Connect with us

Ethiopia

የሽብርተኝነትና መስፋፋትና የመንግሥት ዘገምተኛ እርምጃ

Published

on

የሽብርተኝነትና መስፋፋትና የመንግሥት ዘገምተኛ እርምጃ

የሽብርተኝነትና መስፋፋትና የመንግሥት ዘገምተኛ እርምጃ | ጫሊ በላይነህ@DireTube

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ፣ ካራቆሬ፣ ማጀቴ እና ሌሎችም አካባቢዎች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ” የተደራጁ” በተባሉ ቡድኖች የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ከባድ ጉዳትን አስከትሏል፡፡ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም ከሶስት በላይ ንጹሃን ሰዎች ሞተዋል፡፡ በሥጋት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሸሽ የተገደዱ ሰዎች ቁጥር ብዙ ነው፡፡ እስከትላንትና ድረስ ጥቃቱ የመቀነስ አዝማማያ ቢያሳይም የአካባቢው ማህበረሰብ ደህንነቱ አሁንም ሥጋት አልተለየውም፡፡

ትላንት ከቀትር በኃላ የፀጥታ ሀይሎች አካባቢውን መቆጣጠር በመቻላቸው ጥቃቱ መቀነሱ ተሰምቷል፡፡

መነሻው ምን ነበር?

ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት ዶ/ር አምባቸው መኮንን በትላንትናው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሁኔታው ማዘናቸውንና ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን በመመኘት ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ በዚሁ መግለጫቸው ጥቃቱ በማን፣ ለምን ዓላማ እንደተፈጸመ ገና እየተጣራ መሆኑን በመጥቀስ ሕብረተሰቡ ለውንዥብር እንዳይጋለጥ መክረዋል፡፡

የአማራ ቲቪ፤ ኮሎኔል አለበል አማረ ን የአማራ ክልል የሠላም ግንባታና የሕዝብ ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ትላንት ከአጣዬ በስልክ ባናገራቸው ወቅት የጥቃት ፈፃሚዎች የኦነግ ታጣቂዎች ናቸው ካሉ በኃላ አሁን የፀጥታውን ሁኔታ ተቆጣጥረነዋል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ፀጥታ መምሪያ ሃላፊም በተመሳሳይ ሁኔታ ጥቃት ፈጻሚዎቹ የኦነግ አባላት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ “ይሄ የተደራጀ ሃይል በአካባቢው መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመት ሊሞላው ነው፣ ለክልሉ በየጊዜው አሳውቀን ቢሆንም የክልሉ ፀጥታ በቅርቡ እንደገና ከተዋቀረ ወዲህ እንቅሰቃሴ ቢጀመርም አልተቻለም፡፡የተገደሉና የታፈኑ ሰዎች አሉ።” ማለታቸውን ዘግቧል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ፣ ካራ ቆሬ፣ ማጀቴና በሌሎችም አካባቢዎች በንፁሀን ወገኖች ላይ እየደረሰ ያለውን የተደራጀ ጥቃት በመቃወም ትላንት ሠላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

መንግሥትም በንፁሀን ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ሞትና መፈናቀል እንዲያስቆምም ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በያዝነው ወር መጀመሪያ ሳምንት ላይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምነ ዋቀዮ በተባለ ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቆ ነበር።

በጥቃቱ የተገደሉት ሦስት ኢትዮጵያዊያን እና ሁለት የውጪ ሀገራት ዜጎች ነበሩ፡፡ ከሟጮች መካከል አንደኛው የኩባንያው ባለቤት ነበር፡፡

መንግሥት እንዲህ ዓይነት ጥቃት ሲፈጸም ምን እርምጃ ወሰደ የሚለው የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በዚህም ምክንያት መንግሥት ባለበት አገር በጠራራ ጸሐይ እየተፋፋመ የመጣውን የሽብር ድርጊት በአስተማማኝ መልኩ ማስቆም አልቻለም የሚል ቅሬታ በተደጋጋሚ ከዜጎች እየቀረበበት ነው፡፡ በተጨማሪም የኢኮኖሚ ዋልታ የሆኑ ባለሀብቶች ጭምር በሠላም መታወኩ አገራችንን በቀጣይ ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን መንግሥት አጢኖ በማያዳግም መልኩ ጠንካራ እርምጃ ሲወስድ አለመታየቱ ሽብርተኝነትና አክራሪነት እንዲስፋፋ ምክንያት እየሆነ ነው በሚል በስፋት እየተተቸ ነው፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close