Connect with us

Art and Culture

የበውቀቱ ስዩም ምክር

Published

on

የበውቀቱ ስዩም ምክር | ከበኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

የበውቀቱ ስዩም ምክር | ከበኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

በእውቀቱ ስዩም ሰሞኑን በፌስቡኩ ላይ እንደወትሮው እያዋዛ ሆምጣጣ ሀቅ አስፍሯል፡፡ ‹‹የሚያጀግነውን የሚያውቅ ሕዝብ የተባረከ ነው›› የሚል ርዕስ በሰጠው ጽሁፉ ላይ የማይነጥፍ ቁምነገር ለግሶናል፡፡ በውቀቱ እንደሚለው ኢትዮጵያውያን ከአባቶቻችን የወረሰነው ቤተእምነት እንጂ፣ ቤተሙከራ ስላላወረሱን፣ አገሩ የሳይንስና ምርምር ምድረበዳ ሆኗል፡፡ እናም ለሳይንስ አስተዋጽኦ ያደረጉ ጥቂት ሰዎች ቢኖሩንም እውቅና የምንሰጠውና ሀውልት የምናቆመው ለጦርሜዳ ሰዎች ነው፡፡
የእርሱን አገላለጽ እንደወረደ ልጥቀሰው፤

‹‹በድሃ አቅማችን ወደ ጨረቃ መንኮራኩር ለመላክ ብናስብ ቅብጠት ይሆናል፡፡ ወደ ጨረቃ ዞሮ መሽናት ቂጥኝ ያስይዛል ብሎ የሚያምን ትውልድ እንዳይኖር ለማድረግ ራሱ ብዙ ይቀረናል፡፡ ….የጋቢሳ እጄታ ጎዳና፣ የአክሉ መታሰቢያ አየር ማረፊያ፣ የተወልደ ገ/እግዚአብሔር ፓርክ ማየት እመኛለሁ፡፡ አገርን ከዳር ድንበር ጠላት የሚከላከል ብቻ ሳይሆን ከጠንቀኛ ባክቴሪያና ቫይረስ የሚከላከለንን ማጀገን ያስፈልጋል፤…በአገራችን ከጥንት እስከዛሬ የጀግንነት ትርጓሜ ከጦርነት አልወጣም›› ይልና አንድ ጥልቅ ጥያቄ ጠይቆ ያጠናቅቃል፡፡

ይህ‹‹ምናልባት የጀግንነት ትርጓሜ ስንቀይር፣ ያለንበት ሁኔታ ይቀየር ይሆን›› ብሎ በጥያቄ ያለው የበውቀቱ ጽሁፍ ጎምዛዛ እውነት አዝሏል፡፡

በርግጥም በውቀቱ እውነቱን ነው፡፡ እኛ ሀገር ጀግና ሰው ገዳይ ብቻ ነው፡፡ ሽለላና ቀረርቶውም
‹‹ገዳይ እወዳለሁ ተኳሽም አልጠላ
ሲደክመኝ አርፋለሁ ከጎፈሬው ጥላ›› የሚል ነው፡፡

ሰውን የሚያህል ፍጡርን መግደልን እንደ ትልቅ ጅበዱ የሚያይ ሕዝብ ከሳይንስ ይልቅ ጥንቆላ፣ ከጥናት ይልቅ አስማት፣ ከምርምር ይልቅ አሉባልታ ይገዛዋል/ያሳምነዋል፡፡

ይህ አላንስ ብሎት አሁን ደግሞ የጦርሜዳ ጀግኖችን መናጠቅ ላይ ወድቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ እያለን በአንድ ጥናታዊ መድረክ ላይ ‹‹በላይ ዘለቀ ወሎዬ ነው›› የሚል ይዘት ያለው ምርምር ያቀረቡ አንድ ምሁር፣ በዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተማሪዎች የቀረበባቸው ውግዘት አይረሳኝም፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ደግሞ፣‹‹በላይ ዘለቀማ ኦሮሞ ነው›› ማለታቸው ምን ያህል እንዳሰደባቸው እኛ የፌስቡክ ታዳሚያን አንረሳውም፡፡

ይሁን እንጂ ፕሮፌሰር ጋዲሳ እጄታን ከክልላቸው ውጭ ለሲምፖዚየምም ሆነ ለሽልማት ጠርቶ እውቅና የሰጠ ተቋም የለም፤ ሳይንቲስት ተወልደ ገ/እግዚአብሔር የሰሩት ሥራ ምን እንደሆነ እንኳ ይህንን ጽሁፍ ከምናነብ ሰዎች ምን ያህሎቻችን እንደምናውቅ እንጃ!… ዘፋኞቻችንና ደራሲዎቻችንም ዋነኛ ትኩረታቸው የሣይንስና የፈጠራ ሰዎችን ማጀገን አይደለም፡፡

ዋነኛ ጉዳያቸው የጦርሜዳ ሰዎችን ማሞገስና ማወደስ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ሰዎችን ለማድነቅና ለመዘከር ራሱ ሳይንሳዊ መሆን ይጠይቃል፡፡

ቶማስ ኤዲሰንም ሆነ አይዛክ ኒውተን፣ አንስታይንም ሆነ ጋሊሊ ኢትዮጵያዊ አለመሆናቸው በጃቸው!!

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close