Connect with us

Ethiopia

የኢህአዴግ ምክርቤት አንኳር ውሳኔዎች

Published

on

የኢህአዴግ ምክርቤት አንኳር ውሳኔዎች

የኢህአዴግ ምክርቤት አንኳር ውሳኔዎች

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ከሚያዚያ 7 እስከ 8 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተወያየባቸው ዋና ዋና ነጥቦችን እነሆ፡-
ከፖለቲካዊ ስራዎች አንፃር ሰፊ ውይይት ከተካሄደባቸው ጉዳዮች

መካከል የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲና የአመራር አንድነት ይገኝበታል። ምክር ቤቱ በእህት ድርጅቶችና በአመራሩ መካከል የሚታየውን መጠራጠር በመፍታት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክሯል። ከዚህ አኳያ መታረምና መስተካከል ያለባቸው ነጥቦች ላይ ፍጹም ነጻ በሆነ መንገድ ሀሳብ እንዲንሸራሸርና በመጨረሻም አገርንና ህዝብን ማዕከል ያደረጉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ተፈጥሯል፡፡

በኢኮኖሚው መስክ

ሀገራዊ የኢኮኖሚ መቀዛቀዙን በማስተካከል ረገድ በጎ ሚና እንደነበራቸው የተመለከተው ምክር ቤቱ በተለይም ሀገራዊ የውጪ ምንዛሬ ክምችቱን በማሳደግ በኩል ትርጉም ያለው ስራ እንደተሰራ ገምግሟል። በዚህ መስክ መሻሻሎች እየታዩ ቢሆኑም ከፍተኛ የስራ አጥነት፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት፣ የብድር ጫና ችግሮች በአግባቡ ያልተቀረፉ በመሆናቸው መዋቅራዊ መፍትሄ ለመስጠት መረባረብ እንደሚገባ ምክር ቤቱ አስምሮበታል።

የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት

የወጣቶችን የተሳታፊነትና የተጠቃሚነት ጥያቄዎች በተለይም የስራ አጥነት ችግርን ለመፍታት እስካሁን የተደረጉት ጥረቶች ያሉ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ፍላጎት አንጻር አሁንም ከለውጡ በሚገባው ደረጃ ያልተጠቀሙበት ሁኔታ መኖሩን ምክር ቤቱ በአጽንኦት ገምግሟል። በተጨማሪም ወጣቶቹ ያሏቸውን የፖለቲካ ተሳትፎ ጥያቄዎች ገና በተሟላ ሁኔታ አለመመለሳቸውን አይቷል። በመሆኑም የወጣቶች ተጠቃሚነት ጉዳይ በቀሪ የበጀት አመቱ ወራት ልዩ አገራዊ አጀንዳ እና የርብርብ ማዕከል እንዲሆን ምክር ቤቱ ወስኗል።

ሠላምና ጸጥታ

ለግጭት እና አለመረጋጋት የሚዳርጉ ሁኔታዎች በግልፅ ተለይተው በአስቸኳይ መታረም እንዳለባቸውና መንግስትም ህግን የማስከበር ቁልፍ ሃላፊነቱን በጥብቅ መወጣት እንደሚገባው የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ከዚህ አኳያ ክልሎች እና የየአካባቢው መዋቅር የየራሳቸውን ህገ መንግስታዊ ግዴታ እንዲወጡ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

ሚዲያውን በተመለከተ

ከኋላው ታሪካችን ትምህርት በመውሰድ የወደፊት ተልዕኳችንን ለማሳካት የሚያግዙ መልዕክቶችን ከመቅረፅ ይልቅ ባለፉት ጉድለቶች ላይ ብቻ በመንጠልጠል ብሶትን ማራገብ የሚታይበት በመሆኑ በቀጣይ መታረም እንደሚገባው አሳስቧል።…የጥላቻ ንግግሮችን በህግ አግባብ መከላከል አስፈላጊ እንደሆነም ምክር ቤቱ አምኖበታል።

ለውጡን የሚፈታተኙ ተግዳሮችን በተመለከተ

ከጽንፈኛ ብሄርተኝነት፤ ስርዓት አልበኝነት እና የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ፈተናዎች የአገራዊ አንድነታችንን ችግሮች በመሆናቸው በተባበረ ክንድ በመፍታት፤ ለውጡን ማስቀጠልና ማስፋት ለምርጫ የሚቀርብ ሳይሆን የሀገር ህልውና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ከለውጡ በተቃራኒ ያሉ አስተሳሰቦችን መግራትና ተግባራትን መግታት ወቅቱ የሚጠይቀው ቁልፍ ተልዕኮ መሆኑን አስምሮበታል።

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close