጣጥላቸው ኑሯል ፡፡ ገዥው ፓርቲ አሁንም ትችቶችን የሚሸከምበት ትክሻው እንደዛለ ነው ፡፡ ከሁለት ቀናት ስብሰባው በኋላ ባወጣው መግለጫ ላይ ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡበትን ትችቶች ለውጡን ለመቀልበስ ከመሞከር ጋር ማያያዙም ለዚህ ማሳያ ነው ፡፡

ትናንት የወጣው መግለጫ ባለፈው መሰከረም ከወጣው መግለጫ የቀየረው ብቸኛ ነገር መደመር የሚልን ቃል ሙሉ በሙሉ አስወግዶ የዜጎች ሰላም፣ልማትና ዴሞክራሲ በሚል በመተካቱ ነው ፡፡ ከዚያ ውጭ ብዙ ነገሩ ያው ነው ፡፡ ስራ አጥነት ለመቅረፍ የተሰሩ ስራዎች ቢኖርም ካለው ችግር አንፃር በቂ አይደለም፤የምንዛሬ ጥረቱን ለመፍታት የተሰራው ስራ አጥጋቢ ቢሆንም የሚቀረው ነገር አለ፣የሀገሪቱን ሰላም ባሰተማማኝ መሰረት ላይ ለመጣል በርካታ ተግባራት ቢከናወኑም አሁንም ችግሮች አሉ፤ የፓርቲውን አመራር አንድነት ለመመለስ ከስምምነት ላይ ተደርሷል ………ወዘተ የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች በየስድስት ወሩ ለእድሳት የሚመጡ ይመስል መገናኛ ብዙሃንን ያጨናንቃሉ ፡፡

ግን ገዥው ፓርቲ እስከመቼ ነው የነተቡ ቃላትን ይዞ የሚዘልቀው ? እስከመቼ ነው የምንኖረውን ህይወት ለኛ መልሶ ሊያስረዳን የሚሞክረው ? መልስ በቀላሉ የማይገኝላቸው ጥያቄዎች ፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close