Connect with us

Ethiopia

ሜቴክ እንደ ፔትሮብራስ/አብዮት ልጆቿን ትበላለች!

Published

on

ሜቴክ እንደ ፔትሮብራስ/አብዮት ልጆቿን ትበላለች! | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

ሜቴክ እንደ ፔትሮብራስ/አብዮት ልጆቿን ትበላለች! | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

ትናንት በኢትዮጵያ ይፋ የተደረገው ወደ ደቡብ አሜሪካ ወስዶ ተመሳሳይ ድርጊት ያስታውሰናል፡፡ ይህንን ነገር ከማስታወሳችን በፊት አንድ ጽንሰሐሣባዊ ማዕቀፍ እናስቀምጥ፡፡

ልማታዊ መንግሥት ዋነኛ ግቡ ሀብትን በፍትሃዊነት ለዜጎች ማከፋፈል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ መንግሥት ሐብቱን የሚፈጥርበትንና የሚቆጣጠርበትን ተቋም በማዕከላዊነት ያቋቁማል፡፡ በብዙ ሐገሮች የሆነው እንደዚያ ነው፡፡

ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ እነ ሉላ ዳሲልቫ በዚያች ሐገር የልማታዊ መንግሥትን አስተሳሰብ ተግብረው ሲንቀሳቀሱ በ1953 ዓ.ም በብራዚል የተቋቋመው የፔትሮብራስ ኩባንያ ወደ ግል ያልዞረውም ለዚህ ነው፡፡ በሐገሪቱ ያለውን ነዳጅ በፍትሐዊነት ለናሽናል ኤኮኖሚው እንዲውል ለማድረግ በመንግሥት የበላይ ተቆጣጣሪነት ሥራውን ቀጠለ፡፡

ቀጥሎ ቀጥሎ ቀጥሎ ግን በብራዚል ግዙፍ ዘራፊ ሰዎች የተሰባሰቡበት ሆነ፡፡ ፔትሮብራስም የዝርፊያ ማዕከል ሆነ፡፡ ከፍተኛ የፖለቲካ መሪዎችም በዚህ ሙስናና ዝርፊያ ላይ አውራ ተሳታፊ ሆኑ፡፡ ሌባ ሲካፈል እንጂ ሲሰርቅ አይጣላም እንዲሉም መጨረሻ ላይ በብራዚል ፖለቲከኞች መሀል ጸብ ተፈጠረ፡፡ በዚህ ጸብ መሐል የፔትሮብራስ ካርድ ተመዘዘና፣ የቀድሞዎቹ ፕሬዚዳንቶች ሉላ ዳሲልቫና፣ ዲልማ ሩሴፍ ዘብጥያ ወረዱ፡፡ 2016 (እ.ኤ.አ) ይህንን ድርጅት በሐላፊነት እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ ተመድበው ለሐገር ሳይሆን ለጓዳቸው አውለዋል የተባሉ ሰዎችም ከፕሬዚዳንቶቹ ጋር ተለቃቅመው ገቡ፡፡

ፔትሮብራስ ለልማት ሥራ ሐብትን በፍትሐዊነት አከፋፍሎ የሀገሪቱን ብሔራዊ ኢኮኖሚ ያሳድጋል ተብሎ ሲጠበቅ፣ የሀገሪቱን ሐብት ተደራጅቶ ሲዘርፍ እንደኖረ ቀሰሩ፡፡ የፔጥሎ፣ የሐገሪቱ ሚኒስትሮች (የፋይናንስ፣የኮንስትራክሽን)፣የፓርላማው አፈጉባኤ፣ የብራዚል ባንክ ፕሬዚዳንት፣ ወዘተ ከርቸሌ ወረዱ፡፡የፔትሮብራስ ኩባንያ አመራሮችም እጣፈንታቸው ይሄው ሆነ፡፡ ሕዝብም ሲዘረፍ የኖረውን ሐብት ጋዜጣና ቴሌቭዥኖች ይተርኩለት ጀመር፡፡ መገናኛብዙሃኑ ‹‹ልማታዊ መንግሥት እራሷን በላች›› አሉ፡፡ አብዮት ልጆቿን በላች እንዲል ደርግ!!

ኢትዮጵያም ሰርፕራይዝ የተደረገች ይመስላል፡፡ ምንም እንኳ ጉዳዩ ገና በሕግ ሒደት ላይ የነበረ መሆኑ ቢታወቅም፣ የኢትዮጵያን ልማታዊ መንግሥት በበላይነት ይመሩ ዘንድ ከተቋቋሙ ተቋማት አንዱ የሆነው ሜቴክ በግዙፍ ሙስና ውስጥ መዘፈቁ በሐገር ወዳድ ሰዎች (የፖለቲካ ሞቲቭ ያላቸውን አላልኩም) ሲነሳ የነበረው ነገር የአደባባይ ምስጢር መሆኑ ትናንት ታውቋል፡፡ ጠቅላሚኒስትሩ ከአንድ ሳምንት በኋላ የምንይዛቸው ሰዎች አሉ ካሉ ከሳምንታት በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ከአሁን በፊት ለነበሩት ጠቅላይሚኒስትር አይታዘዙም ነበር መባሉ ደግሞ የባሰ ልብ ያቆስላል፡፡

የሆነው ሆኖ፣አሁን የተከፈተውን ዘመቻ ከአሁን በፊት ከነበሩት ዘመቻዎች በሙሉ ከፍ አድርጎ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ኢሕአዴግ ከአሁን በፊት፣ ምክትል ጠቅላይሚኒስትሩን ጨምሮ፣ የክልል ፕሬዚዳንቶችንና የፌደራል መንግሥቱን ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሙስና አስሮ ያውቃል፡፡ይሁን እንጂ አብዛኞቹ እስሮች ከፖለቲካ ልዩነት ጋር እየተገናኙ ሲጣጣሉ ነበር፡፡ የአሁኑ እስርም ከዚህ ፖለቲካ ፍላጎትና ተጽእኖ ነፃ ስመሆኑ እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡

አሁን ላለው መንግሥት ታማኝ በመሆናቸው ብቻ ሊታለፉ የማይገባቸውነባር ዘራፊዎችና የሌብነት መዋቅር ውስጥም ሆነ፣ የኢሰብአዊ መብት ጥሰት ውስጥ የነበሩ ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ ፖለቲካዊ ታማኝነትና፣ ብሔር ለምሽግነት እንዳይውሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

በብራዚል ሚካኤል ቲመር የተባለ ሰው ፕሬዚዳንት መሆን ስለፈለገ ዲልማ ሩሴፍን እንዲታሰሩ የፔትሮብራስን ካርድ እንደመዘዘባቸው ሁሉ፣ በኢትዮጵያም ያለው ከግለሰቦች አለመግባባት የሚመነጭ ዘመቻ እንዳይሆን ፕሮፌሽናል ሥራ ይጠብዋል-የጠቅላይሚኒስትር ዓቢይ አሕመድን መንግሥት፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close