Connect with us

Africa

ጆሞ ኬኒያታ ነጭ ጭራ ሚስጥር

Published

on

ጆሞ ኬኒያታ ነጭ ጭራ ሚስጥር

ጆሞ ኬኒያታ ነጭ ጭራ ሚስጥር | እስክንድር ከበደ በድሬቲዩብ

ጆሞ ኬኒያታ የኬኒያ መስራች አባት ናቸው:: ኬኒያታ ሀገሪቱ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት እንድትላቀቅ ከታገሉ የኬኒያ አርበኞች በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ:: ጆሞ ኬኒያታ የኬኒያ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር (እ.ኤ.አ 1963-1964) እና የመጀመሪያው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት (እ.ኤ.አ1964 -1978) ነበሩ::

ጆሞ ኬኒያታ በቅጥል ስም ሜዚ ብለው ይጠሯቸዋል:: ”ሜዚ” የሚለው በአፍሪካ ለ”ብልህ አዛውንት” የሚሰጥ ስያሜ ነው:: ኬኒያን ለ14 አመታት የመሩት ኬኒያታ፤ በአለባበሳቸው በተለይ ከእጃቸው የምትጠፋው ነጭ ጭራ ይታወቃሉ:: የቆዳ ጃኬት ፣ ትላልቅ የጣት ቀለበቶች ፣ ጌጠኛ ከዘራ እና ነጭ ጭራ ያዘወትሩ ነበር::

የናይሮቢ የቀድሞ ከንቲባ ቻርልስ ሩባይ የኬኒያታ ነጩ ጭራ የተሰጣቸው በኢትዮጰያው መሆኑን ይናገራሉ : : በንጉስ አጼ ሃይለስላሴ ነጭ ጭራ ለጆሞ ኬኒያታ የተሰጠ ነበር::

እ.ኤ.አ በ1963 ኬኒያ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነጻ የወጣችበት እና ጆሞ ኬኒያታ በጠቅላይ ሚኒስተርነት ባአለሲመት ላይ ያቺን ነጭ ጭራ በብዙህ ሺዎች ለሚቆጠሩት ኬኒያውያን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ ይታያሉ:: በክፍት መኪና ላይ ሆነው በህዝብ ማህል ሲያልፉ ሁል ጊዜ ይህችኑ ጭራ ያውለበልባሉ:: ለኬኒያታ ያቺ ነጭ ጭራ የሰላምና የስልጣን ምልክት ተደርጋ ትወሰዳለች:: ኬኒያታ ያችን ጭራ ሲያራግቡት የሰላም ምልክታቸው እንደማሳየት ይቆጠር ነበር የናይሮቢ ቀድሞ ከንቲባ ይላሉ::

ኬኒያታ በማኦ ማኦ አመጽ በእንግሊዝ አስተዳደር ለ9 አመታት በግዞት ታስረውና ለከፍተኛ የጉልበት ስራ ቅጣት ተዳርገው በ1961 ነበር የተለቀቁት::

በ1963 በምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ስልጣኑን ሲይዙ፤ በነጮች ሰፋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ ተከስቶ ነበር:: ነጮቹ ጆሞ ኬኒያታ ሰብስበው እንዲያናግሯቸው በጠየቁት መሰረት ስብሰባው በናይሮቢ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ ተካሄደ::

በወቅቱ የፕሬዚዳንቱ አራቱ ወጣት የመንግስት አማካሪዎች ነጭ እንግሊዛውያን ሰፋሪዎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ይንገሯቸው ብለው መከሯቸው:: አማካሪዎቹ ነጮቹ ወዲያው ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ይፈልጉ ነበር። ኬኒያታ ”እሺ” ከማለት ሌላ ምንም አላሉም ነበር::

ጆሞ ኬኒያታ በመደረኩ አብረዋቸው ከታደሙት አራቱ አማካሪዎቻቸው መሃል ተቀምጠው ነበር :: ዶ/ር ጆራዬ ሞንጋይ በወቅቱ ከአራቱ የመንግስት አማካሪዎቻቸው አንዱ ነበሩ:: አማካሪው ኬኒያታ የመከርናቸውን ትተው ሌላ ነገር ተናገሩ ይላሉ :: በኋላ ከመቀመጫቸው ተነስተው እንዲህ አሉ::

I think some of you have been …may be worried …what will happen if Kenyatta comes to be the head of the government? Well now let me set you to rest that Kenyatta has no intention of whatsoever to look backwards. We are going to forgive the past..

እንግሊዛውያኑ ሰፋሪዎች እንዳይጨነቁ ኬኒያታ ወደ ኋላ ማየት ሳይሆን ያለፈውን ይቅርታ እንደሚያደርጉ ገለጹላቸው:: የተፈራው ሳይሆን እንግሊዛውያኑና ኬኒያውያኑ አብረው መኖር እንዳለባቸው አስተማሩ::

ኬኒያታ በስልጣን ዘመናቸው በእንግሊዛውያኑ የተሰረው ቤተ መንግስት ውስጥ አንድም ቀን አድረው አውቁም :: ጣረ ሞት ያስቸግረኛል በሚል በቤተ መንግስቱ አያድሩበትም:: እጅግ ቢመሽም ከናይሮቢ 50 ኪሎሜትሮች ርቆ የሚገኘው ትውልድ መንደራቸው ኮንተንዴ ተጉዘው ይገባሉ:: ቤተሰባቸው የአሁኑ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ጨምሮ ይኖሩ የነበሩት በዛች ገጠራማ መንደር ነበር::

ኬኒያታ ”ሀራምቤ” በሚል መፈክር ነጭ ሰፋሪዎችና አፍሪካውያን ለኬኒያ እድገት በጋራ ተባብረው እንዲሰሩ አወጁ :: ኬኒያታ የኬኒያውያን ቆየ ልማድና ባህል ”ሀራምቤ ”የሚል ደውል ደወሉ::

ሀራምቤ የኬኒያውያን ማህበረሰቦች እራስ አገዝ የገንዘብ ማሰባሰብ ወይም በደቦ ልማትን በጋራ የመስራት ባህል መሆኑ ይነገራል:: ሀራምቤ ቃሉ ስዋሂሊ ሲሆን በግርድፉ ” ”ሁላችንም እንተባበር” የሚል ትርጉም አለው:: አሁንም ሀራምቤ የኬኒያ ብሄራዊ አርማ ነው::

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close