Connect with us

Ethiopia

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዜግነት ፖለቲካ ፌርማታዎች 

Published

on

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዜግነት ፖለቲካ ፌርማታዎች  | ሬሞንድ ኃይሉ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዜግነት ፖለቲካ ፌርማታዎች  | በሬሞንድ ኃይሉ

ኢትዮጵያ የዜግነት ፖለቲካን ዳግም ከጀመረች አስር ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመጀመሪያው የፓርላማ ውሏቸው ” ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን” ብለው ብሄር ዘለል ፖለቲካን ካወጁ አርባ ሳምንታት አለፈዋል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የጎሳ መልክ የያዘውን የሀገረቱን ፖለቲካ ኢትዮጵያዊ ለማድረግ ያዋጣል ያሉትን ሁሉ ለማድረግ ጥረዋል፡፡ እንዲህ ያለው መንገደቻውም የተለያየ አስተያት እንዲሰነዘርባቸው አድርጓል፡፡

ከፊሉ ወገን ሀገር ከመሰረቱት ብሄሮች ይልቅ ኢትዮጵያን የማስበለጥ ፖለቲካ ከዚህ በፊት ተፈትነን የወደቅንበት ነው የሚል ትችት ሲሰነዝር የቀረው የብሄር ፖለቲካ ኢትዮጵያን ሊበትናት በመሆኑ ያለው ብቸኛ አማራጭ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንገድ ነው ሲል ይደመጣል፡፡ የእነዚህ ወገኖችን ሙግት ከሀገራችን የታሪክ ዕውነት አንጻር ከተመለከትነው ብዙ ሊያከራክር የሚችል ነው፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ጽሁፍ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ወራት የጀመረችውንና ወደፊትም እገፋበታለሁ የምትለውን የዜግነት ፖለቲካ ነጥሎ የት ያደርሰናል ይላል፡፡

የዜግነት ፖለቲካ በፖለቲካችን ውስጥ አዲስ አይደለም፡፡ ይህ ማላት ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሩት የዜግነት ፖለቲካ ሀሊዮት ዘልማዳዊ ነው ማለት አይደለም፡፡ ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶችን መጠቀስ ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው ኢትዮጵያ አሁን እሄድበታለሁ የምትለው የዜጋ ፖለቲካ በፌደራልዚም ስርዓት ውስጥ ያለ መሆኑ ነው፡፡ የሀገራችን ታሪክ እንደሚነግረን ነገስታቱም ይሁኑ ደርግ የዜጋ ፖለቲካን ለማራመድ የሞከሩት አሀዳዊ በሆነ ስርዓት ውስት ሁነው ነበር፡፡ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰብኩት የዜጋ ፖለቲካ ግን በፌደራላዊ ስርዐት ውስጥ የተፈጠረ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የራሱ መልካም አጋጣሚ እንዳለው ሁሉ ዕንቅፋቶችንም ያበዛል፡፡

በዚህ በኩል የሚጠቀሰው የመጀመሪያው ተግዳሮት ከፌደራሊዝም የመንግስት ስርዓት ባህሪ የሚመነጭ ነው፡፡ ፌደራሊዝም በአንድ ሀገር ሁለት መንግስት እንዲኖር የሚፈቅድ ስርዓት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የዜግነት ፖለቲካን ከክልላዊ ፖለቲካ ቀጥሎ እንዲነሳ ያደርገዋል፡፡ በተለይም አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ባልፈጠረ ሀገር ውስጥ እንዲህ ያለው ችግር ጎልቶ ይሰተዋላል፡፡ በመሆኑም ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ውህደትን ባላመጣች ሀገር ውስጥ የዜግነት ፖለቲካን ለስኬት ማብቃት አዳጋች ነው፡፡

