Connect with us

Ethiopia

የሴቶች ካቢኔና የፓርላማው ቃልኪዳን ፈረሰ?!

Published

on

የሴቶች ካቢኔና የፓርላማው ቃልኪዳን ፈረሰ?! | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

የሴቶች ካቢኔና የፓርላማው ቃልኪዳን ፈረሰ?! | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

‹‹ካልተሳፈሩበት ቶሎ ተሽቀዳድሞ
ጊዜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቆሞ፤›› 

የሚለውን የከበደ ሚካኤልን ግጥም ሸምድደን ያደግን እኛ የዚህ ዘመን ትውልዶች፣ዛሬም የጊዜ ዋጋ አልገባንም፡፡ አጀንዳችን ዘርና ጎሳ፣ ብሔርና አበሳ ሆኗል፡፡ ሥራችንንም የራሳችንን ፃድቅ የሌላውን ሐጥዓን ማድረግ ሆኗል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ገበሬው እንኳ ስራውን ተረጋግቶ እንዳይሠራ በት/ት ፣በሥራ እና በስደት ከተማ የገቡት ልጆቹ የፈጠሩት አለመግባባት አሳስቦታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ እንኳ ወደ ሥልጣን ከመጡ እነሆ ከ12 ቀናት በኋላ ስምንተኛ ወራቸውን ይደፍናሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ሁለቴ ካቢኔያቸውን አዋቅረዋል፡፡ የመጀመሪያው ካቢኔም ሆነ የኋላኛው ካቢኔ ለሕዝብ ቃል የገቡት ነገር አለ፡፡

ይሁን እንጂ ይህንን ቃልኪዳን መለስ ብሎ ለማስታወስ ትዕግስት የለንም፡፡ ትናንት የተፈጸሙ ነገሮችን እንኳ ለማስታወስ ጊዜ አጥተናል፡፡ እነዚህ ካቢኔዎች ለእኛ ለዜጎች የገቡት ቃል ምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም፡፡ አዲሱ በጀት ዓመት ከገባ እንኳ መንፈቅ ሊሆነው ነው፡፡ ዓመቱ እየተጋመሰ ነው ማለት ነው፡፡

ባሳለፍነው ዓመት የተቋቋመው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ ካቢኔ ክረምት ላይ ከፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ይህም በመገናኛብዙሃን ይፋ ተደርጓል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የያኔዋ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ከኋላ ቆመው ሚኒስትሮቹና የቋሚ ኮሚቴዎቹ አመራሮች ሲፈራረሙ በቴሌቭዥን ታይተዋል፡፡
ዛሬ ግን እኛ አንጠይቅም፡፡ያ ውል የት ደረሰ ማለት የሚገባው አንደበታችን በየእለቱ የሚፈጠሩ ሰበር ዜናዎችን በማራገብ እንዲጠመድ አድርገነዋል፡፡

ለማንኛውም እነዛ ሚኒስትሮችም ሆኑ ተቋማቸው፣ የቋሚ ኮሚቴው አመራሮችም ሆኑ ተጠሪ የሆኑበት ተቋም በአብዛኛው የለም፡፡ ያ ውል በአስፈፃሚውና በሕግ አውጭው መሀል የተፈረመ ነው፡፡ ያኔ 30 ሚኒስትሮች መጥተው ውል አስረዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ያንን ውል የፈረሙ ሚኒስቴር መሥሪያቤቶች ቁጥራቸው ወደ 20 አንሷል፡፡ ቁጥራቸው ማነሱ ብቻ ሳይሆን፣ አዳዲስ ሚኒስቴሮችም ተቋቁመዋል፡ ፡እነዚህ አዳዲስ ሚኒስቴሮች በወቅቱ ውል ያላሰሩ ናቸው፡፡

ያኔ ተጠሪ ተቋማትን የሚከታተሉ የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎችም ታጥፈው ታጥፈው ቁጥራቸው ቀንሷል፡፡ በክረምቱ የውል ሥምምነት ላይ ፊርማ የተቀመጡ ቋሚ ኮሚቴዎች አሁን ፈርሰዋል፡፡ ውል ያልያዙ አዳዲስ ቋሚ ኮሚቴዎችም ተፈጥረዋል፡፡

የክረምቱ ውል ሐሳቡ መልካም ነበር፡፡ ሕግ አውጭው (ፓርላማው) ሕግ አስፈፃሚው ሥራውን በአግባቡ እየሰራ መሆኑን የሚከታተልበት አንድ ዘዴ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በረጅም ጊዜ እቅድ የተያዘ አለመሆኑን የሚያሳየው ውል ከተፈረመ ስድስት ወር ሳይሞላ ውሉን ፈራሚዎቹ ሲፈራርሙ ነው፡፡ ወይ ደግሞ በድጋሚ አዲስ ውል ሲፈረም ሲታይ አልታየም፡፡

አሁን ይህንን ጉዳይ በዓመቱ መጨረሻ እንዴት ብለው እንደሚገመግሙት እንጃ! ነው ወይስ በሴቶች የተሞላው ካቢኔ ይህንን ከፓርላማ ጋር የተገባውን ቃል ኪዳን አንፈልገውም አለ?

ይህ ጊዜን ተከትለን ለማንሄድ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እንደተራ ነገር ሊቆጠር ይችል ይሆናል፡፡ ግን ከበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ ይገመገማል የተባለው የመንግሥት ዕቅድ፣ ስድሰተኛ ወሩ ላይ ሆኖ የት ደረሰ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close