Connect with us

Ethiopia

የህወሓትና እምቢተኝነት እሰከየት? | በሬሞንድ ኃይሉ

Published

on

የህወሓትና እምቢተኝነት እሰከየት ? | ሬሞንድ ኃይሉ

የህወሓትና እምቢተኝነት እሰከየት? | በሬሞንድ ኃይሉ

የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) አስተዳደር ከሀገሪቱም ችግር በላይ በፓርቲው ችግር ተተብትቧል፡፡ የኢህአዴግ ከፍተኛ የስልጣን አካል በሀዋሳ ከወር በፊት ስብሰባ ተቀምጦ ላሉብኝ ችግሮች መፍትሄ አስቀምጫለሁ ቢልም ከ40 ቀናት በላይ ግን አብሮ ለመጓዝ ተቸግሯል፡፡ የድርጅቱ ጉባዔ በስብሰባው ማጠናቀቂያ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን አጠናከረናል የሚል መግለጫ ቢሰጥም፣ ዛሬም ግን ከዚህ በራቀ ተግባር ውስጥ ተዘፍቋል፡፡

አዴፓ ከጉባዔው በፊት የነበረ አቋሙን አሁንም ቀጥሎበታል፡፡ የወሰንና የማንንተ ጥያቄን አልታገስም የሚል ማስጠንቀቂያውን ወደ መቐለ እያስወነጨፈ ነው፡፡ ህወሓት ዛሬም የአዴፓን ድርጊት በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ እያወገዘች ትገኛለች፡፡ በፌደራል መንግስቱ ላይ ያላትም ጥርጣሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ አደባባይ ተሰይሟል፡፡ ኢንጅነር ስመኘው በቀል ባለፈ ማግስት መቐሌ ስታዴም ተግኘተው የኢንጅነሩን ግዳያ ምርመራ ክልሎችም ይሳታፉበት ብለው አዲስ አበባን እንደማያምኗት በተዘዋዋሪ የነገሩን ደብረጺወን ገብረሚካዔል (ዶ/ር) ዛሬ በይፋ የፌደራል መንግስቱን ወደ መተቸት ተሸጋግረዋል፡፡

ከዓመት በፊት አቶ ለማ መገርሳ እራሳቸው የሚሳተፉበትን የደህንነት ምክር ቤት ውሳኔ ተችተው መከላክያ ሰራዊት ካለኛ ፍቃድ ኦሮሚያ ውስጥ ሰው እየገደለ ነው እንዳሉት ሁሉ ደብረጺዎንም (ዶ/ር) የራሳቸው ድርጅት ያዋቀረውን መንግስት ለውጭ ተላላኪና የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ የሚሰራ ሲሉ ወርፈውታል፡፡

የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት ወቅታዊ መግለጫ በብዙ መልኩ ፌደራላዊ ስርዓቱን የሚፈትን መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡

አንድ ተደጋግሞ የሚነሳ ጥያቄ ላቅርብ፡፡ ህወሓት ለፌደራል መንግስቱ እምቢተኛ ሁና ከዘለቀች አጸፋው ምን ይሆናል? የትግራይን ክልል የሚያስተዳድረው ህወሓት ለፌደራል መንግስቱ አልገዛም ቢል ሁለት የመፍትሄ አቅጣጫዎች በቀላሉ ሊነሱ ይችላሉ፡፡

የመጀመሪያው ህገ-መንግስስታዊው ሲሆን ሁለተኛው ፓርቲያዊ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ህወሓትን ለማበርከክ ያላቸው የመጀመሪያ አማራጭ ከህገ-መንገስቱ የሚቀዳ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡

ህገ-መንግስታዊ ጣልቃ ገብነት

ህገ-መንግሰት አንቀጽ 62 ፡9 ላይ በግልጽ እንዳሰፈረው የፌደሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግስቱ በክልሎች ጉዳይ ከለማንም ከልካይ ጣልቃ እንዲገባ ትዕዛዝ መስጠት ይችላል፡፡

ክልሎች ህገ-መንግስታዊ ጥስት ሲፈጽሙ አልያም ለፌደራል ስረዓቱ አሻፈረኝ ብለው አደገኛ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ለፌደራል መንግስቱ ልዩ ስልጣንን የሚሰጠው ይህ አንቀጽ እስካሁን በተግባር የተፈተሸ አይደለም፡፡

በቅርቡ ሱማሌ ክልል ላይ የመከላክያ ስራዊት ካለኢሶዴፓ ጥያቄ ዘው ብሎ ቢገባም በኋላ ላይ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቦለት ነው የሚል ማስተባብያ ተፍጥሮለታል፡፡

