Connect with us

Ethiopia

ሀገር የሌለው ኢትዮጵያዊ ወታደር! | ሬሞንድ ኃይሉ

Published

on

ሀገር የሌለው ኢትዮጵያዊ ወታደር! | ሬሞንድ ኃይሉ

ሀገር የሌለው ኢትዮጵያዊ ወታደር! | ሬሞንድ ኃይሉ

ኢትዮጵያ ውስጥ መብትን የመጠየቂያ ብቸኛ መንገድ ወደህገ-ወጥነት አመዝኗል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአራቱም የሐገራችን ማዕዘን ማመጽ የመብት ያህል ተቆጥሯል፡፡ መንግስትም ህግ የማስከበር ሚናውን ከመወጣት ይልቅ ለህገ-ወጥ የጥያቄ መንገዶች መንበርከኩን ተያይዞታል፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታታ የነበሩትን ህገ-ወጥ ተግባራት እንደ ትግል መንገድ እንቁጠራቸው ብንል እንኳ ባለፉት ወራት እየተስተዋሉ ያሉ አለመረጋጋቶች ሀገሪቱ ከዚህ አይነቱ አዙሪት አለመውጣቷን ያሳያሉ፡፡

ከወራት በፊት የታላቋን ሱማሊያ ሰንደቅ ዓለማ ያነገቡ ወጣቶች ጅግጅጋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያወረዱ ሲቀይሩ ሀይ የሚላቸው አልነበረም፡፡ የሀገሪቱን ልዑአላዊነት በሚዳፈር ተግባራቸው ገፍተውበት የመከላክያ ስራዊት አባላት ላይ ድንጋይ እየወረወሩ የህግ-የበላይነትን ሲንዱም ጥቂት ህገ-ወጦች ከሚል የዳቦ ስም ውጭ የደረሰባቸው ነገር የለም፡፡

ከዚህ በኋላ አማራና ትግራይን በሚያዋስኑ የሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች መንገዶች ሲዘጉ መከላክያው ወደ ስፍራው አምርቶ ለማስከፈት ቢሞክርም ከቁብ የቆጠረው አልተገኘም፡፡ በዚህ የተነሳም የመከላክያ ሰራዊቱ አመራሮች ሽምግልና እስከመቀመጥ ደረሱ፡፡ በጊዜው ሰራዊቱ የአካቢውን ነዋሪዎች መማጸኑ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን ያሣል እየተባለ ቢሞገስም በህግ የበላይ ላይ እየተደራደረ እንደነበር ግን የነገረን አንድም አካል የለም፡፡

እናም የዚህ መንገድ መዳረሻችን የመከላክያ ሰራዊትን እኔ ያልኩህን ብቻ ታደርጋለህ ወደሚል ህዝባዊ እጅ ጥምዘዛ ከፍ እንዲል አደረገው፡፡ ከቀናት በፊት ፈጺ ከተማ ላይ የመከላክያ ከባድ ተሸከርካሪዎች እንዳይቀሳቀሱ ሲታገቱ የነገሩን አደገኝነት በመረዳት በህገ-አግባብ ከመፍታት ይለቅ ወደ ድርድር ተገባ፡፡ የዚህ አይነቱ የህግ-የበላይነትን ወዲያ ማሽቀንጠርም ዳንሻ ላይ የጦር ሄልኮፕተር እንድትታገት ምክንያት ሆነ፡፡ አየር ኃይልም እንደ ባዕድ ሀገር ተቋም እራሱን በመቁጠር የቴክኒክ ብልሽት ስለገጠመኝ ነው በሚል ተማጽኖ ንበረቱን አስለቀቀ፡፡

ትናንት ረፋድ ሽሬ ላይ የተፈጠረው ግን ከእስካሁኖችም የከፋው ህገ-ወጥ ተግባር ይመስላል፡፡ የኢትዮጵያን መከላክያ ሰራዊት ተሸከርካሪዎች እንደምርኮ ንብረት ላያቸው ላይ ወጥቶ መጨፈር መልዕክቱ ግልጽ ነው፡፡ ከሰራዊቱ ዕቅድ ውጭ ተሸከርካሪዎቹን ስታድዮም ውስጥ ማገት ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ህገ-ወጥነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት ሀገሩ ላይ በየትኛውም አከባቢ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ መፍቀድ ግዴታ እንጅ ምርጫ አይደለም፡፡ የፌደራል መከላክያ ሰራዊት ላይ ማመጽ በቁሙ ሲታይ የህግ-የበላይነትን መናድ ይሁን እንጅ መደምደሚያው ከፌዴሬሽኑ እራስን የማግለል ምልክት መሆኑ አያከራክርም፡፡ ይህ ደግሞ እጅግ አደገኛ ብቻ ሳይሆን የፌደራሉና የክልሉ መንግስት በፍጥነት ሊወያዩበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረጺዎን ገብረሚካዔል እንዲህ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ማውገዛቸው የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም ተጨባጭ ርምጃን ግን ሊወስዱ ይገባል፡፡ ለእርሳቸው አስተዳደር ተጠሪ የሆነው የክልሉ ፖሊሲም ህግ-የማስከበር ስራውን እንዲወጣ መደረግ አለበት፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ግን የመከላክያ ሰራዊቱ በእጁ መሳሪያ ስላለው እራሱ እርምጃ ይውሰድ ማለት በሚደርሰው ጉዳይ ህገ-ወጦች በርካታ ድጋፍ እንዲያገኙ መፍቀድ ነው፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close