Connect with us

Ethiopia

አነጋጋሪው የሪፐብሊኩ ጥበቃ የሚዲያ ሽፋን

Published

on

አነጋጋሪው የሪፐብሊኩ ጥበቃ የሚዲያ ሽፋን | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

አነጋጋሪው የሪፐብሊኩ ጥበቃ የሚዲያ ሽፋን | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

ጉዳዩ ትናንት ጠዋት በፋና ቴሌቭዥን የቀጥታ ሽፋን አግኝቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ከቤተመንግሥቱ ሰዎች ይሁንታ አልተሰጠውም፡፡  በእለቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሰልጥነው የመጡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠባቂዎች ትርዒት ያቀርቡ ነበር፡፡

ትርዒቱ ወታደሮቹ በሥልጠናው ወቅት ያገኙትን የክህሎትና የኮማንዶ ሥልጠና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይና ለኤታማዦርሹሙ ጀኔራል ሳዕረ የቀረበ ነው፡፡ ሁነቱ በሥህተት ግማሽ ሰዓት ያህል የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ካገኘ በኋላ ተቋርጧል፡፡ ሆኖም ማታ ላይ በመንግሥት ቴሌቭዥኖች እንዲዘገብ ተደርጓል፡፡

የሆነው ሆኖ የጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ መምህር የነበሩት ጀኔራል ብርሃኑ የሚመሩት የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሚጠብቅ ጦር ተቋቁሟል፡፡ ይህ ጦር የአጋዚ ክፍለጦርን የሚተካ ሚና ያለው ልዩ ኮማንዶ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ዋነኛ ሥራውም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከነቤተሰቦቻቸው መጠበቅ ነው፡፡

ይህ ተግባር በውጭ ሀገራትም ሆነ በኢትዮጵያ ከአሁን በፊት የተለመደ ነው፡፡ ጃንሆይ የሚጠብቃቸው ጦር ነበራቸው፡፡ ክቡር ዘበኛ የሚል ሥም ነበረው፡፡ጀኔራል መንግሥቱ ነዋይ ይመሩት ነበር፡፡ ይህ ዘብ የሚቀላቀል ሰው መመዘነኛው ለንጉሱ ያለው ታማኝነት ነው፡፡ይሁን እንጂ በዚህ መልኩ ያቋቋሙት ጦር ከድቷቸው መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮባቸዋል፡፡ የክቡር ዘበኛ ሠራዊትም የጃንሆይና የቤተሰባቸው ጠባቂ ሆኖ እስከመጨረሻው ዘልቆ ነበር፡፡ ጥሩ የታጠቀና የሰለጠነ ቢሆንም ግን መጨረሻም ላይ ጃንሆይን በደርግ ከመፈንቀል አላዳናቸውም፡፡

ቀጥሎ የመጣው የመንግሥቱ ኃይለማርያም አገዛዝም ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጥ ሠራዊት አቁሞ ነበር፡፡ይህ ሠራዊት ከደርግ አባላት ውጭ የሆኑ ሰዎች ያሉበትና የደርግ አባል ባልነበሩት በኮሎኔል ዳኒኤል አስፋው የሚመራ ነበር፡፡ ቀጥተኛ ታዛዥነቱ ለመንግሥቱ ኃይለማርያም የነበረው ይሄ ጦር ‹‹ወታደራዊ ጥበቃ›› የሚል ሥያሜ ነበረው፡፡

ጦሩ ኮሎኔል መንግሥቱ ያሉትን የሚያደርግ ነው፡፡ እነ አክሊሉ ሀብተወልድን ጨምሮ 69 ሰዎችን የገደለው ይሄው ጦር ነበር፤ ጀኔራል አማን አምዶምን የረሸናቸው ይሄው ጦር ነው፡፡ ጀኔራል ተፈሪን፣ ሻምበል ሞገስን፣ ዓለማየሁ ኀይሌን፣ እነ ኅሩይን ጥር 26-1969 ሰብስቦ የገደላቸው ይሄው ጦር ነው፡፡ መንግሥ ኃ/ማርያምም፣ ‹‹ለምሳ ሲያስቡን ለቁርስ አደረግናቸው›› ብለው የፎከሩት ይሄ ጦር በሰራላቸው ገዲል ነበር፡፡

