Connect with us

Business

ስለአልኮል መጠጥ ሽያጭ እና ማስታወቂያ በቅርቡ በፓርላማ የፀደቀ አዋጅ

Published

on

አልኮል መጠጥ ሽያጭ እና ማስታወቂያ በቅርቡ በፓርላማ የፀደቀ አዋጅ

ስለአልኮል መጠጥ ሽያጭ እና ማስታወቂያ በቅርቡ በፓርላማ የፀደቀ አዋጅ:-

~የምግብ ደህንነት አስተዳደርን በተመለከተ፣

• አስገዳጅ ደረጃ የወጣለት ማንኛውም በሀገር ውስጥ የሚመረት ምግብ የአስገዳጅ ደረጃ ምልክት ሊኖረውና ይህንኑ ሊያረጋግጥ የሚችል ወቅታዊ ሰርተፊኬት የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

~ስለ አልኮል መጠጥ ሽያጭ እና ማስታወቂያ

• ማንኛውም የአልኮል መጠጥ ከ 21 አመት በታች ለሆኑ ሰዎች መሸጥ የተከለከለ ነው፡፡
• አልኮል ይዘቱ ከአስር በመቶ በታች የሆነ አልኮል በብሮድካስት አማካኝነት ማስተዋወቅ የተከለከለ ነው፡፡

ይህ ክልከላ የማንኛዉም የአልኮል ምርት የብራንድ ስም፣ አርማ፣ የንግድ ምልክት፣ የድርጅት አርማ፣ የንግድ መለያ ወይም ሌላ ተያያዥ መለያን የአልኮል ምርት ካልሆኑ ሌሎች ምርቶች፣ አገልግሎቶች ወይም ጉዳዮች ጋር በማያያዝ ወይም በሌላ መንገድ ቁርኝት እንዳላቸው በሚያሳይ ማንኛውም ማስታወቂያ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

• የአልኮል መጠጥን ከሎተሪ እጣ ጋር በማንኛውም መንገድ በማያያዝ የሚደረግ የማስተዋወቅ ተግባር የተከለከለ ነው፡፡

• በፋብሪካ ደረጃ ተዘጋጅቶ ለህብረተሰብ የሚቀርብ ማንኛውም የአልኮል መጠጥ ገላጭ ፅሁፍ የአልኮል መጠኑን፣ በተገቢ መንገድ ካልተጠቀሙ የጤና ችግር እንደሚያመጣ እንዲሁም አልኮል መጠጣት ጽንስን ሊጎዳ እንደሚችል በጉልህ በሚታይ ጽሁፍ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡

• ማንኛውም የአልኮል ይዘቱ ከ10% በላይ የሆነ አልኮል አምራች፣ አስመጪ ወይም አከፋፋይ የህዝብና የመንግስት በዓላት እና ስብሳባ፣ የንግድ ትርዕት፣ የስፖርት ውድድርን፣ የትምህርት ቤት ዝግጅትን እና ሌሎች ወጣት የሚሳተፉበትን ኩነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋወሪ ስፖንሰር ማድረግ አይችልም፡፡

• የአልኮል ምርት የጤና ማስጠንቀቂያ መስፈርቶችን የሚመለከተው አንቀጽ 55 ይህ አዋጅ ከጸደቀ ከስድስት ወራቶች በኋላ እንዲሁም አልኮልን በብሮድካስት እና በቢልቦር አማክኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው አንቀጽ 60 ይህ አዋጅ ከጸደቀ ከሶስት ወራቶች በኋላ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

~መድኃኒት እና የህክምና መሳሪያ አስተዳደር

• አስፈጻሚ አካሉ መድኃኒት ወይም የህክምና መሳሪያን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ወይም ለማከፋፈል ከአምራች ድርጅት ጋር የሚደረግ የወኪል ቁጥር ብዛትን አይወስንም፡፡

• በሀገሪቱ መሰረታዊ የመድኃኒት ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ወይም በብዛት የሚሰራጭ መድኃኒት በአባሪነት የሚከተት ገላጭ ጽሁፍ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ መሆን ያለበት ሆኖ ምርቱ በአንድ ክልል ውስጥ ብቻ የሚከፋፈል ከሆነ ገላጭ ጽሁፉ ቢያንስ በእንግሊዝኛ እና በክልሉ የስራ ቋንቋ ይሆናል፡፡

