Connect with us

Ethiopia

‹‹በምሁራን ስም ቡድንንና ሕዝብን የሚያሰደቡ ሚዲያዎች›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

Published

on

‹‹በምሁራን ስም ቡድንንና ሕዝብን የሚያሰደቡ ሚዲያዎች›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

‹‹በምሁራን ስም ቡድንንና ሕዝብን የሚያሰደቡ ሚዲያዎች›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

ጠቅላይሚኒስትሩ በፓርላማ ውሏቸው ለሁለተኛ ጊዜ አንጀቴን አርሰውታል፡፡ ከመጋቢት 24 ወዲህ ፓርላማ ላይ ባሳዩት ‹‹ፐርፎርማንስ›› እርክት ያልሁት ዛሬ ነው፡፡ በተለይ ሚዲያን በተመለከተ የተናገሩት ነገር ድንቅ ነበር፡፡ የዴሞክራሲ ጽንሰ-ሐሳብ ያልገባቸው፣ የሀገር ሰላምና ልማት የማያሳስባቸው፣ በጎሳና በብሔር የሚነዱ ሰዎች የሚዘውሯቸው፣ የጠብመንጃ ፖለቲካ ያልለቀቃቸው፣ ሌሊትና ቀን ቀረርቶና ሽለላ የሚያሰሙ ሚዲያዎች ባለፉት 10 ወራት ወይ ለመንግሥት አልጠቀሙ፣ ወይ ቆመናል ለሚሉት ብሔር አልሆኑ ሀገሩን የ3.2ሚሊዮን ስደተኛ ሀገር አደረጉት፡፡

ጠቅላይሚኒስትሩ ይሄንን በደንብ ተረድተውታል፡፡ ‹‹በምሁራን ስም ሰዎችን እያመጣ አንድን ቡድን ክልልና ሕዝብ ሲያሰድቡ የሚውሉ አሉ›› ሲሉ የተናገሩትም ለዚያ ነው፡፡ ሚዲያ አጀንዳ ቀርፆ ሲንቀሳቀስ እንጂ ቀለብ ሰፋሪዎቹ በሚያቀብሉት ልክ ሲያሸረግድና ሲነጠፍ የሚውል መሆን አልነበረበትም፡፡ ምስጋና ለብሔር ፖለቲካችንና ብስለት ለተነፈጉት ጋዜጠኞቻችን እንድሁም ጥላቻ ላወራቸው አለቆቻቸው ይሄው እርስበርሳችን የምንፈራራ ሆንን!!

ጠቅላይሚኒስትሩ እንዲህ አሉ …

‹‹ሚዲያው ሚናውን ረስቷል፤ ውጣ ታጠቅ፣ ተዋጋና ተኩስ የሚል ሆኗል፡፡ ፌስቡክ ምን አለ ሲል የሚውል ሆኗል፤ ማንን በማን ‹ምሁር› ላሰድብ ሲል የሚውል ሆኗል››

በእውነቱ ልክ ናቸው፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ ሚዲያ የፖሊሲ፣ የስትራቴጂ፣ የርዕዮተዓለምና የፖለቲካ አሰላለፍ ትንተና ሲሰራ አልነበረም፡፡ ፌስቡክ የፈጠረለትን ሴንሴሽናል አጀንዳ ሲያራግብ ውሎ የሚያመሽ ነበር፡፡ የክልሉም ሚዲያ ጠቅላይሚኒስትሩ እንዳሉት ‹‹ታጠቅ፣ ውረር፣ ጨብጠህ አምጣ፣ ራስህን ጠብቅ…››ወዘተ በሚሉ ባለሥልጣናት ታጅቦ ይህንኑ ሲቀሰቅስ ነበር፡፡

ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት ጎራ ብዬ ነበር፡፡በቆይታዬም ከአብዮቱ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ ጋዜጦች (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ የካቲትና አዲስ ዘመን) ያወጧቸው የነበሩ ዘገባዎችን አገላበጥሁ፡፡ ኡፍፍፍፍ !! በእውነት ያኔ ምንም ዓይነት ዘመናዊ ትምኅርት ያልተማሩ የዚያ ዘመን ጋዜጠኞች ከእኛ እኩል ጋዜጠኛ መባላቸው ያሳፍራል፡፡ ምንም የጋዜጠኝነት ት/ት ቤት በሌለበት ሀገር አገር አንቀጥቅጥ የልማትና የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ ፍትህና የአገር ሉዓላዊነት አጀንዳዎችን እንዴት ይጽፉ እንደነበር ያነበበኩት አፌን ይዤ ነው፡፡

የዚህ ዘመን ጋዜጠኖች ግን ወይ እውቀት የለን ወይ እውነት የለን፤ ብሄርን ተጠግተን፣ የፖለቲካ ቀለብ ሰፋሪዎችን ተጠልለን ኡኡኡ ስንል እንውላለን፡፡ ሕዝብን ለማናከስ ጃስ ስንል እንውላለን!!

ጠቅላይሚኒስትሩ ይህንን ነገር እንኳንም አወቁልን!! በቀጣይ የሀሳብ ክርክር ትተው ሕዝብን ለማባላት የሚቀሰቅሱ ሚዲያዎችን፣ ግለሰቦችንና እነዚህን ከኋላ ሆነው ያሰማሩ ባለሥልጣናትንና ፖለቲከኞችን የሚቀጣ ሕግ ይተገብራሉ/ያወጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** ኢትዮጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close