Ethiopia
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ ምግብ እና ቁሳቁስ እየቀረበላቸው አይደለም

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ ምግብ እና ቁሳቁስ እየቀረበላቸው አይደለም
~ የተፈናቃይ ቁጥሩ 45ሺ 900 ደርሷል
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኙ ተፈናቃዮች በመንግስት በኩል በቂ ምግብ እና ቁሳቁስ እየቀረበላቸው አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡
በማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረ ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ የሰዎች ቁጥር 45ሺህ 900 ደርሷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 2ሺህ 700 ተፈናቃዮች ምንም እርዳታ ያልቀረበላቸው ናቸው፡፡
አብዘኛቹ ተፈናቃዮች በጭልጋ ቁጥር 1 ፣በጭልጋ ቁጥር 2 ፣ምዕራብ ደምቢያ፣ ምስራቅ ደምቢያ እና ላይ አርማጭሆ አካባቢ የተፈናቀሉት ናቸው፡፡
ተፈናቃዮቹ በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ከተማ አቅራቢያ እና በምዕራብ ደምቢያ ዓይምባ ቀበሌዎች ተጠልለው ይገኛሉ፡፡
ተፈናቃዮቹ ‹‹በአንድ ላይ ተሰብስበን በመገኘታችን ምክንያት ለተለያዮ በሽታዎች ተዳርገናል›› ብለዋል፡፡
የማዓከላዊ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ.ቤት ኃላፊ አቶ መንበሩ አውደው ተፈናቃዮች ያቀርቡት ጥያቄ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ጽህፈት ቤቱ ለአንድ ሰው በወር 15 ኪሎ ግራም ምግብ ለማከፋፈል ጥረት እያደረገ ነው፤ ግን ደግሞ የተፈናቃዮች ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመምጣቱ አስፈላጊውን ቁሳቁስ እና ምግብ ለማዳረስ መቸገራቸውን አስረድተዋል፡፡
እስከ አሁን ከ2ሺህ 500 ኩንታል በላይ ስንዴ እና 300 ሺህ ኩንታል አልሚ ምግብ መሰራጨቱን ገልጸዋል፡፡
የክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ክንዴ ችግሩን ለመቅረፍ በማዕከላዊ ጎንደር ከሚገኙት የእህል መጋዘኖች 200 ኩንታል እህል ለተጠቃሚዎች ለማድረስ እየተጓጓዘ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ከፌዴራል መንግስትም በተጠየቀው የድጋፍ እርዳታ 600 ኩንታል እህል እየተጓጓዘ ነው ብለዋል አቶ ከንዴ፡፡
ተጎጂዎች አስፈላጊውን የምግብ እና የቁሳቁስ እርዳታ እንዲያገኙ ከክልል እና ከፌዴራል መንግስት ድጋፍ መጠየቃቸወን አስታውቀዋል፡፡
(ምንጭ፡- አብመድ)
-
Ethiopia3 days ago
መንግሥት ሆይ… እባክህ ንቃ!
-
Art and Culture3 days ago
ተዋጽዖ | በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
-
Ethiopia3 days ago
ሲሾሙ በብቃቴ ሲወርዱ በጎሳዬ | በሬሞንድ ኃይሉ
-
Ethiopia5 days ago
የእሮመኛ ዘፋኙ ዳዲ ገላን ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ አለፈ
-
Ethiopia4 days ago
ለፈጣሪም፣ ለመንግስትም፣ ለራሱም የማይመች ሕዝብ – ከአብዱራህማን አህመዲን
-
Africa2 days ago
የወታደር ክፋቱ ስልጣን ላይ ከወጣ አልወርድም ማለቱ!
-
Ethiopia3 days ago
ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያ ጥይቶች በግለሰቦች ቤት ተያዙ
-
Ethiopia3 days ago
የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው መግለጫ ሰጡ