Connect with us

Ethiopia

ያልተጣለው ማዕቀብ ተነሳ!!

Published

on

ያልተጣለው ማዕቀብ ተነሳ!!/ኤርትራ ሆይ እንኳን ደስ አለሽ! | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሐጽዮን

ያልተጣለው ማዕቀብ ተነሳ!!/ኤርትራ ሆይ እንኳን ደስ አለሽ! | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሐጽዮን

ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካዊ አሰላለፍ እንዲህ ያለ አልነበረም፡፡ ሶማሌያን ዩአይሲ እና አልሸባብ እየተፈራረቁባት ነው፡፡ ደቡብ ሱዳን አዲስ ሀገር ሆና አፍሪካን አልተቀላቅለችም፡፡ ዋዜማው ላይ ሆና በኢትዮጵያ አሸማጋይነት ችግር በሰላም እንዲፈታ እየተመከረች ነበርር፡፡

ኤርትራ በአንፃሩ በጦርነት ተሸንፋ ድቅቅ ያለ ኢኮኖሚ እየመራች ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሻዕቢያ ወረራ በኋላ ወደልማት ፊቴን አዙሬያለሁ ቢልም፣ ከአልሸባብ ጂሃድ ሊያመልጥ አልቻለም፡፡ የሞቋድሾው ቡድን ትኩረቱን አዲስ አበባው መንግሥት ላይ አደረገ፡፡ ‹‹በአንድ ቀን የኢትዮጵያ መንግሥትን ጥለን፣ እስላማዊውን መንግሥታችንን አራት ኪሎ እናነግሳለን›› ሲልም ዛተ፡፡

የአራትኪሎው መንግሥት ተበሳጨ፡፡ Deterrence የሚባል ዓለማቀፍ ግንኙነት ላይ አንድ መንገድ የሆነ ቲዎሪም ወደ አእምሮው መጣ፡፡ እናም እሾህን በእሾህ እንዲሉ ሠራዊቱን ወደ ሱማሊያ ሊያዘምት አሰበ፡፡ በዚህ መሀል የመንግሥታቱ ድርጅትና አሜሪካ አንድ ጉድ ይፋ አደረጉ፡፡ ይህ ምስጢር አልሸባብን (UIC) ኤርትራ እንደምትደግፈው የሚያጋልጥ ነበር፡፡

በርግጥም በባድመ የተሸነፈችው ኤርትራ በሞቋድሾ በኩል ብትመጣ አስገራሚ አይደለም፡፡ የብቀላ ፖለቲካ ለለመደው የአፍሪካ ቀንድ ይህ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡

የሆነው ሆኖ የኢትዮጵያ ሠራዊት ወደ ሱማሊያ ገባ፡፡ በሞቋድሾ ጎዳናዎች ላይ የአሜሪካን ሠራዊት አስከሬ ሲጎትት የከረመው የአልሸባብ ሠራዊት፣ በጥቂት ሰሞናት ኦፕሬሽን ብትንትኑ ወጣ፡፡ አሜሪካና እርሷ የምታዝዛቸው የምዕራቡ ዓለም ተቋማትም ለኢትዮጵያ ‹‹እንደው ምን ላድርግልሽ›› ሲሉ ተነጠፉ፡፡ በዚህ መነጠፍ ምክንያትም ኤርትራ ላይ ማዕቀብ ተጣለ፡፡

በርግጥ የዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ኤርትራ አልሸባብን እንደምትደግፍ ማረጋገጫ ነበረው፡፡ ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ ሠራዊት የተሸነፉ የድርጅቱ አመራሮች የሸሹት ወደ አስመራ ነበር፡፡ ይባስ ብሎም አልሸባብ ያሸንፋል ብለው ከሞቋድሾ የቀጥታ ሥርጭት ለመዘገብ የሄዱ የኤርትራ ቴሌቭዥኝ ጋዜጠኞች ተማረኩ፡፡ (እነዚህ ጋዜጠኞች ከዓመት በፊት እስራቸውን ጨርሰው ከኢትዮጵያ ተለቅቀዋል)
ምንም ይሁን ምን ኤርትራ ለአልሸባብ ትጥቅና ስንቅ ትሰፍራለች ተብሎ ታመነ፡፡ ማዕቡም ተጣለባት፡፡ ይህ ማዕቀብ ትናንት ተነስቷል፡፡

ቀድሞ ነገር ይህ ማዕቀብ ገቢራዊ አልነበረም፡፡ ያልወደቀ እቃ አይነሳምና፣ያልጸና ማዕቀብም ተነሳ ማለት ከባድ ይሆናል፡፡ የኤርትራ ባለሥልጣናትን የውጭ ሐገር ጉዞ የሚከለክለውና የጦር መሣሪያ ግዥን የሚከለክለው ይህ ማዕቀብ ተተግብሮ አያውቅም፡፡

ባለሥልጣናቱ የአረብ ሀገራትን፣ ከካይሮ-ጂዳ፣ ከሪያድ-ዶሃ…እንደ ውሃ ቀጂ ሲመላለሱበት እንደነበር ይታወቃል፡፡ የጦር መሣሪያውን የተመለከውም ጉዳይ መቀለጃ ነው፡፡ ኤርትራ ጦር መሣሪያ መግዛት ብቻ ሳይሆን እነ ግብጽ የጦር ሠፈር እንዲገነቡ የፈቀደች ሀገር ናት፡፡

እናም ከኒውዮርኩ የመንግሥታቱ ድርጅት አዳራሽ ወጥቶ መተግበር ያልቻለው ማዕቀብ መነሳቱ ኤርትራን መፈናፈኛ ያሳጣ እንደነበር ተደርጎ የሚቀርበው ዜና አሳማኝ አይደለም፡፡ ይልቅ ኢትዮጵያ አስጣለችባት፣ ኢትዮጵያ አስነሳችላት ቢባል ይቀላል፡፡
የማዕቀቡ መነሳት እልህና መናናቅ ለሞላው ለምሥራቅ አፍሪካ ሠላምም የሚሰጠው ትርጉም ከፍ እንዲያደርገው መመኘት ይሻላል፡፡ኤርትራንም እንኳን ደስ አለሽ እንበላት!!

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** ኢትዮጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close