Connect with us

Ethiopia

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተቀሰቀሰዉ ግጭት ‹‹ተሳትፈዋል›› በሚል 39 ተጠርጣሪዎች ተያዙ

Published

on

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተቀሰቀሰዉ ግጭት ‹‹ተሳትፈዋል›› በሚል 39 ተጠርጣሪዎች ተያዙ

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ጣምያለዉ የዞኑን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በዞኑ በተለይም ከሕዳር 23 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ ሀብት እና ንብረታቸውም ለዉድመት ተዳርጓል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ዜጎችም ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

ችግሩ በማዕከላዊ ጎንደር ብቻም ሳይሆን በምዕራብ ጎንደርም የተከሰተ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዞኑ ወደ 49 ሺህ 500 የሚደርሱ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መጠለያ እና በዘመድ አዝማድ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ። አቶ ብርሃኑ በመግለጫቸው ከየካቲት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክልሉ እና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ከኅብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን የአካባቢውን ሰላም በማስከበር ወደነበረበት ለመመለስ እየሠሩ ይገኛሉ። እስካሁንም ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ኃይል ስምሪት በማድረግ የተሻለ ውጤት የተገኘበት ሥራ መከናወኑን አስታውቀዋል።
የተፈናቀሉ ወገኖች ከገጠማቸው ችግር ነጻ ሆነው ወደ ቀደመ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንዲመለሱ በቅደም ተከተል እየተሠራ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል። የመጀመሪያው ተግባር ሕዝቡን ከጥቃት መከላከል እና የእርስ በርስ ግጭት እንዲቆም ማድረግ መሆኑን የተናሩት ዋና አስተዳዳሪው ‹‹ይህም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም ውጤታማ ሥራ ተሠርቷል›› ብለዋል። ምንም እንኳን ከእርስ በርስ ግጭት ሕዝቡን መታደግ ቢቻልም በግለሰብ ደረጃ የሚፈጸሙ ትንኮሳዎች መኖራቸውንም አስታውቀዋል። መንግሥት ወንጀለኞችን የማይታገስ መሆኑን እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እርምጃ እንደሚወስድም ተናግረዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረስ እና ከድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች፣ የክልሉ እና ከክልሉ ዉጭ የሚገኙ ዜጎች ድጋፍ በማሰባሰብ ተፈናቃዮች እንዲረዱ እየተደረገ መሆኑንም በመግለጫቸው አንስተዋል።

የግጭቱ ተዋናይ የነበሩና የትራንስፖርት ፍሰትን ሲያስተጓጉሉ የነገሩ ግለሰቦች እና ቡድኖች ለመለየት ጥረት መደረጉንም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት ወደ 39 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ን የገለጹት። ይህ ተግባር ወደፊትም ተጠናክሮ ወንጀለኞችን ለሕግ የማቅረብ ሥራው እንደሚቀጥልም በአጽንኦት ተናግረዋል። አስተዳዳሪው አጀንዳ ፈጥረው በግል እና በቡድን የሚንቀሳቀሱ አካላት ከተግባራቸው እንዲቆጠቡም ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዋና አስተዳዳሪው መግለጫ መሠረት ችግሩ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ተዘግተው የነተሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሥራ እንዲጀምሩ ተደርጓል። በሁለቱ በጭልጋ፣ በደንቢያ እና በላይ አርማጭሆ አካባቢ ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት እና ሌሎችንም አካቶ ከ85 በመቶዉ በላይ የሚሆኑት አገልግሎት እንዲጀምሩ ተደርጓል። የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በየአካባቢው ካሉ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሕዝባዊ ውይይት እና የእርቅ መርሀ-ግብሮችን በማዘጋጀት እያወያየ መሆኑም ታውቋ።

በተፈጠረላቸው መድረክም የሕግ የበላይነት እንዲከበር በተደጋጋሚ ዜጎች መጠየቃቸውና ከግጭቱ ከውድመት እና ሕይወት መጥፋት በስተቀር የተገኘ ትርፍ አለመኖሩን ሁሉም አካላት መረዳታቸውንም ተናረዋል፡፡ ሁኔታውን በመረዳት ተፈናቃዮች ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ሁሉም አካላት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።

መንግሥት የፋብሪካ ውጤት የሆኑ የቤት መሥሪያ ቁሳቁሶችን በማቅረብ እንዲሁም ሕዝቡም በአካባቢው የሚገኙ ቁሳቁሶችን በማቅረብ እና በጉልበትም ጭምር በመረባረብ የተፈናቃዮች ቤት ተሰርቶ በተቻለ ፍጥነት ወደ ቀደመ ሕይወታቸው እንዲመለሱ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በደረሠን መረጃ መሠረትም ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል፡

(አብመድ)

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close