Connect with us

Economy

ከንቲባው የጀመሩትን የጎዳና ልጆች የመታደግ ፕሮጀክት ብንደግፍ አዲስ አበባ የት በደረሰች?

Published

on

ከንቲባው የጀመሩትን የጎዳና ልጆች የመታደግ ፕሮጀክት ብንደግፍ አዲስ አበባ የት በደረሰች?

በሀሰተኛ ወሬ የከንቲባውን ቤት ኪራይ ወጪ ከማስላት ከንቲባው የጀመሩትን የጎዳና ልጆች የመታደግ ፕሮጀክት ብንደግፍ አዲስ አበባ የት በደረሰች? አዲስ አበባ እንኳን ተጠላልፈው ተደጋግፈውም ቶሎ አትቀና፤ እናም ተደጋግፈን እናቅናት፤ | ከስናፍቅሽ አዲስ

ከንቲባው የሰሞኑ አጀንዳ ናቸው፡፡ ብዙ ሲባሉ ኖረዋል፡፡ ንግሥት ዘውዲቱ ያላሰሩትን፣ ልጅ እያሱ ያልሞከሩትን፣ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ያላቆሙትን፣ ጓድ ሊቀመንበር የረሱትን አቶ መለስ ወንድ የሆነ ያሉት ጉዳይ የሆነው የእቴጌ ጣይቱ ሐውልት ኢንጅነር ታከለ ኡማ በተሾሙ በሦስት ወሩ ካላሰሩ ብሎ መጮህ ሲጀመር በሽታው ምልክቱ ታይቷል፡፡

ባልተረጋጋች ሀገር ምክንያት ፈላጊ ሰው የሚያጋጩ ቡድኖች አጀንዳ ፍለጋ በሚባትሉበት ሰዓት የእቴጌን መታሰቢያ አዲስ አበባ እናቁመው ብሎ ከመቶ ዓመት በኋላ ትኩስ መርዶ እንደሰማ ሰው መጩሁም ያስተዛዝባል፡፡

ዘር ለመቁጠሩስ ቢሆን ኦሮሞው ታከለ ኡማ ለእቴጌ ጣይቱ መች ሩቅ ሆነው? ታከለ ኡማ ያንንም አለፉ፤ በየምክንያቱ አንዳች ሀሜት የማያጡት ከንቲባ ገና በሹመታቸው ማግስት ለምን የአዲስ አበባ ልጅ አልተሾመም የሚሉ የክፍለ ሀገር ልጆች የተነሱባቸው ሰው ነበሩ፤ አንዱን ሲያልፉ አንዱ ሲተካ ውጥንቅጧ በወጣ ከተማ በማስረጃ መሞገት አንድ ነገር ሆኖ በሀሜት ሀገር ማዳረስ ዞሮ ሁሉንም የሚጎዳ መሆኑ አይቀርም፡፡

ሰሞኑን ከንቲባው “በወር 140 ሺህ ብር እየተከፈለላቸው የሚኖሩ ናቸው” ብለው የዘመቱ ሰዎች “የለም ሰውዬው በኪቤአድ ቤት የሚኖሩ ናቸው” የሚለው ሲነገር ደግሞ ሌላ ዘመቻ ከፍተዋል፡፡

የከንቲባው ቤት ኪራይ ሂሳብ ጉዳይ ደግሞ ከተጋኗል ወደ አንሷል ወርዶ ሌላ መነጋገሪያ ሆነ፡፡ መጀመሪያውኑ ለከተማዋ ርቆ የከተማዋ ተቆርቋሪ መምሰል ምን ያክል አሳሳች ሞጋች እንደሚያደርግ አይተናል፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ በኪቤአድ ቤት የሚኖሩ ሰዎች የተጋነነው የቤት ኪራይ ዋጋ ሁለት ሺ ብር ደርሶ እንደማያውቅ እየታወቀ ከንቲባው ሹመኛ በመሆናቸው ያገኙት የመንግስት ቤት 860 ብር የሚከፈልበት አግባብ አይደለም ይሄም ህገ ወጥ ነው ብሎ መዝመት ሌላው ጠብ ያለሽ በዳቦ ይመስለኛል፡፡

አዲስ አበባ መከራዋ ብዙ ነው፡፡ ውጥንቅጧን የወጣች ከተማ ናት፡፡ ከሰባ አምስት አመት በላይ መሬቷ ተዘርፎ ደሃዋ ተራቁቶ በልቶ ማደር ከቀን ወደ ቀን የሚከፋባት ሞላጫ የሚነግስባት ከተማ ሆናለች፡፡

ይህቺን ከተማ የሁላችንም ለማድረግ ከሚመራት መሪ ጋር አብረን መስራት ይኖርብናል፡፡ ችግር ካለ በማስረጃ መሞገት፣ እንዲታረም ማድረግ መጥፎ አይደለም፡፡ የከተማ ሰው የሰለጠነ ነው ካልን ሀሜት የሰለጠ ሰው ባህሪ አይደለም፡፡

ከንቲባው የጎዳና ልጆችን እታደጋለሁ ብለው ፕሮጀክት ይፋ ሲያደርጉ ቴዲ አፍሮ ከጎዳና ልጆች ጎን ለመቆም ቃሉን ሲያሰማ እንዴት እንዲህ ያለ ቅዱስ ሀሳብ እውን ይሆናል በሚል የተከፈተ ዘመቻ መስሎኛል፡፡

ስለ ከንቲባው የጎዳና ልጆች የሚታደግ ፕሮጀክት ግድ ሰጥቶን አልተከራከርንም፤ መሆን በሚገባው ዙሪያ ፕሮጀክቱን የሚደግፍ አቅጣጫ የሚሰጥ ሀሳብ አልሰነዘርንም፤ ይልቁንስ ዛሬም የቤት ኪራይ ዋጋው እያልን አሉባልታ መቀባበል ይዘናል፡፡

አዲስ አበባ ከከንቲባው ማንነት ያለፈ ብዙ ጉዳዮችን አንስተን ከንቲባዋን የምናነቃበት፣ ስራ እንዲሰራ የምንገፋበት፣ ለውጥ እንዲመጣ ሞተር የምንሆንበት ሰዓት ላይ ተጠላልፎ ለመውደቅ እዚህም እዚያም ትግል አየን፤ ይሄ ትግል ከተማዋን አይታደጋትም፡፡

አሉባልታውን ትተን በማስረጃ እንሞግት፣ ለለውጥ እንስራ፣ ከንቲባን መደገፍ ከተማን መታደግ ነው፡፡ ከንቲባ ሲያጠፋ ደግሞ በምክንያት ማረም ከተማን ማዘመን ነው፡፡ ወሬ ተሰርታ ባላለቀች ከተማ አንድ ከረጢት ሲሚንቶ አይሆንም፡፡ ወሬ በልቶ ማደር ባቃተው የከተማ ነዋሪ ኑሮ አንድ ምሳ ዕቃ ስንቅ መሆን አይችልም፡፡ እናም ስለአዲስ አበባ አንድ ሀሳብ እናስብ፤

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** ኢትዮጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close