Connect with us

Ethiopia

ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ | በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ

Published

on

ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ | በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ

ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ | በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ

ኦቦ ለማ በአሁኑ ሰዐት ኢትዮጵያዊነት እንደመጀመሪያው ሱሱ መሆኑን ለጊዜው ማረጋገጫ የለኝም። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ግን የሆነ ቢመጣ በኢትዮጵያዊነት እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ እንደማይደራደር ግን አልጠራጠርም። ይህንንም የምለው በተናገራቸው ቃላትና በአደረጋቸው ድርጊቶች ተመርኩዤ ነው።

እርግጥ ነው፤ በብዙ ጉዳደዎች ላይ እኔም ሆንኩ አያሌ የኢትዮጵያ ህዝብ አስቸኩዋይ ርምጃዎችን (የበቀል እርምጃዎችንም ጭምር) እንዲወስድ ፈልገን እና ተመኝተን ይህን ባለማድረጉ ፣ እንዲሁም ይህን ለማድረግ ባይችልም እንኩዋን ስለጉዳይዎቹ በአደባባይ ባለመናገሩ፣ እሱን ብንወደውም ሳናዝንበትና ቅር ሳንሰኝበት አልቀረንም። እሱን ጠበቅ አድርገን ለምን ፍላጎታችንን እንዳላሟላልን ብንጠይቀው ግን የራሱ አሳማኝ መልስ ሊኖረው ይችላል። ከመልሱ ውስጥ ግን እሱም ባይነግረንም እኛም በዐይናችን የምናየውና በጆሮአችን የምንሰማው የጸረ-ለውጦች እና እኩይ አላማ ያላቸው ጽንፈኞች መሪር ፈተና እና ጫና እንዳለቡት ሳይንጸባረቅ አይቀርም።

ባለፉት 10 ወራት እሱ ያደረጋቸውን መሳጭ ንግግሮች እና ተጨባጭ ድርጊቶች በጥልቀት ከመረመርኩ በሁዋላ፣ እኔ አንድ መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ።— ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዝቅ ሲል ስልጣኑን እስከመልቀቅ፣ ከፍ ሲል ህይወቱን እስከማሳለፍ ይደርስ ይሆናል እንጂ ኢትዮጵያ ስትበጣጠስ እጁን አጣጥፎ ዐያይም። የኢትዮጵያን አንድነት አስመልክቶ፣ ከመሳጭ ንግግሮቹ ውስጥ አንዱ “አንዳንድ ሰዎች ሀገርን መገንጠል ከዛፍ ላይ ቅጠል እንደመበጠስ ይመስላቸዋል፣ ሀገር ግን የሚበጠስ ቅጠል አይደለም፣” ያለው ነው። እናም ይህን ንግግሩን በተግባር ማዋሉ ነው።

መቼ ቢባል፣ የጅጅጋው ወንጀለኛ አብዲ ኢሌ አገር መገንጡሉን ሊያውጅ አንድ ስአት ሲቀረው ዶክተር ዐብይ ተሽቀዳድሞ አብዲ ኢሌን ይዞ አገር ማዳኑ ነው። እራሱ የደንብ ልብሱን ለብሶ እና የኮሌኔልነት ማእረጉን አድርጎ ወደጅ ጅጅጋ ገስግሶ ነው ጦሩን የመራው የሚሉም አሉ። ይህን ግን እኔ ለማረጋገጥ አልችልም። እንግዲህ ማንም ሆነ ማንም አገር እገነጥላለሁ ብሎ ቢነሳ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ክንዱን ሳይንተራስ አገር ሲገነጠል እጆቹን አጣጥፎ ያያል ማለት ዘበት ነው።

የኢትዮጵያን ጉዳይ አስቀምጦ ለምን አገር ላገር ይዞራል ብለን ብንነቅፈውም፣ በኢትዮጵያ ዙሪያ እና በባህር ማዶም ካሉት ሀገራት ጋራ (ኤርትራን ጨምሮ) የሚመሰርተው ወዳጅነት የኢኮኖሚ ጥቅም ማስገኘት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና አንድነት በውስጥ ጠላቶች ከተገሰሰ በሚያስፈልገው ሁሉ ኢትዮጵያን እንዲያግዙ ይመስለኛል።

ዶክተር ዐብይ ሰሞኑን ኢትዮጵያን ከጎቡኙት የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ጋራ ካደረጋቸው የኢኮኖሚክ ግንኙነት በተጨማሪ፣ የተዋዋላቸው በውትድርና ዘርፍ አብሮ የመስራት ውል በእኔ ዕይታ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና አንድነት ማስጠበቂያም ዩሚበጅ ይመስለኛል።

ነገሬን ለመቁዋጨት ያህል፣ ዶክተር ዐብይ “ስንኖር ኢትዮጵያውያን፣ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን፣” ባለው አሁንም ያምናል ብዬ አስባለሁ። በኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና አንድነት ላይ ያለውም አቋም እንደበፊቱ የጸና ነው ብዬ እናገራለሁ። የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እና አንድነት ለማስከበር እና ኢትዮጵያ እንዳትበጣጠስ ለመከላከል የሚችል በአሁኑ ሰዐት ከእሱ የተሻለ ማን ሰው አለ፣ ብዬ ራሴን ስጠይቅ፣ ኩውስጠውስጤ “ማንም የለም፣” የሚል መልስ አገኛለሁ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close