Connect with us

Education

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ሽረ ናቸው

Published

on

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ሽረ ናቸው

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ሽረ ናቸው

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እና የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሽረ እንዳስላሴ ለሚገነባ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ሽረ ገብተዋል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ በቀዳማዊት እመቤቷ ፅ/ቤት 20 ሚልየን ብር ወጪ ተደርጎበት የሚገነባ ሲሆን ሙሉ ግንባታውም በሁለት አመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የፋና ዘገባ ያስረዳል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ቢሮ የስድስት ወራት ጉዞ

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ወደ ስራ ገበታቸው ከመጡ የስድስት ወራት ጊዜን ያገባደዱ ሲሆን በዚህም ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ የተከናወኑ ተግባራት በአጭሩ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

• 20 ከፍተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በሁሉም ክልሎች ለመስራት ታቅዶ የነበረ ሲሆን ይህንንም በማስመልከት ከአራት የክልል ማለትም ከአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ እና የደቡብ ክልል ትምሕርት ቢሮዎች ጋር ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ለስራውም የሚውለውም ፈንድ ለሚመለከታቸው አካላት የተላለፈ ሲሆን ግንባታውን ለመጀመር በሶስት ወረዳዎች የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በደሴ ከተማ ጦሳ ፈላና ዞን የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት፣ በጎደር ከተማ ሎዛ ማርያም አካባቢ የሎዛ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሊበን ጬቃላ ወረዳዎች የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠባቸው ናቸው፡፡

• በአዲስ አበባ፣ አልፋ መስማት የተሳናቸውን ትምሕርት ቤት፣ የቀጨኔ የሕጻናት ማሳደጊያ፣ የአማኑኤል የዓዕምሮ ሕክምና ሆስፒታልን እንዲሁም የካትሪን ሃምሊን የፊስቱላ ሕክምና ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

• በተጨማሪም፣ በዚሁ አዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አራት የመንግስት ትምሕርት ቤቶች ተዘዋውረው የሕጻናት ተማሪዎችን የምግብ ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡

• በባህርዳርና ጎንደር ከተሞች አይነ ስውራን ተማሪዎችን በጎበኙበት ወቅት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፤

• የአሸንዳን ክብረ ባዕል በማስመልከት በመቀሌ ከተማ ተገኝተው የባዕሉ ተካፋይ ሆነዋል፡፡

• የዘመን መለወጫን ባዕልንም ምክንያት በማደረግ በመስከረም 1፣ 2011 ዓ.ም. በብሔራዊ ቤተመንግሰት ከተለያዩ የሕጻናት ማሳደጊያዎች ለመጡ 400 ሕጻናት የምሳ ግብዣ በማዘጋጀት የበዓል ምሳ ጋብዘዋል፡፡

በውጭ ሀገራት የተደረጉ የስራ ጉብኝቶች

• በህንድ ሀገር፣ የአካል ጉዳት ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ለማገዝ የሚደረግን ጥረት ለመጎብኘትና የሚጠቅሙ ልምድ ለመውሰድ ወደ ህንድ አቅንተዋል፡፡

• በተባበሪት መንግስታት የምግብ ፕሮገራም እና ዓለምአቀፍ የምግብ ፖሊሲ ጥናት ተቋም ትብብር አዘጋጅነት “Accelerating the End of Hunger and Malnutrition” በሚል ርዕስ ታይላንድ በተካሄደው ዓለም ዓቀፍ ኮነፈረንስ ላይ ተገኝተው በፕሮግራሙ የተሳተፉ ሲሆን በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

✔ የገቢ ምንጮችን ማጎልበት

• ቢል ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር የነበረውን ውል አድሶ ማስቀጠል

• እየሩሳሌም የልማት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን በባሕርዳር ከተማና አካላይ ከተሞች የሚገኙ ሴተኛ አዳሪዎችን መልሶ የማቋቋምና አቅምን የማጎልበት ስራ ላይ ያተኮረ የስራ ዕቅድ ለስዊድን ኤምባሲ ለማስገባት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

• ከተለያዩ ከጽ/ቤቱ ጋር ለመስራት ፍላጎት የሚያሳዩ አካላት የሚያቀርቧቸውን የተለያዩ የስራ ዕቅዶችን መገምገምና ማጽደቅ

• በተለዩት የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ የስራ ዕቅዶችን እየነደፉ ተባባሪ አካላትን መጋበዝ

✔ ከተለያዩ አካላት ጋር የተደረጉ የስራ ትብብሮችና ወደፊት የሚከናወኑ ተግባራት

• የእስራኤል ኤምባሲ

• የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

• ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

• ከኢትዮጵያ ሳይካትሪ/ ሳይኮሎጂ ማሕበር፣

• የኢትዮጲያ አርክቴክትቶች ማሕበር፣ እና

• ከልዩ ኦሎምፒክ መስራች ኮሚቴ ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት፤

 

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close