Connect with us

Africa

የጸደዩ አብዮትና ኢትዮጵያ | ከሬሞንድ ኃይሉ

Published

on

የጸደዩ አብዮትና ኢትዮጵያ | ከሬሞንድ ኃይሉ

የጸደዩ አብዮትና ኢትዮጵያ | ከሬሞንድ ኃይሉ

ትናንት በርከታ የዓለም መገናኛ ብዙኃን ስለቡአዚዝ ሲያወሩ ነበር፡፡ ቱንዚያዊው ቡዓዚዝ ከዓመታት በፊት በዚች ቀን አፋኝ ያለውን ስርዓት በመቃወም እራሱን አቃጠለ፡፡ ቡዓዚዝ የሞተው ለኛም ነው ያሉ የሀገሬው ሰዎችም በቀናት ውስጥ መንግስታቸውን በመቃወም ከአደባባይ ተሰየሙ፡፡ መሪያቸውንም አወረዱ፡፡ የሰሜናዊ አፍሪካዊት ሀገር ገድል ወደ አረቡ ዓለም እንደ ሰደድ እሳት ተስፋፋ፡፡ ከሳዓውዲ አርቢያ እሰከ ኦማን ከግብጽ እሰከ ኪዌት ብሎም ሊቢያ ያሉ ወጣቶች አምባገነናዊ ስርዓትን በመቃወም መሪዎቻቸው ላይ አመጹ፡፡

የጸደይ አብዮት የሚል ስያሜ የተሰጠውና ምናብ በሚመስል መልኩ ትላላቆቹን መሪዎች ያንገዳገደው ብሎም የናደው ማዕበል ሆሲኒ ሙባረክን ከግብጽ ቤተ-መንግስት አሰናበተ፡፡ ጋዲፊም ጣራቸው ቢበዛም ከሞት ለማመልጥ አልታደሉም፡፡ ሸሽተው ከተደበቁበት ቦታ በደም ተጨማልቀው እስከሰወዲያኛው አሸለቡ፡፡ የሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት አምባገነን መሪዎች መውደቅ የአረቡን አለም በአዲስ ተስፋ ዋጀው፡፡ ግብጻዊያንም ሆነ የሊቢያ ህዝብ አመባገነን መሪዎቹን ሲያሰናብት ወደ ዴሞክራሲ እያመራ እንደነበር እርግጠኛ ነበረ፡፡

ነገር ግን ተስፋቸው በጊዜ ሂደት የሚለምልም ሳይሆን የሚጨፈገግ ሆነ፡፡ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ከሦስት ዓመት በፊት የጸደይ አብዮት መነሻ ከሆነው ቡዓዚዝ እናት ጋር ባደረገው ቆይታ የገለጸው እውነትም ይህንን ነው፡፡ “ልጄ የሞተው በታሪክ ውስጥ ዕርባና በሌለው ነገር ነው፡፡ ዛሬም ቱንዚያ የመሪ ለውጥ አደረገች እንጅ የኑሮ ውድነቱም ሆነ አምባገነናዊነቱ እንዳለ ነው “ይላሉ የቡዓዚዝ እናት፡፡

ሊቢያም ጋዳፊ ስታሰወገድ ዳግም የመወለድ ያህልን ሀሴት ብታደርግም የኋላ ሞቷን ግን ከመሞት አልዳነችም፡፡ ከሀገራቸው ተርፎ ለአፍሪካ ህብረት ርብጣ ገንዘብ የሚለግሱት ሙዕመር ጋዳፊ ሞት ለሊቢያም ሞት ሆነ፡፡ የአክራሪ ቡድኖች መፈንጫ ሁናም ከዓለማችን አደገኛ አከባቢዎች እንዷ ለመሆን በቃች፡፡ ሊቢያን በመግድል የተሳተፉት ፕሬዘዳንት ኦባማም የስልጣን ዘመናቸው ሲያበቃ የሚቆጨወት ነገር ምንድን ነው? ሲባሉ ሊቢያ ላይ የሰራሁት ነገር አሉ፡፡

ከጋዳፊ በላይ ምን ሊመጣብን ያሉት ሊቢያውያን ከዛም የባሰ ነገር እንዳለ ተረዱ፡፡ በመጨረሻም አባቱን ሲገድሉ ያሳደዱትን የጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አልስላም ከዕስር ለቀቁ፡፡ በጸጸት ውስጥ ሁነውም የአባቱን መንበር መረከብ ያለብት እሱ ብቻ ነው እስከማለት ደረሱ፡፡ ሊቢያም ከለ ጋዳፊ ልጅ ዳግም ሀገር አትሆንም አሉ፡፡ ግን በጦር አበጋዞች የተከፋፈለችው ሀገር አልሲላምን ወደ ስልጣን ለማምጣት የሚሆን የአፍታ ሰላም እንኳን ለማግኘት አልቻለችም፡፡ እናም አልችም የለችም ለማለት እንዳዳገት ከዛሬ ደጃፍ ተደረሰ፡፡

ሙባረክን የሸኙት ግብጻዊያንም ከጎረቤቶቻቸው የተሸሉ ቢሆንም ከጣር ግን አላመለጡም፡፡ በዚህ የተነሳም ከሙባራክ ቢለያዩም ዴሞክራሲ እንደ ሰማይ ርቋቸዋል፡፡ የሀገሬው ሰውም ከትናንት የባሰ የኑሮ ወድድነት ጋር ተናንቋል፡፡ ግብጽ በተዓመር ከመፍረስ ብትድንም ግማሽ አካሏ የሆነውን የሲና በርሃ ግን በሞት አፋፍ ላይ ይገኛል፡፡ በርግጥ የመንና ሶሪያን ላየ ሰው የግብጽ ሁኔታ ተመስገን የሚባል ቢሆንም የጸደይ አብዮት ግን ህመማቸው መሆኑ አያከራክርም፡፡

የአረቡ ዓለም “አብዮት” በሚሉት እንዲህ ያለ ትርምስ ውስጥ በሚነጉድ ስዓት በርካታ የእኛም ሀገር የህትመት ውጤቶች የጸደይ አብዮት ኢትዮጵያ መምጣት አለበት የሚል አስተያየትን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል፡፡ መስቀል አደባባይን እንደ ታህሪሪ አደባባይ፣ የጸደይ አብዮትን በኢትዮጵያ የሚሉ ርዕሶችን በጠቀምም ህዝቡ ወዳልተዘጋጀበት አብዮት እንዲገባ ገፋፍተዋል፡፡ በዚህ የተነሳሱ ወጣቶችም የቡአዚዝን ታሪክ ለመድገም ክብሪት እራሳቸው ላይ እስከመለኮስ ደርሰዋል፡፡ ይህ እውነት ዛሬ ላይ የተወሰኑ ጥያቄዎችን እንድናነሳ ይጋብዘናል፡፡

የጸደይ አብዮት በኢትዮጵያ ቢነሳ ዕጣ ፋንታችን ምን ይሆን ነበር? ሊቢያን ወይንስ ግብጽን? በጊዜውስ አብዮቱን ማን ሊመራው ይችል ነበር? የኢትዮጵያ ህዝብስ ለአብዮት ዝግጁ ነበር ወይ? ለውጥ ቢከተልስ ወደ ዴሞክራሲ ሊያሻግረን የሚችለው ኃይል ማን ይሆን ነበር?

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close