Connect with us

Ethiopia

ያሸነፍነው ኤች አይ ቪ ኤድስ ሊያሸንፈን እየታገለ ነው

Published

on

ያሸነፍነው ኤች አይ ቪ ኤድስ ሊያሸንፈን እየታገለ ነው

ያሸነፍነው ኤች አይ ቪ ኤድስ ሊያሸንፈን እየታገለ ነው፡፡ ዱከም የዓለም ኤድስ ቀን ተከብሮባታል፡፡ ረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ የልማት ኮሪደር ሰራተኞች የስርጭት መጠኑ የጨመረባቸው አካባቢዎች ቤተሰብ ናቸው፡፡ ***

ኤች አይ ቪ የአፍሪካ ችግር በነበረበት መጥፎ ጊዜ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከባድ ጉዳት ደርሶብናል፡፡ እያንዳንዱን ቤት ያንኳኳ ስቃይና ሀዘን አስተናግደናል፡፡ የበሽታው ጠባይ ሳይንስ በቅጡ እንዲህ ነው ሳይለው ባለማወቅ ብዙ ችግር አስተናግደናል፡፡

በአጭር ጊዜ የምንወዳቸውን አጥተናል፡፡ አምራችና የተማረው ሃይል አልቆ ሀገር ከባድ ችግር ውስጥ ገብታ ነበር፡፡ ወላጅ ያጡ ህጻናት ቁጥር በቀላሉ የሚቆጠርም አልነበረም፡፡ በማግለልና ለመከላከል የሚያስፈልግን ግንዛቤ ባለማወቅ የገባንበት ፈተና ለዓመታት ሀገራችንን ፈትኗታል፡፡ ያም ሆኖ የማይናቅ ስራ ተሰራ፡፡ ከያኒያን በስራዎቻቸው ማለባበስ ይቅር ብለው ወጡ፡፡ እድሮች ከመቅበር መከላከል መፍትሔ ነው ብለው ዘመቱ፤ መንግስት የሚወደስበትን የመከላከል ስራ ሰራ፡፡

ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመቆጣጠር የሰራንው ስራ መንግስትና የኢትዮጵያን ህዝብ አስመሰገነ፡፡ ይህ ውጤት ለዚያ ችግር ትልቅ ድል ሲሆን ለዛሬው መፋዘዝ ደግሞ የኩራት መንስኤ ሆኖ ዳግም ችግር አረበብን፡፡ አሁን ኤች አይ ቪ ኤድስ ከሀገራችን አልጠፋም፡፡ አሁንም ችግሩ በወረርሺኝ ደረጃ ያለ፤ በመቶኛ ሲሰላ ቀላል መስሎ ብዙ ዋጋ ሊያስከፍለን ያሰፈሰፈ ችግር ሆኗል፡፡

በየዓመቱ በፈዘዘ መልኩ ስናከብረው የሰነበትነው የዓለም ኤድስ ቀን ዘንድሮ ህዳር 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በዱከም ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡

ኤች አይ ቪ ኤድስ ስጋት መሆኑ ሲያበቃ መዘናጋቱ አየለ፤ ይህንን ተከትሎ የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች ደስታን ፍለጋ በቆሙበት ጎራ ሲሉ ሌላ የስጋት መንስኤ ተቀሰቀሰ፤ ሴተኛ አዳሪዎች የእኔ ከሚሉት ሰው ጋር በመተማመን ያለ መጠቀም ሲተኙ ህልማቸውን አደጋ ውስጥ የሚከት ችግር ተፈጠረ፡፡

የልማት ኮሪደሮችና ግዙፍ ፕሮጀክቶች የስርጭት መጠኑ ከጨመረባቸው አካባቢዎች መካከል የሚጠቀሱ ሆነ፡፡ መመርመር የቆመበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ተመርምረው ራሳቸውን ያወቁ እና ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸው ሰዎች የግንዛቤ ስራው በመፋዘዙ መድሃኒቱን ለመጀመር መዘናጋት ታየባቸው፡፡

መድሃኒቱን የሚወስዱ ሰዎችም በአግባቡ ጸረ ኤች አይ ቪ መድሃኒቱን በመጠቀም ጤናማ ሕይወት እንዳይኖሩ ሦስቱን ዘጠናዎች ለማሳካት እየሄድንበት ያለው ጉዞ ጎታታ ሆነ፡፡

ዱከም ለምን? ከባድ መኪናዎች ጎራ ብለው ፈታ ያለ ጊዜ የሚያሳልፉባት መዲና ሆነች፡፡ ማሳጅ ቤቶቿ ቁጥራቸው ጨመረ፡፡ የእረፍት ቀናት መዝናኛዎች ምሽት የነጻነት መዝናኛዎች ሆኑ፤ እነኚህ ሁሉ ያለ ጥንቃቄና ያለ ግንዛቤ ሲከናወኑ አደጋው ከባድ ነውና ከኦሮሚያ ክልል ከተሞች በኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ዱከም አስጊዋ እና ቁጥሩ እየጨመረባቸው ከመጡ ከተሞች አንዷ ሆነች፡፡

ሰፋፊ የኢዱስትሪ መንደሮች ያሏት፤ ለረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች የምትመረጠው፣ በእረፍት ቀናት መዝናኛነት ለሸገሮች ተመራጭ የሆነችው ከተማ በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ካልተሰራባት አደጋዋ የከፋ ይሆናል፡፡ እንደ ዱከም ሁሉ ከተሞቻችን የስርጭቱ መጠን ይጨምር ዘንድ ጥንቃቄ በጎደለው፣ መከላከልን ችላ ባለ ሕይወት ውስጥ ናቸው፡፡

በእርስ በእርስ ግጭቶች፣ በውጪ ምንዛሪ እጥረት፣ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ፣ በኑሮ ውድነትና ዋጋ ግሽበት እንዲሁም በስራ አጥነት መከራዋን በምታየው ሀገራችን ኤች አይ ቪ እንደ ቀድሞው ከአቅማችን በላይ ከሆነና ከተስፋፋ ዳግም የሁላችንንም ቤት የሚያንኳኳ መከራ ይሆንብናል፡፡ እናም መፋዘዙ ይብቃ፤ እንመርመር፣ እራሳችንን እንወቅ፣ ኤች አይ ቪን እንከላከል፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close