Connect with us

Ethiopia

ለህወሓት ቀኑ አልመሸም፣ አሁንም አፉን ሞልቶ ይናገራል

Published

on

ለህወሓት ቀኑ አልመሸም፣ አሁንም አፉን ሞልቶ ይናገራል | በጫሊ በላይነህ

ለህወሓት ቀኑ አልመሸም፣ አሁንም አፉን ሞልቶ ይናገራል | በጫሊ በላይነህ

አሁን እየተፈጠሩ ላሉት አገራዊ ቀውሶች ከሚቀመጡ መፍትሔዎች አንዱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የውህደት ጥያቄን ማሳካት አንዱ እንደሆነ በራሱ በኢህአዴግ ታምኗል፡፡ በዚህም መሠረት ኢህአዴግ በዓመቱ መጀመሪያ በሐዋሳ ባካሄደው ጉባዔ ውህደቱ እንዲፋጠን ወስኖ ወጥቷል፡፡ ውህደቱ አጋር ድርጅቶችንም እንዲያቅፍ ተስማምቷል፡፡ ያኔ ህወሓት ውሳውን ተቀብሎ አጽድቆ ወጥቷል፡፡

ይህን ተከትሎ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋርና ሶማሌ ክልል ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት አንድ ጠንካራ አገራዊ ፓርቲ መመሥረት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚነጋገርበት፣ የሚወስንበት፣ ድምፁ የሚሰማበት ሥርዓት ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ገልፀው ነበር።

ሰሞኑን ግን የህወሓት ማዕከላዊ ኮምቴ እንዲከናወን አጽድቆት የወጣውን ሃሳብ የሚያፈርስ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ በተለይ ተፈጠሩ ያላቸው ችግሮች የራሱም አስተዋጽኦ መኖሩን መዘንጋቱ እንዲሁ ግራ አጋቢ መሆኑ አልቀረም፡፡

መግለጫው እንዲህ ይላል፡፡

“ኢህአዴግ ጀምሮት የነበረውና ተኮላሽቶ የቀረው በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴ ወደ ትክክለኛውን መስመር እንዲመለስ ከማድረግ ይልቅ፣ በቅርብ ጊዝያት አማራጭ የመፍትሔ አቅጣጫ ተብሎ እየቀረበ ያለዉ ጉዳይ፣ ኢህአዴግ በማዋህድ አንደ ሀገራዊ ፓርቲ ማድረግ የሚል ነው። በመሠረቱ የፓርቲ ውህደት ጥያቄ በተለያዩ ጊዜያት ሲነሳ የነበረና በጥናት እንዲመለስ አቅጣጫ ተቀምጦ እንደነበር ግልፅ ነው። ይህ አቅጣጫ የተቀመጠው ደግሞ ኢህአዴግ ጤናማ በነበረበት ወቅት፣ በመሠታዊ የድርጅቱ እምነቶችና መስመር ላይ ፅኑ እምነት በነበረበት እና ምንም መሸራረፎች ባልነበረበት ወቅት ነው። ይሁን’ንጂ የደፈረሰና ጉራማይለ አመለካከትና እምነት የያዘ ኢህአዴግ፣ አይደለም ለውህደት ከዚህ ከቀደም ለነበረው አደረጃጀቱም የሚሆን የአስተሳሰብና ተግባር አንድነት የሌለው ኢህአዴግ ነው ያለው። በሁሉም መሰረታዊ ጥያቄዎች የፕሮግራም፣ ስትራቴጂ፣ መለያ እምነቶች በእህት ድርጅቶች መካከል አንድ የሚያደርግ አመለካከትና እምነት በሌለበት፣ ሁሉም ወደተለያየ አቅጣጫዎች በሚላጋበት ውህድ አንድ ፓርቲ ሊታሰብ የሚችል አይደለም። ”

ህወሃት አያይዞም “አንድ የሚያደርግ የጋራ አመለካከት በሌለበት ወቅት አንድ ድርጅት እንደ ድርጅት ህልወና ሊኖረው አይችልም። አንድ የሚያደርግ አመለካከት በማይኖርበት ጊዜ ድርጅታዊ መበታተን እንጂ ውህደት ሊመጣ አይችልም። ስለዚህ ከውህደት በፊት፣ የሚያዋህደንን ነገሮች ልናስቀምጥ ይገባል። ”

ህወሓት ትላንት የዘራው አክራሪ ብሔርተኝነት እና ተጨቁነናል ትርክት ዛሬ ለቀውስ እንደዳረገን ገና አልተገለጸለትም፡፡ “ሁሉም ነገር የእኛ…. ክልላችን ለቃችሁ ውጡ…” የሚሉ የዘረኝነት የቀውስ አዙሪት ውስጥ የዶለን የእሱ ብሄር ተኮር አብዮታዊ ዴሞክራሲ መሆኑን ገና የገባው አልመሰለኝም፡፡ እናም ራሱን እንደጺላጦስ ከደሙ ንጹህ አድርጎ ዛሬም ሌላው ላይ ጣት መቀሰሩን ቀጥሏል፡፡ አፉን ሞልቶ መፍትሄው በድሮው መንገድ መሄድ ነው ይላል፡፡ ዛሬም ለህወሓት ቀኑ አልመሸም፡፡ ረግጦ፣ አፍኖ፣ ገድቦ፣ ገርፎ፣ ዘርፎ…የኖረበትን ያለፉት 27 ዓመታት አምባገነናዊ አገዛዝ “ሠላም” ነበር የሚል ዜማም አሰምቶናል፡፡ ወይ ህወሓት!?

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close