በ1990ዎቹ በጋንቤላ የአኛዋክና ኙዌር ጎሳዎች መካከል የተነሳውን ግጭት ለማብረድ የፌደራሉ መንግስት በራሱ ጊዜ ገብቶ እርምጃ ቢወስድም የማስተባባያ ዜናው ግን ከሱማሌ ክልሉ ጋር የተመሳሰለ ነበር፡፡

ይህ አማራጫ ህገ-መንገስታዊ መሆኑ ባያጠያቅም በህገ-መንገስቱ የተካተተው ግን አንደ ለሌሎች አንቀጾች ህዝብ ተወያይቶበት አይደለም፡፡ በዚህ የተነሳም ዛሬም የፖለቲካ ልሂቁ ሳይቀር የፌደራል መንገስቱ በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ መግባት አይችልም ሲል አስተያየት ይሰጣል፡፡

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺወን ገብረሚካዔልም (ዶ/ር) በመግለጫቸው ካለ ክልሉ መንግሰት ፍቃድ የፈደራል ኃይሉ መግበት አይችለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ እውነታው ግን እሱ አይደለም፡፡ እውነታው ፌደራል መንግስቱ በክልሎች ጉዳይ ካለክልሎቹ ፍቃድ መግባቱ ህገ-መንገስታዊ መሆኑ ነው፡፡

ከዚህ በመነሳት የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ አስተዳደር ከህወሓት ጋር ያለው ልዩነት እየሰፋ ከሄደ ያለው አማራጭ የፌደረሽን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲያስልፍ አድርጎ በክልሉ መንግሰት ላይ ዕርምጃ መውሰድ ነው፡፡ በርግጥ ይህ አማራጭ ህገ-መንገስታዊ መፍትሄውን የሚጠቁም እንጅ ለሀገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ ተመራጭ አካሄድ አይደለም፡፡ የትግራይ ህዝብ ለህወሓት እየለገሰው ካለው ድጋፍ አንጻር ከተመለከትነውም መፍትሄው አደገኛ ሊሆን እንደሚችል አያጠራጥርም ፡፡

ሌላው መንገድ

ሁለተኛው የመፍትሄ አማራጭ ድርጅታዊ ነው፡፡ ኢህአዴግ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ እንዳሰፈረው ዕህት ድርጅቶች በራሳቸው ፍቃድ አልያም ታገደው ካባልነት ሊሰናበቱ ይችላሉ፡፡ ወቅታዊውን የፖለቲካ መፍትሄ ትርምስ ለሚመለከት ሰው ሌላኛው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊያሸንፉበት የሚችሉት መንግድ ይኼ ይመስላል፡፡ የኢህአዴግ ምክር ቤት አሰቸኳይ ስበሰባ ተጠርቶ የህወሓትን እርምጃ መኮነን ከዛም በየደረጃው ዕርምጃ መውሰድ፡፡ እንዲህ ያለው መፍትሄም የፌደራል መንግስቱን ሽባ እንዳልሆነ ለማሳየት ካልሆነ በስተቀር ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል አያከራክርም፡፡

ከዚህ ውጭ ሌላ ምን አማራጭ አለ?

ህጋዊ ማዕቀፍ ያላቸው ሁለቱ ወቅታዊው መፍትሄዎች እነዚህ ናቸው፡፡ ነገር ግን ዲፕሎማሲያዊ የሆነው መንገድ ሰፊ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህወሓት መግለጫ በኋላ በነበራቸው የፓርላማ ውሎ ክልሎች አንዳንዴ የፌደራል መንግስቱን መሞገት መቻል አለባቸው ሲሉ መደመጣቸውም ነገሩን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ያላቸውን ዝግጁነት ያሳያል፡፡

ይሁን እንጅ ይህም አማራጭ አማራጭ ዕጦት የወለደው አመራጭ እንጅ ትክክለኛ መፍትሄ አይደለም፡፡ ክልሎች ያሻቸውን የሚተገብሩባትን ሀገር መፍጠርም የፌደራል ስርዓቱን መና ያስቀራል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ስልጣን የይስሙላ ያደርጋል፡፡ ግን ፖለቲካችን የተሸለውን መጥፎ ከመመረጥ ውጭ ሌላ አማራጭ ስለሌለው ለጊዜው እሱን መከተል የሚያዋጣ ይመስላል፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** ኢትዮጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close