Connect with us

Africa

አማርኛና ጃንሆይ ተሞሸሩ | በሬሞንድ ኃይሉ

Published

on

አማርኛና ጃንሆይ ተሞሸሩ | በሬሞንድ ኃይሉ

አማርኛና ጃንሆይ ተሞሸሩ | ሬሞንድ ኃይሉ@DireTube 

በሰሞነኛው የአፍሪካ ህብረት ስበስባ ጠቅላይ ሚኒሰተር ዐቢይ አህመድ ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ወርቅነህ ገበየሁ ይልማን ደሬሳን ያስታውሱኝ ይዘዋል፡፡ ደግሞም የስካይ ላይት ሆቴሉ የእራት ግብዣ ከግምሽ ምዕተ አመት በፊት በጊሆን ሆቴል ከሆነው ጋር ተመሳስሎበኛል፡፡

1952 ዓ.ም የአፍሪካ ነጻ መንገስታት መሪዎች ሸገር ላይ ከትመው ስለ አህጉራዊ ድርጅት ምስረታ ሲነጋገሩ ቀዳማዊ ኃይሰስላሴ “አፍሪካ በነገድና በጎሳ ተከፋፍላ እሰከመቼ ትቀጥላለች ? በመለያየታችን ከተጎዳን አንድ መሆን ግዴታችን እይደለምን ?” የሚል ሀሳብን አንስተው ነበር፡፡ ነገርየው ከዛሬው የጠቅላይ ሚኒሰተር ዐቢይ አህመድ ለአፍሪካ ከመደመር ውጭ አመራጭ የላትም ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

 

ከግምሽ ምዕተ ዓመት በፊት የነበረው ይህ አጋጣሚ ሁለቱን መሪዎች የሚያመሳስለው ግን በንግግራቸው ብቻ አይደለም፡፡ በወቅቱ ንጉሱ ለአፍሪካ አቻዎቻቸው የዕራት ግብዣን አድርገው “ከሀገር መሪነት የዘለለ ወንድማዊ ፍቅር ይኑረን “የሚል መልዕክትን አስተላልፈዋል፡፡ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ይልማ ደሬሳ አሰተባባሪነት የተካሄደው የዕራት ግብዣ በጊዮን ሆቴል የተካሄደ ሲሆን በርካታ መሪዎችም ደስታቸውን የገለጹበት ነበር፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መገባዳጃም ታሪክ እራሱን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ለአፈሪካ አቻዎቻቸው የእራት ግብዣን አድረገዋል ፡፡

“ወደጅነታችን ከፖለቲካም ያለፈ ወንድማዊ ነውም” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ወርቅነህ ገበየሁም የአቶ ይልማን ምግባር ወርሰው አፍሪካዊ ወንድሞቻቸውን ሲያስተናግዱ አምሽተዋል፡፡ ወቅታዊው የአፍሪካ ህበረት ስብስባ በኢትዮጵያ ታሪክና ትውፊት የታጀበ ይመስላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከላይ ካነሳናቸው መገጣጠሞች ባለፈ ለኢትዮጵያዊው መሪ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የመታሰቢያ ሀውልት መቆሙ ተጠቃሽ ነው፡፡ አሰገራሚው ነገር ግን እሱ ብቻ አይደልም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ያነሱ የነበረው አማርኛን የአፈሪካውያን ቋንቋም የማድረግ ርዕይም ተሳክቷል ፡፡

ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያን ሁለት ነገሮችን የሚፈጥር ይመስላል፡፡ የመጀመሪውያው ከአፍሪካ ህበረት ጋር ያለንን ትስስር እንዲጎላ ያደረገዋል ፡፡ ሁለተኛው አማርኛ አለማቀፋዊ ቋንቋ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡ በእስካሁኑ የህበረቱ መንገድ ኢትዮጵያ ከምታገኘው ጥቅም ባለተናነሰ ብዙ መስዕዋትነትም ስትከፍል ቆይታለች፡፡

በየዓመቱ ለሚካሄደው ጉባዔም ለመሪዎች ማረፊያና ልዩ ልዩ ወጭዎችን ስትሸፍን ኑራለች፡፡ ይህም ሲሰላ የተገኘውን ጥቅም ያህል በርካታ ገንዘብ ስታወጣ እንደኖረች ያሳየናል፡፡ ይህ መስዕዋትነት ግን ይህ ነው በሚባል ጥቅም የተቃኘ አልነበረም፡፡ ከዚህ አንጻር የዘንድሮው ጉባዔ ኢትዮጵያ የህብረቱ መቀመጫ ብቻ ሳትሆን የህብረቱ በላቤት መሆኗንም ያስመሰከረ ነው፡፡

አፍሪካ ህብረት የሚገባ እንግዳ የቀዳማዊ ኃይለስላሴን ሀውልት ተመልክቶ አማርኛን ለመስማት ከታደለ ኢትዮጵያ በርግጥም የአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት መሆኗን ለመገንዘብ አፍታ አይፈጅበትም፡፡ ለዚህ ደግሞ ጠቅላይ መኒስትር ዐቢይ አህመድና መንግስታቸውን ማመስገን ያስፈልጋል፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close