Ethiopia
“በትግራይ በአሁን ሰዓት ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው” አቶ ገብሩ አሥራት

የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ገብሩ አሥራት ወደትግራይ በሸሹ ከፍተኛ አመራሮች ምክንያት በአሁን ሰዓት በትግራይ ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ሆኗል አሉ፡፡
አቶ ገብሩ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት በአሁን ሰዓት የህወሓት ፖለቲከኞች በጠቅላላ ሸሽተው ትግራይ ላይ ተደብቀዋል፡፡ … ለምን ሸሹ የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ፣ እነዚህ ባለስልጣናት ሸሽተውም ዝም ብለው አልተቀመጡም፡፡ ህዝቡን እየቀሰቀሱት ነው፤ ለዚህ መሠረት የሚሆናቸው የፖለቲካ ድባብ ደግሞ ተፈጥሮላቸዋል፡፡
ለምሣሌ በብአዴን እና በተወሰኑ የአማራ ልሂቃን እየተነሳ ያለው የመሬት ማስመለስ የጦርነት ንግግሮች፣ ህዝቡን ለማወናበድ ተጨማሪ ስንቅ ሆኗቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የኤርትራ ፕሬዚዳንት ፉከራም አለ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በሙሉ ተደማምረው ፖለቲካዊ ሁኔታውን ቀይሮታል፡፡ ፖለቲካዊ ሁኔታው ስለተቀያየረና ህግ ለማስከበር አመቺ ባለመሆኑ ነው፣ እነዚህ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ያልተያዙት፡፡
በትግራይ የተደበቁ ፖለቲከኞች፤ በየቦታው ትግራይን አስመልክቶ የሚነገሩትን ነገሮች ፍርሃት መፍጠሪያ እያደረጓቸው ነው፡፡ ህዝቡን 360 ድግሪ ተከበሃል እያሉ እያስጨነቁት ነው ብሏል፡፡
የህወሓት ባለስልጣኖች ይሄን ሁሉ ጥፋት አጥፍተው ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ በሸሹበት ወቅት በመጀመሪያ ወጣቱና ህዝቡ ቁጣ ነበረው ያሉት አቶ ገብሩ ለምን መጣችሁ? ይሄን ሁሉ ጥፋት አጥፍታችሁ፣ የኛ መሬት መደበቂያ አይሆንም ብሏቸው ነበር። ኋላ ላይ ግን በግዛት ይገባኛል ሰበብ በትግራይ ላይ የሚፈጽሙት ነገሮች፣ የትግራይ ተወላጆች ንብረት መዘረፍና መፈናቀል ጉዳይን እነዚህ ሃይሎች ለራሳቸው የፖለቲካ አላማ ተጠቅመውበታል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም “ለህወሓት ወይም ለኢህአዴግ ስልጣን መራዘም ተብሎ፣ ህዝቡ ጦርነት ውስጥ መግባት የለበትም፡፡ አሁን ህዝቡን በተለያየ አቅጣጫ እያስፈራሩ በስልጣን ለመቆየት ነው፣ ሁሉም ሃይሎች እየተንቀሳቀሱ ያሉት፡፡ ህወሓት በስልጣን ለመቆየት ህዝቡን በዚህ መልኩ እያዘጋጀ ነው፡፡ በሌላ በኩል እነ ብአዴንም በስልጣን ለመቆየት ሲሉ ህዝቡን ባልሆነ መንገድ እየቀሰቀሱት ነው፡፡ ይሄ ሁኔታ በሁሉም ወገኖች መቆም አለበት፡፡ ህዝብ ወደ ጦርነት መገፋት የለበትም፡፡” ብለዋል፡፡
አቶ ገብሩ አሥራት እንደመፍትሔ ያስቀመጡት ሃሳብ መደራደርን ነው፡፡ “ሀገርን በእልህ ለማፍረስ ከመጣደፍ፣ መንግስት በሆደ ሰፊነት መደራደር አለበት፡፡ እንኳን ከሀገር ውስጥ ፓርቲዎች ይቅርና ከሻዕቢያ ጋርም ተደራድሯል፡፡ በእልህና በመገፋፋት ማንም አሸናፊ አይሆንም፡፡ መደራደር ደግሞ የሽንፈት ምልክት አይደለም፡፡ ድርድር ስል ግን የህዝቡን የለውጥ ፍላጐት የሚቀለብስ መሆን የለበትም፡፡ የህዝቡ የለውጥ ፍላጐት በምንም መመዘኛ ለድርድር መቅረብ የለበትም፡፡ ኢህአዴግ እርስ በእርሱ ከሚያደርገው ድርድር በተጨማሪ ከሌሎች ሀገር አቀፍ ፓርቲዎችም ጋር መደራደር አለበት፡፡ የዚህችን ሀገር ችግር ለብቻዬ እፈታለሁ ቢል የሚሆን አይደለም” ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
-
Ethiopia3 days ago
መንግሥት ሆይ… እባክህ ንቃ!
-
Art and Culture3 days ago
ተዋጽዖ | በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
-
Ethiopia3 days ago
ሲሾሙ በብቃቴ ሲወርዱ በጎሳዬ | በሬሞንድ ኃይሉ
-
Ethiopia5 days ago
የእሮመኛ ዘፋኙ ዳዲ ገላን ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ አለፈ
-
Ethiopia4 days ago
ለፈጣሪም፣ ለመንግስትም፣ ለራሱም የማይመች ሕዝብ – ከአብዱራህማን አህመዲን
-
Africa2 days ago
የወታደር ክፋቱ ስልጣን ላይ ከወጣ አልወርድም ማለቱ!
-
Ethiopia3 days ago
ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያ ጥይቶች በግለሰቦች ቤት ተያዙ
-
Ethiopia3 days ago
የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው መግለጫ ሰጡ