Connect with us

Ethiopia

ህዝበኝነት አዲሱ የኢህአዴግ ወረሽኝ

Published

on

ህዝበኝነት አዲሱ የኢህአዴግ ወረሽኝ | ሬሞንድ ኃይሉ

ህዝበኝነት አዲሱ የኢህአዴግ ወረሽኝ | ሬሞንድ ኃይሉ

በኢህአዴግ ዕህት ድርጅቶች መከካል ያለው ፉክክር መልኩን እየቀያየረ ቀጥሏል፡፡ ከቅርብ ጊዜት ወዲህም ህዝበኛ የፖለቲካ አስተሳሰብን የያዙ ተግባራት ተበራክተዋል፡፡ ያለፈው ሳምንት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር ደብርጺዎን ገብርሚካዔል በአክሱም ጺወን ንግስ ላይ የነበራቸው አለባባስ መነታረኪያ ቢሆንም ነገሩ ግን የሁሉም ፓርቲዎች ባህሪ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

ኦዲፒ ስልጣን ዕጁ ከመግባቱ በፊት የነበሩትን ጊዜያት ከሞላ ጎደል ህዝበኛ የሆነ አስተሳሰቦችን ሲያራምድባቸው ቆይቷል፡፡በኢህአዴግ ስብስባ ላይ አብሮ የወሰናቸውን ነገሮች ሳይቀር በመድርክ ሲያወግዝ እንደነበርም ይታወሳል፡፡

አዴፓ መግለጫ ባወጣ ቁጥር የአማራን ህዝብ በብቸኝነት ከጎኑ የሚያሰልፍበትን የድንበር ውዝግብ ጉዳይ ደጋግሞ ያነሳል፡፡ ድርጅቱ በድንበር ላይ ያሉ የማንነት ጥያቄዎችን በአፋጣኝ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ከነገርን ይኸው አመት አልፎታል፡፡ ቀጣይ መግለጫውም በዚህ ላይ መመስረቱም የሚያከራክር አይደለም፡፡

ህወሓት የትግራይ ወጣቶች የታገሉለትን ህገ-መንግስት ከፊት አስቀምጣ በትግራይ ያላትን ተቀባይነት ለማስፋት ትዳክራለች፡፡ ለዘመናት ትታው የነረችውን ህዝብ በማይጨበጥ ተስፋ እክስሃለሁ ትላለች፡፡

የደኢህአዴን አመራርም ወ/ሮ ሞፋራያትን ከፊት አስቀምጦ ህዝብ የምክስበት ወቅት ላይ ነኝ ማለት ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ወቅታዊ ወረሽኝ ህዝበኝነት ነው፡፡ አራቱም ድርጅቶች በመሪዎቻቸው በኩል ህዝበኝነትን መፎካከሪያ አድረገውታል፡፡ ለእንዲህ ያለው የፖለቲካ አካሄድ ሩቅ ይመስል የነበረው ህወሓትም ዘግይቶም ቢሆን በተቀላቀለው ውድድር የሚሸነፍ አይመስልም፡፡

ህዝበኝነት(populisim) ብሄርተኝነትን ማዕከል ያደረግ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህ ብሄርተኝነት ደግሞ ፖለቲካዊ አልያም ኢኮኖሚያዊ መልክ ሊኖረው ይችላል፡፡ ኦዲፒ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ህዝበኝነት ጎን ለጎን ለማስኬድ ሲጥር የምንመለከተውም ለዚህ ነው፡፡

ቲም ለማ ከፖለቲካዊ ብሄርተኝነቱ ባልተናነሰ የኢኮኖሚ ብሄርተኝነትም ይስተዋልበታል፡፡ ለሀገር የውጭ ምንዛሬ ግኝት ትልቅ አስተዋጾ የነበራቸውን የማዕድን ማውጫዎችን ነጥቆ ለክልሉ ወጣቶች መስጠቱም ለዚህ ተግባሩ አንድ ማሳያ ነው፡፡ አዴፓም አባይ ኢንዱስትሪ የተባለ ድርጅትን ከመሰረተ በኋላ ከደብረታቦር እስከ ድብረብርሃን የመሰረት ድንጋይ በመጣል የአማራን ህዝብ ቢያማልልም በታሰበው ደረጃ ለመጓዝ ግን አልተቻለውም፡፡

ኦዲፒም ሆነ አዴፓ ህዝበኛ አስተሳሰቦችን ይዘው ባለፈው አንድ ዓመት ሚሊዮኖችን ቢያማልሉም በተጨባጭ ግን በክልላቸው የፈጠሩት ለውጥ ያለ አይመስልም፡፡ ህወሓትም ደብረጺወን ገብረሚካዔልን (ዶ/ር ) ወደ መቐሌ ልካ የክልሉን ብሄርትኝንት እንዲያቆጠቁጥ ከማድረግ የዘለለ ሚናን እስካሁን አልተወጣችም፡፡

በኢህአዴግ ውስጥ የሚሰተዋለው ክልልን ማዕከል ያደረገው የህዝበኝነት ፉክክር መዳረሻው ሀገርን ማቆርቆዝ እንደሚሆን አያከራክርም፡፡ የኢትዮጵያ ችግር በህዝበኝነት ጎዳና አይደለም በተደረራጀ የስትራቴጅ ዕቅድ ቢመራ እንኳን ውጤቱ አጥጋቢ እንደማይሆን የሚጠበቅ ነው፡፡ ይሁን እንጅ የዛሬው መንገዳችን ከዚህም በራቀ መልኩ የየዕለት የፖለቲካ ፍጆታን ግባቸው ባደረጉ ፖለቲከኞች መመራት ሁኗል፡፡

ኢህአዴግ ጥልቅ ታህድሶ አድርጌበታለሁ የሚለውን ያለፈውን አንድ ዓመት ብንመለከት እንኳን የሀገሪቱ ችግር ይበልጥ እየተወሳስበ እንጅ እየተፈታ ሲሄድ አልተመለከትንም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋና ምክንያት አንድ ነው፡፡ ፖለቲከኞቻችን የአጭርና የረጅም ጊዜ ስትራቴጀዎችን ነድፈው ሀገራዊ ችግሩን ከማቃለል ይልቅ የየዕለት ተወዳጅነትን ለማጋበስ መሽቀዳደምን የዘወትር ተግባቸው አድርገዋል፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close