Connect with us

Ethiopia

ላሊበላ አይቀርም፤ ደብረ ሮሐ ካቀራችሁ-መርሐቤቴ ኦፍና አማኑኤል ሂዱ …

Published

on

ላሊበላ አይቀርም፤ ደብረ ሮሐ ካቀራችሁ-መርሐቤቴ ኦፍላ አማኑኤል ሂዱ ...

ላሊበላ አይቀርም፡፡ ደብረ ሮሐ ካቀራችሁ-መርሐቤቴ ኦፍና አማኑኤል ሂዱ 

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የልደትን በዓል ምክንያት በማድረግ በሀገራችን በተለየ ሁኔታ ወደሚከበርባቸው አካባቢዎች በምናብ ይዞን ሊጓዝ ነው፡፡ ላሊበላ አይቀርም፤ ላሊበላ ከቀራችሁ መርሐቤቱ ኦፍላ አማኑኤል ሂዱ ሲል አስደናቂዎቹን የገና በዓል አከባበሮች እንዲህ ይተርክልናል፡፡ |ሄኖክ ስዩም በድሬቲዮብ

የኢትዮጵያ እናቶች ወደላሊበላ የሚሄዱት ገናን ለማክበር ብቻ አይደለም፡፡ መንፈሳቸውን ለአንድ አመት ያድሳሉ፡፡ ደሳሳ ቤታቸው የማትሰለቻቸው የውቅር ተአምር ውስጥ አስቀድሰው ሲመጡ ነው፡፡ እናም በየዓመቱ ወደ ላስታ ይጓዛሉ፡፡

ተራሮች እንቅፋት አይኾኑም፡፡ የመንገድ ረዥም የለውም፤ መንገድ ወደ ላሊበላ ሲጓዙ አጭር ነው፡፡ ሲፈልጉ “አልጋ በአልጋ ነው መንገዱ ቅዱስ ላሊበላ ሲሄዱ” ሲሉ ምስጋናቸውን እያቀረቡ ኮረኮንቹን ዳገት ቁልቁለቱን የተነጠፈ መኝታ ኾነልኝ ሲሉ አቅልለው ይሻገሩታል፡፡ ደብረ ሮሐ አይቀርም፡፡

ዓለም እንኳን ከየጥጉ ዐለት ጉያ የተሸጎጠ፣ ምድር ከርስ ውስጥ የከተመ፣ ሽቅብ ጉኖ የሚያማልል የውቅር ጥበብ ሊመለከት ይመጣል፡፡ የላሊበላ ክብር ከቅዱሱ ድንቅ ስራዎች ብቻ የሚወጣ አይደለም፡፡ ዛሬም ካህናቱ በዚያ ታላቅ ስፍራ ታላቅ በኾነ ኢትዮጵያዊ ስልት አምልኮተ እግዚአብሔር ሥርዓትን በመንፈሳዊ ዜማ ሲያቀርቡ መመልከት ወደ ሰማይ የመውጣት ያኽል ነው፡፡

ልደት በላሊበላ እንዲኽ ተብሎ የሚገለጽ ቃል አይደለም፡፡ ራሱ ቅዱስ ላሊበላ የተወለደው በዚህ ቀን ነው፡፡ ደብረ ሮሐ ሁለት ልደት ታከብራለች፡፡ ነፍሱ ፈጣሪውን አክብራ በድንጋይ ምሰሶ ድንጋይ ያቆመውን ቅዱስ ላሊበላ እና ለሰው ልጅ ሁሉ ቤዛ ኾኖ የመጣውን የክርስቶስን ልደት፡፡ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በኮኮብ ተመርተው ሊሰግዱ ከሄዱት የጥበብ ሰዎች አንዱ ኢትዮጵያዊ ነው ይላሉ፡፡

ኢትዮጵያን ስለ ክርስቶስ መወለድ ቀድመው የነገሯት ከዋክብት ናቸው፡፡ ከዚያ እጅ መንሻዋን ይዛ ወደ ቤተልሔም ሄደች፡፡ ብዙ ሺዎች ተራሮችን አልፈው ወንዞችን ተሻግረው የተከዜን በርሃ ሳይፈሩ፣ የበሽሎን ጉልበት ሳይሰጉ፣ የአባይ በርሃን ሰንጥቀው ቅዱስ ላሊበላ ሲሄዱ ኖረዋል፡፡

ልደትን በላሊበላ አለመኾን ይቆጫል፡፡ ላሊበላ መሄድ ያልቻለ ሰው ደግሞ እዚሁ አዲስ አበባ አቅራቢያ መርሐቤቴ እንዲሄድ እመክራለሁ፡፡ ኦፍና አማኑኤል ይባላል፡፡ መርሐቤቴ አለም ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ታሪካዊ ስፍራ ነው፡፡ አስቀድሞ አብርሃ ወ አጽበሐ እንደ መርጦ ለማርያም ድንቅ አድርገው ያነጹት የአራተኛው ክፍለ ዘመን አሻራ ነበር፡፡ ዛሬ ያ ፈራርሷል፡፡ ከፍርስራሹ ፋይዳ አላቸው የተባሉት በክብር ተቀምጠዋል፡፡

በስፍራው ዛሬም ኦፍና አማኑኤል ታንጾበታል፡፡ ኦፍና አማኑኤል የአማኑኤል በዓል በድምቀት ይከበርበታል፡፡ በማግስቱ ደግሞ የልደትን በዓል በድምቀት ያስተናግዳል፡፡ የካህናት የሩር መጫወቻዋ ለዘመናት በመቅደሱ የኖረች ቅርስ ናት፡፡

የገና ጨዋታውን ከነክብሩ ለማየት ብቸኛው ቦታ ነው፤፤ ባህላዊ ጨዋታው መንፈሳዊ ትርጉሞች ሲሰጡት መመልከትም ይችላል፡፡ እኛ ገናችንን እንዲህ ለሺ ዓመታት ስናከብረው ኖረናል፡፡ ገና ገና ብዙ ዘመን እንዲህ በኢትዮጵያዊ ወግ እየተከበረ ይቀጥላል፡፡ መልካም የልደት በዓል፤

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close