Business
ከአዋሽ ኮምቦልቻ -ወልዲያ ሀራ- ገበያ የባቡር መንገድ ስራ ፕሮጀክት የመጨረሻ የዋሻ ቁፋሮ ስራ ተጠናቀቀ

ከአዋሽ ኮምቦልቻ -ወልዲያ ሀራ- ገበያ የባቡር መንገድ ስራ ፕሮጀክት የመጨረሻ የዋሻ ቁፋሮ ስራ ተጠናቀቀ፡፡
• ፕሮጀክቱ በቀጣይ ዓመት ይጠናቀቃል
– ከአዋሽ ኮምቦልቻ የመጀመርያው ምዕራፍ 270 ኪሎ ሜትር የመንገድ ስራም ተጠናቋል
ከአዋሽ ኮምቦልቻ -ወልድያ ሀራ -ገበያ የባቡር መንገድ ስራ ፕሮጀክት 393 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተገነባ ይገኛል፡፡ የመጀመርያው ምዕራፍ ከአዋሽ ኮምቦልቻ 270 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡
ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ከኮምቦልቻ -ወልዲያ ሀራ -ገቢያ 122 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ከሚገነቡ 12 የዋሻ ቁፋሮዎች መካከልም የመጨረሻ የሆነው 1 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር ቁፋሮ ስራ መጠናቀቁንም የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አብዱል ከሪም ሙሀመድ ለአብመድ አስረድተዋል፡፡
የሁለተኛው ፕሮጀክት ምዕራፍ ዋና ዋና ስራዎች መከናወኑን የገለጹት ኢንጅነሩ አፈጻጸሙም 65 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል የባቡር ፕሮጀክቱ በ1 ነጥብ 7 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እየተገነባ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይህም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
ከአዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ- ሀራ- ገበያ የባቡር መንገድ ስራ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈጻጸሙ 85 በመቶ ደርሷል፡፡ ፕሮጀክቱን በመገንባት ላይ ያለው የቱርኩ ያፒ መርከዚ ነው፡፡ በቀጣይ 2012 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
-
Ethiopia3 days ago
መንግሥት ሆይ… እባክህ ንቃ!
-
Art and Culture3 days ago
ተዋጽዖ | በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
-
Ethiopia3 days ago
ሲሾሙ በብቃቴ ሲወርዱ በጎሳዬ | በሬሞንድ ኃይሉ
-
Ethiopia5 days ago
የእሮመኛ ዘፋኙ ዳዲ ገላን ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ አለፈ
-
Ethiopia4 days ago
ለፈጣሪም፣ ለመንግስትም፣ ለራሱም የማይመች ሕዝብ – ከአብዱራህማን አህመዲን
-
Africa2 days ago
የወታደር ክፋቱ ስልጣን ላይ ከወጣ አልወርድም ማለቱ!
-
Ethiopia3 days ago
ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያ ጥይቶች በግለሰቦች ቤት ተያዙ
-
Ethiopia3 days ago
የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው መግለጫ ሰጡ