Connect with us

Business

ፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት /BRT/ ተስፋ

Published

on

ፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት /BRT/ ተስፋ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን ዘርፈ ብዙ የትራንስፖርት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ ተስፋ ከተጣለባቸው የብዙሃን ትራንስፖርት ዘርፎች አንዱ ፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት /BRT/ ነው፡፡

ፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት ፕሮጀክት በከተማዋ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ አዲስ ምዕራፍ በመክፈት ለብዙሃን ትራንስፖርት ተጨማሪ ስንቅ ይሆናል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ለብቻ በተለየለት የኮሪድር መንገድ በመጠቀም ህበረተሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደሚፈልግበት ቦታ በማጓጓዝ ፈጣን፣ አስተማማኝ፣ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡

በዚህም መሰረት ለከተማዋ በብዙሃን ትራንስፖርት እምርታ የማምጣት ተስፋ የተጣለበት የአገሪቱ የመጀመሪያው ፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት የBRT- B2 ፕሮጀክትን የተሳካ ለማድረግ የኮንትራት ማሻሻያው ጥር 14 ቀን 2010 ዓ.ም ተፈርሞ ወደስራ ተገብቷል፡፡

ፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት /BRT/ ተስፋ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን ዘርፈ ብዙ የትራንስፖርት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ ተስፋ ከተጣለባቸው የብዙሃን ትራንስፖርት ዘርፎች አንዱ ፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት /BRT/ ነው፡፡

 

ከፈረንሣይ የልማት ትብብር ኤጀንሲ በተገኘ 85 ሚሊዮን ዩሮ ብድርና ዕርዳታ፣ እንዲሁም በከተማው አስተዳደር በሚሸፈን 45 ሚሊዮን ዩሮ በጠቅላላው በ130 ሚሊዮን ዩሮ በጀት ግንባታው ይከናወናል፡፡ ከዊንጌት በፓስተር አድርጎ አውቶቡስ ተራን አቋርጦ በተክለ ሃይማኖት በኩል ሜክሲኮን ይዞ በቄራ ወደ ጆሞ መንደር የሚዘረጋውና 23 ጣቢያዎችን የሚያካትተው ይህ ፕሮጀክት፣ እንደ ቀላል ባቡር ፕሮጀክቱ ሁሉ በመንገድ መሀል ለመሀል የሚዘረጋ ነው፡፡ በዚህ ኮሪደር 18 ሜትርና 12 ሜትር ዝርመት ያላቸው 157 አውቶቡሶች የሚሰማሩበት ይሆናል፡፡

40 በመቶ የከተማዋ ነዋሪዎች የሚገኙባቸውን አምስት ክፍላተ ከተሞች የሚያካልለው ይህ የአውቶቡስ መስመር፣ በአንድ ሰዓትና በአንድ አቅጣጫ ብቻ 6,500 ተሳፋሪዎችን የማመላለስ አቅም ይኖረዋል፡፡

በሰባት ሜትር የመንገድ ስፋት በሁለት አቅጣጫ የሚገነባው ይህ የአውቶቡስ መስመር፣ ከመነሻ እስከ መድረሻ ለሚጓዙ፣ ፈጣን የኤክስፕረስ ተሳፋሪዎች፣ ወደ ሌሎች መንገዶች በመግባት የሚሰጡትን ጨምሮ ሌሎችም አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ ካርድ የታገዘ የብዙኃን አገልግሎት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡

በአንጻሩ የፕሮጀክቱን ዲዛይን ስራ ለማጠናቀቅ ከታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ ከ12 ወራት በላይ የዘገየ ሲሆን በየጊዜው በኮንትራቱ ላይ የሚነሱ የልዩነት ጥያቄዎችን በአፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የዝርዝር ዲዛይን ስራው በቀጣይ ሶስት ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ከዝርዝር ዲዛይን ሥራው ጎን ለጎን የግንባታ ተቋራጭ ለመቅጠር፣ ብሎም የአውቶቡሶች ግዥና የስማርት ሲስተም ግዥዎችን ለማካሄድ ጨረታ የሚወጣ ይሆናል፡፡

ከBRT- B2 ፕሮጀክት ትግበራ በተጨማሪ በተለያዩ የጊዜ ሰሌዳ ፈጣን አወቶቡስ አገልግሎት ኮሪደሮችን ለማልማት የታቀደ ሲሆን በ2009 በጀት ዓመት የተለያዩ ፋይናንስ አፈላላጊ ድርጅቶች በBRT ፕሮጀክቶች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት አሳይተዋል፡፡

በመሆኑም ለማከናወን ከታሰቡ የBRT ኮሪደሮች የተወሰኑትን ለማልማት ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል። በተጨማሪም የBRT- B3 ኮሪደርን AVIC International BJ ከተሰኘ ተቋም ጋር ፋይናንስ በማፈላለግ ለማልማት የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ ፕሮጀክቱን ወደስራ ለማስገባት ያለውን ትጋት የሚያስመሰክር ነው፡፡

እንዲሁም የ BRT- B1 እና BRT- B6 ኮሪደሮችን ለማልማት Bejing Urban Construction Company የተሰኘ ታዋቂ የቻይና የዲዛይን እና የኮንስትራክሽን ኩባንያ ገንዘብ ለማፈላለግና ለመገንባት ፍላጎቱን በደብዳቤ ማሳወቁ በዘርፉ ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር ለሚሰራው ስራ ያለውን እገዛ ያሳያል፡፡

የBRT- B4 እና B5 ኮሪደሮችንም ለማልማት Zhongmei Engineering Group LTD ከተባለ የገንዘብ አፈላላጊ ተቋም ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ በብዙሃን ትራንስፖርት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የትጋት ጥጉን ያስመሰክራል፡፡

በሌላ በኩል ለBRT- B7 ኮሪደር ከKorea Exim Bank ጋር በተደረገ ውይይትም 60 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እንዲመደብ ተወስኗል፡፡ ስለሆነም ለፕሮጀክቱ ስኬት የቅድመ አዋጭነት ጥናት ለማካሄድ የሚረዳ የፕሮጀክት ጽንሰ ሃሳብ በቡድኑ ተዘጋጅቶ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የተላከ ሲሆን ሚኒስቴሩም የአዋጭነት ስራው እንዲሰራ ለአበዳሪው ተቋም በደብዳቤ አሳውቋል፡፡

በቀጣይም በማስተር ፕላኑ የተለዩ ተጨማሪ ኮሪደሮች እንደ አስፈላጊነታቸው የሚካተቱ በመሆኑ በብዙሃን ትራንስፖርት ላይ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት የተስፋ ጎህ መፈንጠቁ ማሳያ ነው።

ምንጭ፦ በትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close