Business
ሜቴክ ለአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት በየሳምንቱ የሚያስረክበው የአውቶቡስ ቁጥር 137 ደረሰ

የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን/ሜቴክ/ ከህዳር 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ 122 በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ የተመረቱ አውቶቡሶችን ለደንበኛው ማስረከቡ ይታወሳል።
ከዚህ በፊት ሳምንታዊ የምርት አማካይ ቁጥር 10 እስከ 13 የነበረ ሲሆን አሁን 15 ደርሷል። በዚህም ምክንያት ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም 15 አውቶቡሶች በማስረከብ ቁጥሩን 137 አድርሷል።
በቀጣይ ሳምንትም ከ15 በላይ እንደሚያስረክብ የሚጠበቅ ሲሆን ከየካቲት ወር ጀምሮ ሳምንታዊ የምርት መጠን 24 ያደርሳል።
ቀስ በቀስም በቀን 6 በማምረት የሳምንት ምርቱን 36 እናደርሳለን ያለው ኢንዱስትሪው የሠራተኛው ተነሳሽነትና ታታሪነት መጨመር፣ የማምረቻ መስመር መጨመርና የተቋሙ ባለሙያዎች አቅም ጨማሪ ማሽኖችን በሞዲፊኬሽን መስራት መቻላቸው ያስገኘው አቅም ለምርቱ መጨመር አስተዋፅኦ የነበረው መሆኑን ተቋሙ ገልፇል።
ወደፊት ለታቀዱ ምርት የመጨመር ዕቅዶች ደግሞ የብየዳ ባለሙያዎችን ከእህት ኢንዱስትሪዎች መጠቀምና ሁለት የነበረውን ፈረቃ ወደ ሶስት ማሳደግ ታሳቢ ተደርጓል ሲል ኮርፖሬሽኑ ገልጿለ።
-
Ethiopia3 days ago
መንግሥት ሆይ… እባክህ ንቃ!
-
Art and Culture3 days ago
ተዋጽዖ | በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
-
Ethiopia3 days ago
ሲሾሙ በብቃቴ ሲወርዱ በጎሳዬ | በሬሞንድ ኃይሉ
-
Ethiopia5 days ago
የእሮመኛ ዘፋኙ ዳዲ ገላን ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ አለፈ
-
Ethiopia4 days ago
ለፈጣሪም፣ ለመንግስትም፣ ለራሱም የማይመች ሕዝብ – ከአብዱራህማን አህመዲን
-
Africa2 days ago
የወታደር ክፋቱ ስልጣን ላይ ከወጣ አልወርድም ማለቱ!
-
Ethiopia3 days ago
ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያ ጥይቶች በግለሰቦች ቤት ተያዙ
-
Ethiopia3 days ago
የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው መግለጫ ሰጡ