ሆኖም 1969 ጥር 26 (እነ ተፈሪ ከተገደሉ በኋላ) ሻለቃ ምትኩ የተባለ መኮንን ኮሎኔል ዳኒኤልን ከገደለው በኋላ ይህ ዘብ በሌሎች ሰዎች ሲመራ ቆይቷል፡፡ የተለየ እንክብካቤና ሥልጠና ስለሚሰጠውም፣ በተክለ ሰውነት የተሻሉ ወታሮች ነበሩት፡፡ ይህንን የተመለከቱ የአዲስ አበባ ሰዎችም ይህንን ሠራዊት ቅልብ ጦር የሚል ቅጽል ስም አውጥተውለት ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ የመጣው የኢሕአዴግ መንግሥትም ከመከላከያ የአጋዚ ክፍለ ጦር የተውጣጡ ወታደሮች የተዋቀሩበት ጦር ነበር፡፡ወታደሮቹ በውጭ ሀገር እና በሀገር ውስጥ የሰለጠኑ ታማኝነትም ያላቸው ነበሩ፡፡ እነዚህ ወታደሮችም አቶ መለስንና አቶ ኃ/ማርያምን ከነ ቤተሰቦቻቸው ሲጠብቁ ኖረዋል፡፡

አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይንና ቤሰቦቻቸውን የሚጠብቀው የአሁኑ ጦር ደግሞ የሪፐብሊኩ ጥበቃ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ጦሩ መግቢያዬ ላይ እንደጠቀስሁት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሰለጠነ መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡ ስያሜውም ከሌሎች ሀገራት የተወሰደ ነው፡፡ ለምሳሌ የጣሊያን መንግሥት ቁመታቸው ከ2.1 ሜትር የሚልቅን ወጣቶች ከመላ ሀገሪቱ አሰባስቦ አሰልጥኖ የሪፐብሊኩ ጋርድ አባል ያደርጋል፡፡ ኢራቅም በተመሳሳይ Republican Guard አላት፡ ፡በአሜሪካም ከሲአይኤም ከኤፍቢአይም ውጭ የሆነ ሰክሬት ሰርቪስ የተባለ ይህንኑ Republican Guard የሚተካ ጠባቂ ኃይል አለ፡፡ እናም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቋቋሙት ጥብቅ ጦር ከዓለም የተለየ አይደለም፡፡

ይልቅ ትልቁ ጉዳይ ይህ የሠለጠነን ጦር በቴሌቭዥን ማሳየት ተገቢ ነው ወይ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ዋነኛ ተልዕኮው ፕሬዚዳንቱንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከነቤተሰቦቻቸው መጠበቅ የሆነን ጦር አጠባበቁንና አሰለጣጠኑን በቴሌቭዥን ማሳየት ለጠላት አማራጭ እንዲፈልግ ምክር የሚሰጥ አይሆንም ወይ፤ የጥበቃ ዝግጁነቱንና አቅሙን በዚህ ደረጃ ማሳየትስ ተጠባቂዎቹን አደጋ ውስጥ አይከትትም ወይ፤ በእያንዳንዱ ማኅበረሰብ የእለት ከእለት ውሎ ላይ ተጽእኖ ያለው ይመስልስ በቴሌቭዥን ማሳየት ምን ትርጉም ይሰጣል፤ ሁለተኛ ለወታደሮቹ ማኅበራዊ ሕይወትስ መታሰብ አልነበረበትም ወይ፤ ከዚያ ቀጥሎስ ጠባቂዎቹን ማንነታቸውን ማሳየት ተገቢ ነው ወይ የሚለው ጉዳይ ያልተብራራ ጥያቄ ነው፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** ኢትዮጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close