Connect with us

Business

ኢቫንካ ትራምፕ ኢትዮጵያ ልትመጣ ነው

Published

on

ኢቫንካ ትራምፕ ኢትዮጵያ ልትመጣ ነው

ኢቫንካ ትራምፕ ኢትዮጵያ ልትመጣ ነው | Bekky@diretube

የነጩ ቤተመንግስት አማካሪና የዶናልድ ትራምፕ ልጅ የሆነችው ኢቫንካ ትራምፕ በዚህ በያዝነው የአፕሪል ወር ወደ አፍሪካ መጥታ በኮትዲቯርና በኢትዮጵያ የአራት ቀን ቆይታ እንደሚኖራት ተወርቷል።

የሴቶች አለም አቀፋዊ ተሳትፎ፣ እድገትና ልቀት ላይ የሚያተኩረው (Women’s Global development and Prosperity initiative) አመራር መሆኗን ተከትሎ ነው የመጀመሪያ አፍሪካዊ ጉዞዋን የምታካሂደው።

በትናንትናው እለት ከነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባዮች እንደተሰማው በአይቮሪኮስት የሚካሄደውን ሴቶችን በኢኮኖሚ ተሳትፎ ሀይል የማስታጠቅ ስብሰባ (women’s economic empowerment summit) የምትካፈል ሲሆን በኮትዲቯር ቆይታዋም ከስብሰባው ውጭ ሴት ፖለቲከኞችን ኢንተርፕረነሮችን እና የዋአኔ ሰጪ ቦታ ላይ የሚገኙ ሴቶችን ታገኛለች ብሎ አሶሺየትድ ፕሬስ አውርቷል።

ከዚያም በኋላ ከፍተኛ የሴቶች ተሳትፎ በፖለቲካ እያሳየች ወደምትገኘው ኢትዮጵያ ትመጣለች። በቢዝነሱ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ እንስቶችን፣ በፖለቲካው ምህዳር ሚናቸው ያደጉ ሚኒስትሮችና ባለስልጣናትን እንዲሁም የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ሚናቸው ከፍ ያሉ ባለሙያዎችን ያገኛሉ ተብሏል።

አብረዋትም የአለም አቀፍ የአሜሪካ እድገት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ማርክ ግሪንና የውጭ የግል ንግዶች ፕሬዚዳንት ዴቬድ ቦሄይን እና ከአለም ባንክ ክሪስቲና ጂኦርጂቫ ያጅቧታል።

ለአሶሽየትድ ፕሬስ በሰጠችው ቃልም ወደ አፍሪካ ለምታደርገው ጉዞ ዝግጁ መሆኗን ተናግራ በጉዞውም ደስተኛ እንደሆነች ገልጻለች።

በፌብርዋሪ የተመሰረተው የኢቫንካ ኢኒሼቲቭ በ2025 50 ሚሊየን የሚደርሱ ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማንቃት እየሰራ የሚገኝ ኢኒሺዬቲቭ ነው።

በስቴት ዲፓርትመንት በጀት የሚደገፈው የኢቫንካ ኢኒሺዬቲቭ በተለይ በታዳጊ አገራት የሚገኙ ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃትና ለማሳደግ የሚሰራ ሲሆን እስካሁን በተመደበለት የ100 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክቶችን አቀናጅቶ ለሴቶች የገንዘብ ድጋፍ፣ ስልጠናዎችንና የህግ ማዕቀፎችን ለማስተካከል ይውላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በህንድና በጃፓን ተመሳሳይ ጉዞ እንዳደረገች ይታወሳል።

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close