Connect with us

Education

ህዋዊ በኢትዮጵያ የ2011 የቴክኖሎጂ ውድድር ማጠናቀቁን አስታወቀ

Published

on

ህዋዊ በኢትዮጵያ የ2011 የቴክኖሎጂ ውድድር ማጠናቀቁን አስታወቀ

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ውድድር በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ከ4,000 በላይ ተማሪዎች እና መምህራን አሳትፏል፡፡

አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ – ማክሰኞ፣ የካቲት 26፣ 2011 ዓ.ም- በትናንትናው እለት በሀርሞኒ ሆቴል በተካሄደው የህዋዊ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ICT) የሞያ ውድድር የመዝጊያ ስነሥርዓት ላይ፤ ህዋዊ ውድድሩ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ በህዋዊ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየዉ ውድድር ከቻይና ኤምባሲ ባለስልጣናት፤ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር፤ በሀገሪቱ ላለፉት ሶስት ወራት ሲካሄድ እንደነበረ ይታወሳል፡፡

ዉድድሩ ለተማሪዎች እና መምህራን በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ያላቸዉን ብቃት ለመገምገም የተዘጋጀ ሲሆን ሃያ (20) የትህምሕርት ተቋማት እና ከ4,000 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በህዋዊ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዉድድር አሳትፏል፡፡ ይህ ከመንግስት፤ ትምህርትና ኢንዱስትሪ የተዋቀረ ሐሳብ የተለያዩ ጥቅሞችን ከማበርከትም ባሻገር በዩኒቨርስቲ ድርጃ ላይ ላሉ ተማሪዮች የቴክኖሎጂ ዝውውር፤ የተሻለ ሥርአተ ትምህርት ለማዳበር እና ተማሪዮችን ለወደፊት የቅጥር እድሎችን ለማዘጋጀት ታስቦ ነው፡፡

“ይህ ልዩ ዉድድር ለተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እና መምህራን ጋር የልምድ ልዉዉጥ እንዲያደርጉ እድሉን ስለሰጠናቸዉ ደስ ብሎናል” ይላሉ የህዋዊ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ቴድ ሜንግዩ፡፡

ዉድድሩ ሶስት ደረጃዎች የነበሩት ሲሆን ይህም አንደኛ፤ መካከለኛ እና የመጨረሻ ደረጃዎችን ያካትታል፡፡ እያንዳንዱ የትምህርት ተቋም የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፈተናዎችን በማካሄድ ሶስት ከፍተኛ ነጥብ ላመጡ ብቁ ተማሪዎች በመምረጥ እነዚህ ተማሪዎችን ደግሞ የህዋዊ ተወካዮች በተገኙበት የመካከለኛ ደረጃ ዉድድር ተወዳድረዋል፡፡ ከዚያም ከመካከለኛ ደረጃ ዉድድር 10 ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ብቁ ተማሪዎችን በመምረጥ ለመጨረሻ ደረጃ ዉድድር ተሳትፈዋል፡፡

እንደ ሚታወሰው ዉድድሩ ከመካሄዱ በፊት በሕዳር 2011 ዓ.ም በትምህርት ሚኒሰቴር ግቢ ዉስጥ ህዋዊ ዉድድሩን የመክፈቻ ፕሮግራም በማድረግ የዉድድሩን ሶስት ክፍሎች ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ የመክፈቻ ፕሮግራሙን በመቀጠል ህዋዊ ዉድድሩን ለማስተዋወቅ የሚሆኑ ዝግጅቶች፤ ማለትም የበራሪ ወረቀት ስርጭት፤ ትላልቅ የማስተዋወቂያ ሰሌዳዎችን መስቀል እና የመንገድ ትርኢት ማነቃቂያ ሲሰራ እንደቆየ ያታወቃል፡፡

“ይህን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዉድድር የማዘጋጀታችን አላማ ለተማሪዎችና መምህራን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን አዳዲስ ክህሎቶችንና ግኝቶች ይፋ በማድረግ፤ የኢትዮጵያን መገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለማሳደግ እና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ነዉ” ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በመዝጊያዉ ፕሮግራም ላይ የህዋዊ ተወካዮች ለተማሪዎች፤ ለመምህራን እና ለትምህርት ተቋማት የሽልማት ስነስርአት ያካሄዱ ሲሆን፤ ከሶስቱ አሸናፊዎች መካከል ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ይብራ መሃሪ እና የማነ ሰጊድ (ከመምህራን) አንደኛ ሲወጡ፤ በአስተባባሪነት አሸናፈ የሆኑት ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ራሄል ተስፋዬ ነበሩ፡፡ የሽልማቶቹ አይነት ከህዋዊ ሜት 10 ሞድል ተንቀሳቃሽ ስልክ አንስቶ እስከ ሰርቲፊኬት ተሰጥቷል፡፡ ከአሸናዎቹ መካከል ተማሪ ይብራ መሃሪ ተመርጦ በሸንዘን ቻይና በሚኪያሄደዉ የአለም አቀፍ ወድድር ላይ ይሳተፋሉ፡፡

ስለ ህዋዊ
ህዋዊ በአለም አቀፍ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መፍተሄ ሰጪ ድርጅት ነዉ፡፡ ደምበኞችን ያማከለ አዳዲስና ጠንካራ የሽርክና ማህበሮቻችንን በመጠቀም ጫፍ እስከ ጫፍ የሚያካክሱ የቴሌኮም የአውታረ መረቦች፣ መሳሪያዎች እና የክላዉድ ኮምፒውቲንግ መፍትሄዎች አቋቅመናል፡፡ ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች፣ ኩባንያዎች እና ደምበኞች የተሻለ መፍትሄዎችን እና አገልግሎት ለማበርከት ምን ጊዜም ዝግጁ ነን፡፡ ምርቶቻችን እና መፍትሄዎቻችን በ 140 ሀገሮች አገልግሎት ላይ የዋሉ ሲሆን ይህም በአለም ዉስጥ ላሉ አንድ ሶስተኛ ለሚሆኑ ህዝቦች አገልግሎት ሰጥተናል፡፡

ስለ ህዋዊ ዉድድር የመለጠ መረጃ ለማግኘት ይጎብኙ፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close