Connect with us

Ethiopia

አስር የዶ/ር አብይ አህመድ ባህሪ ተብሎ ቢጠየቅ 99 ከመቶ ኢትዮጵያዊ ሌባ ጠል መኾናቸው …

Published

on

አስር የዶ/ር አብይ አህመድ ባህሪ ተብሎ ቢጠየቅ 99 ከመቶ ኢትዮጵያዊ ሌባ ጠል መኾናቸው ...

አስር የዶ/ር አብይ አህመድ ባህሪ ተብሎ ቢጠየቅ ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ ኢትዮጵያዊ ሌባ ጠል መኾናቸው ብሎ ይመልሳል፡፡

ጀግና መሳሪያ በታጠቀ አጃቢያቸው ፊት መሪውን ሌባ ብሎ የተሳደበ ሳይኾን ጀግና ሳይተኩስ ያለፈ ተሰዳቢ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ሲያልፍ ፊቱን ማየት ያስገድል እንደነበር የአዲስ አበባን ህዝብ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ዶክተር አብይን ግን አጃቢው ፊት ሌባ ብሎ መስደብ ይቻላል፡፡ *** ከስናፍቅሽ አዲስ

የሁመራ ኤርትራው መንገድ በይፋ ተከፍቷል፡፡ በልደት በዓል ተሰነይ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአማራና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮችን ይዘው ነበር የተጓዙት፡፡

ኦቦ ለማ መገርሳ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በዝግጅቱ ላይ አለመገኘታቸው በጭምጭምታ ተወርቷል፡፡ ከተሰነይ ኡምሃጅር የተደረገው የሁለቱ ሀገራት የልደት በዓል ኩነት የተከዜን ወንዝ ሪቫን ቆርጦ ተጠናቋል፡፡ ዝግጅቱ በብዙ መልኩ ሀገራዊ ጠቀሜታ ያለው ነበር፡፡

ለምሳሌ በዛላምበሳ ድንበር የተዘጋውን በር ምክንያት በማድረግ ጥያቄ ለሚያነሱ የህወሃት አክቲቪስቶች የህወሃቱ መሪ ሥርዓት ለማስያዝ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በሌላ በኩል በአማራና በትግራይ ክልል መሪዎች መካከል የታየው መግባባት የሚመስል ምልክት ያንዣበበውን የሁለቱን አካባቢዎች የጥላቻ ፖለቲካ ደመና ገፍፎ ወደ ጸሐይ ለመቀየር ተስፋ የሰጠ ነበር፡፡

አበቃለት የተባለው የቀጠናው ሰላምም እንዳላበቃለት ወዲ አፎም ትምህርት ሊሆን በሚችል መልኩ ምልክት ሰጥተዋል፡፡ ሁመራ ኤርትራ መንገድ ተከፍቷል፡፡

በአከፋፈቱ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደ ተራ ሰው የሚኖሩት አቶ ገዱ እና ጸረ ሌብነት መገለጫ በመሆን በኩራት የሚነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ሌባ ተብለው ተሰድበዋል፡፡

መቼም የቋንቋ ልዩነት ተፈጥሮ ትርጉም ተሳስተን ካልሆነ በስተቀር ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ህዝብ የዶክተር አብይን አስር ባህሪ ተናገር ቢባል በወል የሚስማማበት ሌባ ጠል መሆናቸውን ነው፡፡

ለሌላ ያለውን ጥላቻ በረድ ያድርጉት የሚባሉትን መሪ ሌባ ብሎ መስደብ በቅኔ የማሞገስን ያህል ተስማሚ ስም አድርገን ወስደነዋል፡፡ በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አመራር ዲሞክራሲያዊ መሆኑን ያሳየበት በዓልም ነበር፡፡

መለስ ዜናዊ ሲያልፍ ፊቱን ማየት ያስገድል እንደነበር የአዲስ አበባን ህዝብ መጠየቅ ይቻላል፡፡ መኪናህን ወደ ፊቱ አድርጎ መቆም መቻል አለመቻሉን ሲወጣ ሲገባ መኪና ይዞ ከወጣ ሰው መጠየቅ ይቻላል፡፡ ዶክተር አብይን ግን አጃቢው ፊት ሌባ ብሎ መስደብ ይቻላል፡፡

ይህቺን ኢትዮጵያ ለመስራት ብዙ ቄሮዎች ብዙ ፋኖዎች ብዙ ሞተዋል፡፡ ብዙ ዲያስፖራዎች ለስደት ኑሮ ተዳርገዋል፡፡ መሳካቱን እያየን ነው፡፡ ብዙ አክቲቪስቶች የተሳዳቢዎቹን ጀግነት ሲያወድሱ ሰምተናል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በተሰረቀ መሬት ላይ ቆሞ ሌባ ብሎ መሳደብ እያሉ ሲኮንኑ አድምጠናል፡፡ ከሁለቱም ሀሳብ የሚልቀው ግን የተሰዳቢው ጀግነት ነው፡፡

የታጠቀ ወታደርህ ፊት ስምህን እየጠራ ሌባ ሌባ የሚልን ተሳዳቢ አንድ ጥይት ሳይተኮስ ሰምቶ ማለፍ አፍሪካ ውስጥ መሆኑ ብቻ ጥቁርን ያኮራል፡፡ መግደል እየቻለ ተሰድቦ ያሸነፈ መሪ ነው ጀግና፤ አሁንም የጥላቻ ፖለቲካ ሩቅ አያስኬድም፡፡

የጥላቻ ፖለቲካ የጥቂት ክፉዎች እርሾ ነው፡፡ በምክንያቱ የሚጎዱት ግን ሚሊዮኖች ናቸው፡፡ ሰሞኑን የኤርትራ ድንበር እንቅስቃሴ ህግ የተከተለ ይሁን በሚለው ዙሪያ የተደከመውን ድካም አፈር የሚያስበላ ቅስቀሳ በትግራይ ቲቪና በድምጸ ወያነ ሲቀሰቀስ ነበር፡፡ ክፋት መስማት የማይሹት ወዲ አፎም ግን ሌላ ተአምር በሁመራ በኩል አሳይተዋል፡፡

በሁመራም፣ በዛላምበሳም ሆነ በራማና በቡሬ ህግን የተከተለ እንቅስቃሴ፣ የንግድ ግብይት፣ የመውጣት መግባት ሥርዓት ይከናወን ማለት ለሁለቱም ሀገራት የሚጠቀም ሀሳብ ነበር፡፡

ሀሳቡ ጤንኛ መሆኑን ዶክተር ደብረ ጽዮን ከሁመራ መልስ በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል፡፡ አሁንም ቢሆን ብዙ እሾሆች ይቀሩናል፡፡ ሀገር ጥለው ፈርጥጠው እሳት የሚለኮሱትን ትተን ህዝብ ጉያ ሆነው ህዝብ ካልተጫረሰ በሚል የኔ ወገን ጀግና ነው ዓይነት ቅስቀሳቸውን የቀጠሉ ሰዎች አሉ፤ የማንም ወገን ፈሪ አይደለም፡፡ የማንም ወገን ከራስ ወገን የሚለይ አይደለም፡፡ እኛ ሁላችን ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ ኢትዮጵያውያን፤ ሌባ መሪ የሌለን ኢትዮጵያውያን፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close