Connect with us

Ethiopia

“ማነው?” ሳይሆን ” ምን ይሰራል?” | በኪዳኔ መካሻ

Published

on

"ማነው?" ሳይሆን " ምን ይሰራል?" | በኪዳኔ መካሻ

“ማነው?” ሳይሆን ” ምን ይሰራል?” | በኪዳኔ መካሻ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሌክሳንደር አሰፋ በሀገረ አሜሪካ የኔቫዳ ግዛት ተወካይ ሆኖ ቃለ መሀላ መፈፀሙን ሰማን።

ከዛሬ 19 አመት በፊት በስደት ከኬንያ ወደ አሜሪካ የገባው አሌክሳንደር ለዚህ ደረጃ መብቃቱ፤ የኛ ብሔር ተኮር ፖለቲካ ላይ የሚያሽሟጥጥና ሰው እዚህ ደርሷል እናንተ ከጎጥ መውጣት መከራ ሆኖባችሁዋል የሚል መሰለኝ ።

በኛውማ ሀገር ተወልዶ፣ አድጎ ቤተብና ኑሮ በመሰረተበት ስፍራ ብሔሩ የሌላ በመሆኑ ቋንቋውን ባለመናገሩ፤ እንኳን አስተዳዳሪ ሊሆን እንደ ተራ ግለሰብ ለፍቶ ከሚኖርበት ሚፈናቀለው፣የሚሽማቀቀው፣ ባይተዋርነት ሚሰማው ስንቱ ነው?

በፌደራል መንግስት ደረጃ አንኳን ያሉ ሹማምንትን ብቃታቸውን፣ የትምህርት ዝግጅትና የህዝብ አገልጋይነታቸውን ከመመዘን ይልቅ ብሄራቸውን፣የብሔር የኮታ ምጣኔን፣ የፖለቲካ ዳራቸውን እያነሳን ምንተች፣ ምንብሰለሰል፣ ተጠራጥረን ሌላውንም ጥርጣሬ ውስጥ እያስገባን፤ የራሳችንን ብሔር ስልጣን እና ተጠቃሚነት ከሌላው የተሻለ ለማድረግ ምንፋለጥ ስንቶች ነን?

ከተሞቻችንን እንኳን የሚኖርባቸውን ህዝብ ከማየት ይልቅ ከሚገኙበት ክልል አንፃር እያሰብን አንድ ክልል ወይም አንድ ብሔር የበለጠ ተጠቃሚነት ሊኖረው ይገባል ብለን ምንሞግት ብዙ ነን እና ቤት ሳይሆን ሀገር ይቁጠረን።

ይሄ ቦታ የዚህ ክልል ነው፤ ይሄ ብሄር ክልልነት ይገባዋል፤ ይህ ወረዳ ልዩ ዞን ነው..የሚሉ ብዙ ጥያቄዎችስ በየአካባቢው የወጠሩንስ ለምንድን ነው?

ብዙዎቻችን እኮ ባሁኑ ጊዜ በቋሚነት ለመኖር እና ለመስራት ብቻ ሳይሆን ለጥቂት ቀናት ስራ እንኳን ካካባቢያችን ወጣ ማለት እየፈራን ነው፤ ድሮ የሌላውን አኗኗር፣ አካባቢ፣ ባህል ለማወቅ አጓግቶን ካደግንና ከኖርንባቸው አካባቢዎች ውጭ ያሉት ዩንቨርስቲዎች እኮ በየክልላችን እንመደብ፣የደህንነት ዋስትና የለንም የሚሉ ተማሪዎችን ብሎም መምህራንን በብዛት እያጋጠሟቸው ነው።

ለምን ይሆን? አዎ ፣ ፖለቲከኞቻችን የሚያራግቡት የማንነት ጥያቄ ሳይሆን የማንነት ችግር ሳይኖርብን አይቀርም። ፖለቲከኞቻችንም ያን እየቆሰቆሱ በማንደድ ስልጣናቸውን፣ ገንዘባቸውንና ተፅእኖ ፈጣሪነታቸውን ያበስሉበታል።

በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ ከተለያየ የአለማችን ክፍል ከሚገኙ የሰው ልጅ ዝርያዎች ቀደም ብለውም ሆነ በቅርቡ የሄዱት በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸው፣ በባህልና በቋንቋቸው ሀገሩን የሚያበለፅጉና የሚያሳድጉ እሴቶች እንዳላቸው ታውቆ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተከብረው፤በሕግ አግባብ በየደረጃው አልፈው ከዜግነት እስከ መሪነት ይደርሳሉ።ከሌላ የአለማችን ክፍል ብቻ ሳይሆን ከኢትዬጵያ፣ከሱማሊያና ከኬንያ የሄዱ ግለሰቦች ንብረት እና አስተማማኝ ነፃነት ብቻ ሳይሆን ስልጣን ጭምር አግኝተው እስከ መጨረሻው መንበር ይደርሳሉ።

እዚህ ደግሞ በተቃራኒው ስምህ እስከ ቅድመ አያትህ ለነገር ይቆጠራል፤ የቀደምት አያቶችህ ዘር ተቆጥሮ እከሌ የኛ እገሌ የነሱ ትባላለህ። ጎረቤትህ ቡና ከሚያጣጣህ ይልቅ ድምበር ጫፍ ላይ ያለው በብሔር ገመድ ተስቦ ቅርብህ ነኝ ይልሀል። አንተም ትሰማውና ሌላውን ሁሉ ትተህ ማንነትህ ያሳስብሀል።

ማን ነን ብለው በዘር በብሔር በቋንቋ ለመላቸው ቢያሳስቡህም የተወለድከው፣ ያደከው፣ የተማርከው፣በሁዋላም ሰርተህ የምትኖረው አግብተህ የምትወልደው እና እንዳደክበት ከምትመሰርተው ቤተሰብ የቅርብ ዘመዶችህ እና ወዳጆችህ የሚያውቁህ የሚወዱህ በግለሰነትህ መሆኑን ትረሳና የማንነት ጥያቄህን ታነሳለህ።እንደ ልጅ ፣እንደ ወንድም እንደ አባት እንደ ባል ፣እንደ አጎት፣ እንደ አያት ፣

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** ኢትዮጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

 

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close