• ማንኛውም የመድኃኒት አምራች ወይም አስመጪ መድኃኒቱ ገበያ ላይ ከመዋሉ በፊት የመድኃኒቱን የችርቻሮ ዋጋ በሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ በምርቱ ማሸጊያ ላይ መለጠፍ አለበት ፡፡

• የመድኃኒት እና ህክምና መሳሪያ ገላጭ ጽሁፍ በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ፣ የመለያ ምልክት ስለማስቀመጥ እና የችርቻሮ ዋጋ ስለማስቀመጥ የሚደነግነው የአዋጁ አንቀጽ 53 ንዑስ-አንቀጽ (3)፣ 53 ንዑስ-አንቀጽ (5) እና 53 ንዑስ-አንቀጽ (7) ይህ አዋጅ ከጸደቀ ከአስራ ስምንት ወራቶች በኋላ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

~የትምባሆ እና ተያያዥ ምርቶች አስተዳደር፣

• የኤሌክትሮኒክ ኒኮቲን መስጫ መሳሪያን ወይም ሌላ ከሲጋራ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የቴክኖሎጂ ምርት ወደ ሀገር ውስጥ ለንግድ አላማ ማስገባት፣ ማምረት፣ ማከፋፈል፣ ለሽያጭ ማቅረብ ወይም መሸጥ የተከለከለ ነው፡፡

• ማንኛውም ሰው ከበር መልስ ባለ ለህዝብ ክፍት በሆነ ማንኛውም ቦታ፣ ከበር መልስ ባለ ማንኛውም የስራ ቦታ፣ በሁሉም የህዝብ መጓጓዣ እና በጋራ መኖሪያ ቤት ማንኛውም የጋራ መገልገያ ቦታ ላይ ማጨስ ወይም ትምባሆን መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

o ማጨስ ወይም ትምባሆን መጠቀም በተከለከለባቸው ከበር መልስ ባሉ ለህዝብ ክፍት በሆኑ ቦታዎች እና የስራ ቦታዎች በአስር ሜትር ዙሪያ ውስጥ ባለ መግቢያ በር፣ መስኮት ወይም አየር ወደ ውስጥ ሊያስገባ በሚችል ሌላ ቦታ ውስጥ ማጨስ የተከለከለ ነው፡፡

• እድሜው ከ21 ዓመት በታች ለሆነ ሰው የትምባሆ ምርትን መሸጥ ወይም ከ21 ዓመት በታች በሆነ ሰው እንዲሸጥ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

• በትምባሆ ኢንዱስትሪ አማካኝነት ለበጎ አድራጎት አላማ እና ለሌላ ማንኛውም ተያያዥ ተግባር የሚደረግ የገንዘብ ስጦታ ወይም የአይነት ድጋፍ የተከለከለ ነው፡፡

• ማንኛውም የትምባሆ ምርት የውጭ ማሸጊያ አስፈጻሚ አካሉ በሚያወጣው መስፈርት መሰረት እና በጊዜ ቀመር የሚቀያየር የጤና ማስጠንቀቂያ ጽሁፍ እና ባለቀለም ምስል በአንድ ላይ መያዝ አለበት፡፡

o አስፈጻሚ አካሉ የሚያወጣው መስፈርት የጤና ማስጠንቀቂያውን ለመክበብ የሚውለውን ቦታ ሳይጨምር በትምባሆ ምርቱ የውጭ ማሸጊያ በእያንዳንዱ የፊት እና የኋላ ገጽ ከ70% ያላነሰ ቦታ የሸፈነ መሆን አለበት፡፡

• በችርቻሮ ሱቆች ውስጥ ትምባሆ መቀመጥ ወይም መደርደር ያለበት ሸማቹ በቀጥታ በእጁ ሊያነሳው ወይም በአይኑ ሊመለከተው በማይችልበት ሁኔታ መሆን አለበት፡፡

• የትምባሆ ምርት የጤና ማስጠንቀቂያ መስፈርቶችን የሚመለከተው አንቀጽ 57 ንዑስ-አንቀጽ (1-3) ይህ አዋጅ ከጸደቀ ከአስራ ሁለት ወራቶች በኋላ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close