ሁለተኛው የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በራሱ ከዜግነት ፖለቲካ ጋር ቁርሾ ያለበት መሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከሁለት አስርታት በላይ የብሄር ፖለቲካን ባስበለጠ የፌደራል ስርዓት ውስጥ ቆይታለች፡፡ በዚህ የተነሳም የብሄር ፖለቲካን ያነገቡ ኃይሎች መፈንጫ ሁናለች፡፡ ዛሬ ላይ ካሉት ከስልሳ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ አርባ ያህሉ የብሄር ፖለቲካ አራማጃ መሆናቸውም ለዚህ አብነት ነው፡፡

የእነዚህ ፓርቲዎች መብዛት ተወደደም ተጠላም የሚነግርን ሃቅ ኢትዮጵያ ለብሄር ፖለቲከኞች የተመቸች ሀገር መሆኗን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የዜጋ ፖለቲካን ለሚያስቀድሙ ወገኖች ዕረፍት የሚነሳ ጉዳይ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡

ከዚሀ በተጨማሪም የዛሬዋ ኢትዮጵያ ሀገራዊ መግባባትን የፈጠረች ሀገር አለመሆኗም የራሱን ስጋት በዜግነት ፖለቲካ ላይ ፈጥሮ ይስተዋላል፡፡ የእነዚህ ተግዳሮቶች መበራከትም የዜግነት ፖለቲካን ለሚናፍቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከባድ የቤት ስራን ፍጥሯል፡፡ ወቅታዊው ዕውነታው ይህ ቢሆንም የተጠቀሱት ስጋቶች ግን ዘላለማዊ አይደሉም፡፡ በዚህ ምክነያትም ቲም ለማ ለዜግነት ፖለቲካ የሚያመቹ መደላድሎችን መፍጠር ይችላል፡፡ ለእንዲህ ያለው ግብ መሳካት ደግሞ መንግስት አሁን የጀመረው ብሄራዊ ዕርቅን የመፍጠር ጉዳይ እንዱ ነው፡፡ ይህ ብሄራዊ እርቅ ግን ከፊሉን ወገን አስደስቶ የቀረውን የሚያስከፋ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡

አሁን ካለንበት የብሄር ፖለቲካ ሙሉ ለሙሉ ለመላቀቅ ከተፈለገ ግን አማራም ሆነ ኦሮሞው ሱማሌም ሆነ ትግራዩ ከብሄሩ በላቀ የሚተሳሰርበትን ሀገራዊ ባህል መግንባት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ባህል ደግሞ ካለኢኮኖሚ ዕድገት የሚታሰብ አይደለም፡፡ አውሮፓውያን ለየአከባቢያቸው ጠበቃ የነበሩ ዜጎቻቸውን ለሀገር እንዲጮኹ ማድረግ የቻሉት ኢንዱስትራላይዜሽናቸው ስኬታማ ሰለሆነ ነው፡፡

የእንግሊዝ አከባቢው ብሄርተኝነት የነጠፈው ፍብሪካዎች ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ከመንደራቸው ከፍ ብለው በፋብሪካ ውስጥ ስለሚከፈላቸው ደሞዝ መጨነቅ የጀመሩ ሰሞን ነው፡፡ ዘመናዊ የሚባለውን የዜጋ ፖለቲካ በእንግሊዝ ምድር በማራመድ አንጋፋ የሆነው ሌበር ፓርቲ ውልደትም ከዚህ የሚነጭ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የዜግነት ፖለቲካ የሚያስፈልጋት ሀገር መሆኑ ከሞላ ጎደል የሚያስማማ ሀቅ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄር ዘለለ ፖለቲካም እንዴት እውን ይሆናል የሚለው ካልሆነ ተቃውሞ የሚሰማበት አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ የዜግነት ፖለቲካን የሚናፍቀውን ህዝብ ከፍ ያደርገዋል፡፡ መሰረታዊው ጥያቄ ግን የዜግነት ፖለቲካ ስለተመኘነው እናገኘዋለን የሚለው ነው፡፡ መላሹ አይደለም የሚለው ይሆናል፡፡ እንዲህ ከሆነ ከብሄራችን የዘለለ የሚያስተሳስረንን መደላድል የማዘጋጀት የቤት ስራ በውሉ መስራት አለብን፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close