Connect with us

Ethiopia

‹‹አዳዲስ አልቃሽ እያስተናገድሁ ነው የምውለው ›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

Published

on

‹‹አዳዲስ አልቃሽ እያስተናገድሁ ነው የምውለው ›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

‹‹አዳዲስ አልቃሽ እያስተናገድሁ ነው የምውለው ›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
(ከበኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን)

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ ወደ ፖለቲካዊ መነቃቃት ያስገቡን መሪ ናቸው፡፡ ይነስም ይብዛም በአሥር ወር ውስጥ ብዙ ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡ በውጭም በውስጥም ለመሥራት የጣሯቸው ነገሮች አሉ፡፡

አንዳንዱ ሰው ግን አስገራሚ ነው፡፡ ከአሥራ አንድ ወር በፊት ኡኡኡ ብሎ ዝም ያለውን በሙሉ፣ ከእርሱ በተቃራኒ የቆመን ሁሉ ‹‹የቀን ጅብ›› እያለ፣‹‹ተደምሬያለሁ›› ብሎ መፈክር ይዞ እንዳልወጣ፣ አሁን በጠቅላይ ሚኒስትሩና በመንግሥታቸው ላይ እርግማን ሲያዘንብ እየታየ ነው፡፡ ‹‹በፈረኦን ቤት ያደገ ሙሴ›› እያለ እንዳልፃፈ ዛሬ፣‹‹ራሱ ፈረኦን ነው›› ወደሚል ቀይሮ እያጣጠለ ነው፡፡ይሄ በውነቱ ውለታ ቢስ መሆን ነው፡፡

ጎበዝ ኧረ እየተረጋጋን፡፡ ስንቀነስ እንዲህ ከቸኮልን ስንደመር ምክንያት አልነበረንም ማለት ነው፡፡ ለነገሩ ጠቅላይሚኒስትሩ ራሳቸው ይሄንን ሕዝብ በደንብ አውቀውታል፡፡ እርካብና መንበር በሚለው መጽሐፋቸው በጥልቀት ማኅበረሰባዊ ትንታኔ ጽፈዋል፡፡ከገብረሕይወት ባይከዳኝና ከልደቱ አያሌው ውጭ ሕዝብን የተቸ ልሂቅ የማውቀው ዓቢይ አሕመድን ብቻ ነው፡፡ሕዝብ ውለታ ቢስና ለለውጥ የማይሁን ‹ኤንቲቲ› እንደሆነ አስነብበውናል-በእርካብና መንበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጽሀፍ በዘለለ በተለያዩ የመድረክ ንግግሮቻቸውም ይህንን ሐሳብ አጎላምሰውታል፡፡ ለምሳሌ የበዓለ ሲመታቸው ሰሞን ወደ ደቡብ ተጉዘው በሀዋሳ በተካሄደ ስብሰባ ላይ፣ ‹‹ይሄ ሕዝብ አስፓልት ብትሰራለት ሳር አማረኝ ይላል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለነገሩ ኮሎኔል መንግሥቱም፣ ‹‹ይሄ ሕዝብ ወርቅ ብታነጥፍለት ፋንዲያ ነው ይላል›› ብለው ሕዝቡን ራሱን አስቀውት ነበር፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት የታዳጊ ክልሎችን ሰብስበውም ‹‹ይህንን ሕዝብ ይዞ መሻገር ከባድ ነው›› የሚል አንድምታ ያለው ንግግር ተናግረው ነበር፡፡

‹‹አልቃሽ ሕዝብ አይሻገርም›› ያሉት ጠቅላይሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ ‹‹እያመመኝ መታከም አልቻልኩም›› ብለዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ምክንያት ያደረጉት ‹‹በክላሽ ሲታኮስ የሚውለውን›› አልቃሽ ሕዝብ ነው፡፡ ቀጠሉናም‹‹አዳዲስ አልቃሽ እያስተናገድሁ ነው የምውለው ሶፍት ይዤ መቅረብ ሆኗል ሥራዬ፤ በዚህ ከቀጠልን በሚቀጥለውም ዓመት ለቅሶ ይሆናል››አሉ፡፡ ሕዝቡ ማልቀስ እንጂ ምሳጋና እንደማያውቅም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ እንኳን ለመሪዎቹ ለኃይማኖቱም መገዛት ያልቻለ መሆኑን ደግሞ ‹‹ሀይማኖታችሁ እንኳን የማይገዛችሁ ከሆነ እኔ እንዴት እፈታላችኋለሁ››በማለት ገልጸውታል፡፡‹‹የሰላም ዋጋ የገባው ሕዝብ የለንም›› ያሉት ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ፣‹‹ኃላፊነት የማይወስድ ሕዝብ ችግር አይፈታም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማስተዋል አለበት፡፡

ሁሉም ተበዳይ እንጂ በዳይነቱ አይታየውም›› ብለዋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ አጠቃላይ ችግር ማንና ማንን መቼ እንደሚያወዳድር አያውቅም፤ መሪዎቹ በሥልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያ 10 ወራት ጋር አነፃፅሩኝ፡፡ የ20 ዓመቱን ሰው ከ10 ወሩ ጋር ካወዳደርክ አልገባህም ማለት ነው›› ሲሉም ሕዝቡ ንቃተ-ኅሊናው ገና እንደሆነ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

ይህንን የጠቅላይሚኒስትሩን ንግግር ስንመለከት ነው እንግዲህ ከ10 ወር በፊት ተደምረው አሁን እየተቀነሱ ያሉ ሰዎችን መረዳት የማይከብደን፡፡ ቀድሞ ነገር በምክንያትና በስሌት ብንደመር ኖሮ አሁን በሰሞነኛ ነፋስ ተቀንሰናል ለማለት አንፈጥንም ነበር፡፡ችግሩ ሁሉንም ነገር በስሜት ስለምናደርገው ውጤቱ እራሳችንን ማሳጣት ሆነ፡፡

ቸኩለን ተደምረን ፈጥነንማ አንቀነስ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close